Page 1 of 1

"የስበራትና" "የሰባሪዎች" ምክክር

Posted: 03 Jun 2024, 19:33
by TGAA
የብሄራዊ ውይይት ገለልተኛ በሆነ ብሄራዊ ተቋም ይካሄድ ሲባል “ፍጹም ገለለተኛ መፍትሄ አፈላላጊ ማለት ነው ፤ እርግጥ የሀገር መሪ ተገኝቶ ችግሮቹ ብዙ መሆናቸውን ግንዛቤ ሰጥቶ ሙሉ ትብብሩን ለዚህ ብሄራዊ ተቋም እንደሚያደርግ የበጎ መኞቱን ገልጾ መውረድ አግባብ ቢሆንም አብይ ያደረገው ግን የተገላቢጦሽ ነው ፡፡
1ኛ፡ እንኳን የተቃወሙትን ፖለቲከኞች እንዲሳተፉ ቀርቶ ተቃውመው የጻፉበትን ሳይቀር እሰር ቤት አጎሮ ከማን ጋር ነው የሚማከረው ፡ አዳራሹ የብልጽግና ምክክር እንጂ ብሄራዊ ምክክር ምኑ ነው የሚመስለው? ፤
2ኛ፤ አጀንዳውን ይህ ገለልተኛ ኮሜቴ መርጦ ያሉትን ችግሮች ምን እንደሆነ ጠቁሞ ከሚመካከረውን ሀሳብ ጠይቆ ማቅረብ ሲኖርበት አብይ የጀመረው ስብራት ስባሪ የሚለውን ትርክት ኮሜቴው ላይ በመጫን ውይይቱን ላይ ተስጽኖ ለማሳደር ነው መግብያ ንግግሩን የተጠቀመበት፡፡ ተሰባሪው ማን ነው ሰባሪው ማን ነው ይችን ትርክት የማያውቅ ሰው አለ፤ ሰባሪ ነው በሚል ትርክት ህዝብ እየተጨፈጨፈ ይህን መድረክ ላይ ይዞ እንደመጣ ግልጽ ነው ፡ ስብራት የለም ያለው ዘረኛ አስተዳደር ነው !
3ኛ፤ ለምርጫ እንደመጣ ሰው ሀገሪቱን ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተበትን ሳይሆን ወያኔ የጀመረውን ፕሮጀግት እኔ ጨረስኩት የራስ ውዳሴና ፤ የፓርኬን እዩልኝ ማስተዋወቂ ነው ፤ ይህ የሚወደስ እንኳን ቢሆንም 70% ሀገሪቷ ህግ የማይከበርበት ፤ ከአፍሪካ በውስጥ 4 ሚሊየን ህዝብ ተፈናቃይ ባለበት ሀገር ስለፓርክ ማውራት ከንቱነት ነው 130 ሚልየን ፓርክ ምኑ ነው ፤ ከኦሮሙማው አብይ የወያኔ የኢኮኖሚ ፖላን በብዙ እጥፍ ህዝብ ላይ ያቶከረነው ፤ ዘረፋውና ወገተኝነት ቢኖሩም ፤ አሁን በባሰ ሁኔታ ፤ ደግሞም ህዝባዊ አመጽ በየቦታው ተነስቶ ድሮን እሰከመጠቀም የደረሰ መንግስት ምን ያህል በህልም አለም እንደሚኖር በግልጽ ያሳያል ፡፡
3ኛ፤ የብሄራዊው ገለልተኛ ተቋም በአብይ መሰመር ተሰምሮ ተሰጥቶታል ፤ የአብይን ስልጣን እንዲያጸና እንጂ የሚፈቀድለት ሊነቀንቀው አይደለም ፤
4ኛ፡ ለአሜሪካ ለመሞት ዝግጁ ነኝ የሚል መሪ የውጭ ሴረኞች ሰላማችንን የሚነሱት የሚል የውሸት ጋጋታ ፤ የኢትዮጵያ ትልቁ የሰላም ጠንቅ ፤ አብይና ሽመልስ ናቸው ፤ ትልቁ የሰብአዊ ጥሰት በአሁኑ ሰአት ያለው አብይና ሸመልስ የሚመሩት ኦሮምያ ውስጥ ነው ፤ አሁን ደግሞ አብይ ጦርነት ባወጀበት አማራ ላይ ነው ፡፡
5ኛ፡ አብይ ሀገሪቷን በጦርነት ማመስና ህዝቡን የሚከፋፍል ፖሊስ ማራመድ ብቻ ሳይሆን ጎረቤት ሀገሮች ኢትዮጵያ እንደጠላት እንዲያዩን የማሀይም የውጪ ፖለቲካ እያራመደ ነው፡ መጀመርያ ሀገሪቱን አበልጽግ ጥቅም ካለ በፍላጎት ይመጣሉ ፤ባይመጡም ኢትዮጵያ አወዳድራ ጥሩ ጥቅም ታገኛለች ፡
የውይይት መድረክ እጁና እግሩ በአብይ የታሰረ የአብይ የሳምንት ማደናገርያ ትርኢት ነው ፡፡ የምያሳዝነው እውቀት ያላቸው “ገለልተኝነት “ምን እንደሆነ የሚያውቁ ነገር ግን በፍርሀቻም ሆነ በጥቅም ተይዘው የዚህ የአብይ የማፌዣ የመድረክ ተዋናይ መሆናቸው ነው፡፡ “ ይህ ብሶ አብይ ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ ብሎ ይመጻደቃል ።