Page 1 of 1

በሪሳ ለምን ነበር ስኬታማ ያልሆነዉ?

Posted: 06 Jun 2024, 18:18
by Naga Tuma
ይህን ጥያቄ ከጠየኩኝ ሰንብቻለሁ። ጥያቄዉ እየቆየ ሲሄድ እየጠነከረ ይመጣል።

ካልተሳሳትኩ በሪሳ የመጀመርያ ኦሮምኛ ጋዜጣ ነበር።

ኣሁን ሳስብ ኦሮምኛ የዳበረ ቋንቋ መሆኑ በሪሳ በፍጥነት ማደግ ኣይችልም ነበር ወይ ብዬ እጠይቃለሁ።

ዸንጋ የሚባል የቴሌቭዥን ፕሮግራም በበሳልነቱ በኣጭር ግዜ ዉስጥ ቋንቋዉን የማይችሉትን ጭምር ስቦ እንደነበረ ኣስታዉለሁ።

በሪሳ ለምን ነበር እንደ ዸንጋ በፍጥነት ያላደገዉ?

ይህን ጥያቄ የበለጠ ወሳኝ የምያደርገዉ በቅርቡ የሰማሁኝ የመሸፈት እና የሽሽት ታሪክ ነዉ።

በሪሳ ሕጋዊ ነበር። ከመሬት ለኣራሹ ኣብዮት በኋላ በሪሳ መጀመር ወሳኝ የሆነ ተጨማሪ የሀሳብ ዉይይት መድረክ መሆን ኣይችልም ነበር?

ከአዲስ አበባ ዉስጥ ሽሽትን ያስከተለዉ በዉስጡ በሕቡዕ መደራጀት ነበር ተብሏል።

ሕጋዊ መድረኩን በመጠቀም መታገል እና አዲስ አበባ ዉስጥ በሕቡዕ መደራጀትን የማመዛዘን ዉይይት እና ክርክር ነበረ?

መሬት ለኣራሹ ከሆነ መሬቱ ይልማ፣ ሕጋዊ የቋንቋ መድረኮች፣ ጋዜጣ እና ሬድዮ፣ ከተገኙ በሕጋዊ መድረኮች ቋንቋዉን እናሳድግ የማለት ዉይይት እና ክርክር ነበር?

ኢጭኣት ዉስጥ መግባት፣ ከስልጣን ተነስተዉ የነበሩትን የሃገር መሪዎች ለመመርመር ከደርግ ጋር መስራት፣ እና በሕቡዕ መደራጀት የበሰለ ኣስተሳሰብ ነበረ ወይስ ያልበሰለ የስልጣን ሩጫ?

የበሪሳ ፅሑፎች ዛሬ ለጥናት ቢፈለጉ የት ነዉ የሚገኙት? ኣዘጋጆቹ እና ፀሓፊዎቹ እነማን ነበሩ?

Re: በሪሳ ለምን ነበር ስኬታማ ያልሆነዉ?

Posted: 06 Jun 2024, 19:40
by almaze
From my perspective, the newspaper Wurissa's limited popularity might be attributed to its name, which might not possess enough appeal to captivate the attention of Ethiopians.

Re: በሪሳ ለምን ነበር ስኬታማ ያልሆነዉ?

Posted: 06 Jun 2024, 21:48
by Naga Tuma
almaze wrote:
06 Jun 2024, 19:40
From my perspective, the newspaper Wurissa's limited popularity might be attributed to its name, which might not possess enough appeal to captivate the attention of Ethiopians.
Its official name was በሪሳ, not ዉርሳ, right? If so, why do you distort it?

Do you know the meaning of በሪሳ and concluded that it is unappealing?

Have you ever had a chance to read any of its contents?

Did you ever consider contributing a content?

Do you know where its copies are archived?