⛑️ "ነጩ ዶክተር ካላከመኝ" ⛑️
Posted: 09 Jul 2024, 14:28
"ነጩ ዶክተር ካላከመኝ"

ዶክተር አስናቀው ታፈረ ለረጅም ዓመታት በልብ ህክምና መምህርነት ሞያ ያገለገሉ የጤና ባለ ሞያ ናቸው። ህዝብን ማገልገል ክብር ነው፣ ድሃ ወገንን ከህመም ስቃይ እና ከሞት ለመታደግ በህክምና ሞያ ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው የሚል ፅኑ እምነት አላቸው።
ዶክተር አስናቀው ታፈረ ከአንድ ነጭ ተማሪያቸው ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ህመምተኞችን እየጎበኙ ነው። አንድ በአንድ ህመምተኞቹን እያዳረሱ ፣ አንድ ትግራዋይ የልብ ህመምተኛ ጋር ደረሱ።
ትግራዋዩ ነጭ–አምላኩ ነበሩና " ነጩ ዶክተር ካላከመኝ" ብለው ድርቅ አሉ። እንግዲህ ወጣቱ ነጭ ዶክተር አስናቀው ታፈረን ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ በስራ ልምድ ፣ በግል ተሰጥኦ ይወዳደራል ተብሎ አይታሰብም ። ከእርሳቸው ሰፊ ልምድ ፣ ስር ሆኖ ሊማር በፈቃደኝነት የመጣ ነው።
ትግራዋዩ ግን በሀሳባቸው ፀኑ። ስለዚህ ዶክተር አስናቀው መላ ዘየዱ። እርሳቸው ለነጩ ተማሪ እንደ ረዳት ሆነው ትግራዋዩን ሊመረምሩ። በዚህ መሰረት ነጩ ተማሪ የዶክተር አስናቀውን መመሪያ እየተከተለ ትግራዋዩን መረመረ። በሽታቸውም ታወቀ።
ዶክተር አስናቀው የፈውስ መድሃኒቱን ማዘዣው ላይ ፅፈው ለነጩ ተማሪ አስረከቡ። ተማሪው ደግሞ ለትግራዋዩ።
ትግራዋዩ ፣ መልአክ የመሰለ ነጭ ሰው ስላከማቸው በጣም እየተደሰቱ፣ ገና መድሃኒቱን ሳይወስዱ የመሻል ስሜት እየተሰማቸው ፣ ሆስፒታሉን ለቀው ወጡ።
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ ዶክተር አስናቀው ያንን ትግራዋዩ ሰውዬ ከመንገድ ያገኟቸዋል። የተለመደ ጥያቄያቸውንም ይሰነዝራሉ ፦ "እንዴት ኖት አሁን? ጨርሶ ተሻሎት?"
ትግራዋዩ ሲመልሱ ፦ "አሁን ፍፁም ጤነኛ ነኝ። ጭራሽ አሞኝ አያውቅም። ያ የተባረከ ፈረንጅ በሙሉ ነው የፈወሰኝ"
ዶክተር አስናቀው በትግራዋዩ የጤንነት ሁኔታ ተደስተው፣ አሁን እውነቱን ብነግራቸው ችግር የለውም ብለው አሰቡና፦ "ይኸውሎት አቦይ፣ ፈረንጁ የኔ ተማሪ ነበር ፣ ከኔ ሊማር ነው የመጣው። ያከምዎት ፣ ህመምዎን ያገኘሎት ፣ መድሐኒት ያዘዘሎት እሱ አይደለም፣ እኔ ነኝ" ቢሉ፣
ትግራዋዩ መልሰው፦ "ለዚያ ነዋ የልብ ህመሙ እየደጋገመ የሚነሳብኝ!"