Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Noble Amhara
- Senior Member
- Posts: 13512
- Joined: 02 Feb 2020, 13:00
- Location: Abysinnia
Post
by Noble Amhara » 06 Jun 2024, 10:28
አፄ ዳዊት ክፍለ ጦርን ከእስክንድር ጋር ለማያያዝና ለግለሰቦች ለመስጠት የተሠራው ሙከራ ትክክል አይደለም"
******
ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፣ የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ፣ ሻለቃ ሙሉቀን የተላለፈ መልእክት
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፣ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ከአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ፣ ከእስክንድር ነጋ ክፍለ ጦር ጋር በመናበብ ልዩ ልዩ ኦፕሬሽኖችን አካሂደናል።
ነገር ግን የእየ ዕዝ ሰንሰለቶቻችንን ጠብቀን የኩታ ገጠም ስልት ውይይቶችን ከማካሄድና በመናበብ ኦፕሬሽኖችን ከማከናወን ባለፈ በክፍለ ጦር ደረጃ የዕዝ ሰንሰለቱን ባልጠበቀ መልኩ የፈጠርነው ምንም ዓይነት ጥምረት ወይንም ውሕደት የለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፣ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦርን ከእስክንድር ጋር ለማያያዝና ለግለሰቦች ለመስጠት የተሠራ ሙከራ መኖሩን አይተናል። ይህ ትክክል አይደለም።
አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የሚተዳደርና ዕዝ እና ሰንሰለቱን ጠብቆ የሚሄድ ነው።
የአማራ ሕዝብ ዋነኛ ጠላቱ ሥርዓቱ በመሆኑ ሕዝቡ ይህንን አውቆ ጫፍ የደረሰውን የአማራ ትግል ሕዝባዊ አድርጎ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፋለሁ። ከሀገር ውጭ እና በሀገር ውስጥ የምትኖሩ የአማራን ትግል የምትደግፉ፥ የአማራ ትግል የሁሉም ታጋዮች ትግል መሆኑን አውቃችሁ አንዳንድ የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚ ቡድኖች የሕዝብን ትግል ለግለሰቦች ለመስጠት ሲባል ወደ ግለሰብ በመውሰድ የሰፋ ልዩነት ያለ ከማስመሰል ድርጊቶቻችሁ እንድትቆጠቡና ትክክለኛውን መልእክት ከእኛ ከታጋዮች እንድትቀበሉ እናሳስባለን።
ሻለቃ ሙሉቀን፥ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፣ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር አዛዥ
(ሙሉ መልእክቱን በቪዲዮ ይዘን እንመለሳለን