Page 1 of 1

እንጉርጉሮ ባህል ሆኖ ምን ይናገር የነበረ?

Posted: 24 Jul 2024, 13:33
by Naga Tuma
በቀላሉ ባህል ማለት ቢቻልም የኣንድ ማህበረሰብ መሠረታዊ ባህል መቼ እንደጀመረ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል?

በቀላሉ ግመል ማለት ቢቻልም ለመጀመርያ ግዜ ግመልን ከዱር እንስሳነት ለሰዉ ልጅ መገልገያነት ማን የት ለማዳ እንዳደረገ በቀላሉ ማወቅ ይቻለል?

ግመልን ለምሳሌ የጠቀስኩኝ ቃሉ ራሱ በሰፊዉ ለማዳ ስለሆነ ነዉ።

ቦረና ጋለ ይባላል። በኣማርኛ ግመል ነዉ። በትግርኛም ተመሳሳይ ይመስለኛል። በእንግሊዘኛ ካሜል ነዉ። በበርካታ ቋንቋዎች ተመሳሳይ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ጨሌ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ እንደ ባህል ተጣብቆ የሚታወቅ ነዉ።

የጎጃም የልጅ ማዘያ አንቀልባ ጨሌዎች የተደረደሩበት ነዉ። ቦረና በእንጉርጉሮ ጨሊ ይላል። በትግርኛ እንጉርጉሮም ዉስጥ ጨሌ ሲባል ሰምቻለሁ።

ስለዚህ ጨሌ በባህል ምን ኣመልካች ነዉ? ንፅህና ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ።

ጎንደር አባ ጃሎ ይላል። ቦረና ጅለ ይላል። አባ ጃሎ እና ጅላ ባህል ዉስጥ ስለምን የሚገልጹ ናቸዉ?

ስለዚህ ከጥንት ግዜ ጀምሮ ነባር ባህል ምን ይናገራል? በጥልቁ ስናዳምጠዉ።

ብዙ ግዜ በኣንድ ቋንቋ የታወቀን እንጉርጉሮ ወደ ሌላ ቋንቋ ተተርጉሞ ብያንጎራጉሩት ማህበረሰቡ ይህ ከባህሌ የተለየ ነዉ ማለት ይችላል? ትግርኛ ተናጋሪዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተተርጉሞለት ቢሰማዉ ይህ ከባህሌ የተለየ ነዉ የሚል ይሆናል? ተርጉሞ ማንጎራጎር የሞከረ ባለሙያ ኣለ?

የጥላሁን ገሠሠን ዋይ ዋይ ሲሉ የምለዉን ኣሳዛኝ እንጉርጉሮ ለመጀመርያ ግዜ ከሰማሁኝ ቀን ጀምሮ ምነዉ ወደ ትግርኛ ተተርጉሞ በተንጎረጎረ ብያለሁ።

የትግርኛ እንጉርጉሮዎችም ምነዉ ተተርጉመዉ በሰማናቸዉ እላለሁ።

ለምሳሌ የልኩኝ የጥላሁን እንጉርጉሮ ይሄ ነዉ።