Page 1 of 1

ወይ ፒያሳ! ልክ ያኔ እንደ ዘነጥንባት ዛሬም አማረባት !!

Posted: 17 Jun 2024, 12:17
by Horus
ሲሊማ ኢትዮጵያ! ሞዳ ኖቫ! ዘ ኬቭ ! ባር ቼንትሮ! ትሪያኖ! ጉድ ነው!!

Re: ወይ ፒያሳ! ልክ ያኔ እንደ ዘነጥንባት ዛሬም አማረባት !!

Posted: 19 Jun 2024, 07:14
by Selam/
ድንቄም ማማር!

ድሮ ክትፎህን በልተህ፣ ሲኒማ አይተህ፣ ማኪያቶ ጠጥተህ፣ ባቅላባ በልተህ፣ ድራፍት ግጥም አድርገህ ጠጥተህ ነበር በፒያሳ ጎዳና የምትዘንጠው። ዛሬ የዓብዮትን በዕርዳታ የተሰራ ብልጭልጭ መብራትና ለመጠጥ ውሃ ጠፍቶ አደባባይ ላይ የሚደንሰውን ውሃ አይተህ፣ በአንድ ወር ውስጥ የተሰሩትን ህንፃዎች ተሻሽተህ ፈስህ እየጠማህ መንገዱን ታቀጥነዋለህ።

Re: ወይ ፒያሳ! ልክ ያኔ እንደ ዘነጥንባት ዛሬም አማረባት !!

Posted: 19 Jun 2024, 08:07
by Misraq
ወንድማችን ሆረስ እስቲ ለኮሪደር ልማት ተብሎ ከቦታው ተጠራርጎ ስለተባረረው ማህበረሰብም በነካ እጅህ ንገረን። የዚህን ሥራ ፕሮጀክትስ የማን ካምፓኒ ጨረታ እንዲያሸንፍ ተደርጎ ወሰደ? በእርግጥ ይህ ጥያቄ ሰፋ አድርገው ማሰብ ለሚችሉ ነው። ግን ሞክር እስቲ

Re: ወይ ፒያሳ! ልክ ያኔ እንደ ዘነጥንባት ዛሬም አማረባት !!

Posted: 23 Jun 2024, 10:21
by Union
ድንቄም አለ :lol:

ሱቃቸውን ለተቀሙት እና ለፈረሰባቸው እልፍ አላፍ ጉራጌዎች ለአንድ ሰከንድ እንኳን አስብላቸው

የጉራጌ PP አድማ በታኝ የምንልህ ለዛ እኮ ነው :lol: