የቃሉ እና ቃልቻ፣ እና ሃሳ እና ሀሳብ ዘፈን ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈዉ እና ድምፃዊ አሊ ብራ እንደዘፈነዉ
Posted: 21 Jun 2024, 17:12
ስለ ኢትዮጵያ ጥንት ታሪክ ያጠኑት ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢሳቅ ኢትዮጵያዊያን በኣብዛኛዉ መሠረታቸዉ ኣንድ ነዉ ብለዉ ደምድመዋል።
ብያንስ ከሙሴ ዘመን እስከዚህ ዘመን መለኮት እያሉ ነዉ የሚኖሩት።
ለዚህ ማስታወሻ ኣንድ ቃል በቂ ነዉ። ቃሉ የሚለዉ ቃል። ቃልቻም ተብሎ ይታወቃል።
እንደ እኔ ግንዛቤ ከሁሉ አከባቢ በላይ ሐረርጌ ዉስጥ የቃሉ ጽንሰ ሀሳብ ለታሪክ ቆይቷል።
እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ጎራ የሚባልበት ቃሉ እና የቃሉ ቤት በአከባቢዉ እንደነበረ ሰምቻለሁ። ሰዉ ጎራ ብሎ ሲወጣ በኣጋጣሚ ኣይቻለሁ።
ካልዘነጋሁ እስከዚህ ዘመን ድረስ ኣዛዉንትን ቃልቻ ይላሉ።
ኣንዱን ጎሳቸዉን ወይም ማህበረሰባቸዉን አፍረን ቀሎ ብለዉ ይጠራሉ። የቃሉ አረቶች ማለት ነዉ። የቃሉ አረት ልጆች ማለት ነዉ።
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1964 ነዉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቦረና ሄዶ ላካ ኣንተ ነህ ብሎ የጻፈዉ።
አሊ ብራ ሃት ኬኘ ቶኮ ማልቱ አዳን ኑ ባሴ ብሎ ከዘፈነ ሰንብቷል።
በቅርቡ ነበር ሃሳ፣ ሂስ፣ ሀሳብ፣ ህሳብ መሠረታቸዉ ኣንድ ቃል መሆን እንደሚችል ኣስተዉዬ የአሊ ብራን ዘፈን ያስታወስኩኝ።
ይህን ሁሉ ሳስታዉስ ኢትዮጵያን እንደ ኣንድ ከለላ ቤት፣ ኢትዮጵያዊያንን እንደ ኣንድ ቤተሰብ ማሰብ ኣይከብደኝም።
በዚህ ዉስጥ ስንቱን ጨቅላ ራስ፣ ጭቃ ራስ፣ ዕድሜ ልክ የማይገባዉ ራስ፣ ዕድሜ ልክ ካድሬ ራስ፣ እና ኣዲስ የፖለትካ ሀ ሁ ቆጣሪዎችን እንቁጠር?