Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6864
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ጎንበስ በማለት ቅኔ፣ ለቅኔ ልሂቃን

Post by Naga Tuma » 17 Jul 2024, 02:25

ከበደ አበራን የሚመለከት ጉዳይ ስለነበረዉ መገናኘት ፈለገ።

ኣንድ ቀን ከበደ ከበቀለ ጋር ሆኖ፣ አበራ ከአበበ ጋር ሆኖ ከስራ መዉጫ ግዜ ቢሮ አከባቢ ተገጣጠሙ።

አበራ እና አበበ እኩያዎች ቢሆኑም በስራ ምደባ አበራ ከአበበ በላይ ነዉ።

ከበደ እና በቀለ እኩያዎች ቢሆኑም በትምህርት ዉጤት የከበደ ይበልጥ ነበር።

ከበደ አበራን ለመጀመርያ ግዜ በጉዳዩ ምክንያት ሳይተዋወቁ በፊት አበበ አበራን እንደማያከብረዉ በስፍራዉ ይሰሩ ከነበሩት ቀድሞ ከተዋወቃቸዉ ሰራተኞች ሰምቶ ነበር።

አበራ ከአበበ ጋር ሆኖ፣ ከበደ ከበቀለ ጋር ሆኖ ከተገጣጠሙ በኋላ ከበደ አበራን ሰላም ብሎ ጉዳዩን በኣጭሩ ነገራቸዉ።

ጉዳዩ በሃላፊነታቸዉ በቀጥታ የሚመለከታቸዉ ነዉ እና በኣጭሩ ኣየዋለሁ ኣሉት።

ከበደ መልሳቸዉን እንደሰማ በቅጽበት ጎንበስ ብሎ ኣመሰግናለሁ በማለት በቅጽበት ወደ አበበ ዞሮ ቀና ኣለ እና ዐይኖቻቸዉ ተገጣጠሙ። በቁመትም ተመጣጣኝ ስለነበሩ ፊት ለፊት ተገጣጥመዉ ተሰነባበቱ።

ከበደ የኣንድ ግዜ የማጎንበስ ቅኔ ምን እንደነበረ እስከዛሬ ድረስ ለማናቸዉ ግልጽ እንደነበረ ኣያዉቅም።

ያልተደገመ ነዉ። ምክንያቱም ከዛን ቀን ግጥምጥሞሽ በኋላ ከበደ አበራ እና አበበን ኣብረዉ ሆነዉ ኣይቶ ኣያዉቅም።

አበራ እና ከበደ በስራ ምክንያት ይገናኙ ነበር። ከበደ ገበያ ሲሄድ አበራ ሲዝናኑ ከርቀት እያየም መዝናኛ ስፍራዉ ከኣቅሜ በላይ ነዉ ብሎ ያልፍ ነበር።

ምናልባትም ገበያ ሲሄድ ከርቀት ስያዩት የሚወሰልት መስሎኣቸዉ ይሆናል።

በቀለ የከበደ እኩያ ስለሆነ ኣንዳንዴ እግረመንገዱን ጎራ እያለ ያልፍ ነበር።

አራቱ የተገጣጠሙ ዕለት ጎራ ብሎ ትንሽ ተጫዉቶ ነበር።

ስለማጎንበሱ ኣላስተረፍካቸዉም ኣለ። ከበደ ታዝቦት በቅጽበት ዞር ብሎ ስያያዉ በቀለ ወደ ጎን ዞሮ ይስቅ ስለነበረ የትዝብት ዓይኖቹን ኣላያቸዉም። ከበደ በትዝብቱ ጸና።

በቀለ እግረመንገዱን ጎራ እያለ ስያልፍ የወንደላጤን ቤት ቀስ በቀስ እየሞላህ ነዉ ያለ፣ ኣንድ ቀን የወንደላጤን ሽሮ ወጥ ቢጋበዝ ጣፋጭ ነዉ፣ ባለቤትህ ፈርዶባታል ያለ ባለዉለታ ጓደኛ ነዉ።

ቅዳሜ ገበያ መመላለሱ መወስለት እንዳልነበረ ኣንድ ምስክር ነበር።

ዓመታት ሳይቆጠሩም ስለ ትዝብቱ የማያዉቁ የምህንድስና ኮርስ ተማሪዎች በማመጽ ምስክሮች ሆኑ።

ከብዙ ዓመታት በኋላ ኣጭር ጥያቄ ለቅኔ ልሂቃን፥ የማጎንበስ ቅኔዉ ምን ነበር?