Page 1 of 1

ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 02 Jun 2024, 21:43
by Horus
ታዘበ ስንል ምን ማለታችን ነው? ዘበት ስንልስ ምን ለማለት ነው? ትዝብት ስንልስ?

የሚሉሽ ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ!

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 02 Jun 2024, 21:53
by almaze
Horus wrote:
02 Jun 2024, 21:43
ታዘበ ስንል ምን ማለታችን ነው? ዘበት ስንልስ ምን ለማለት ነው? ትዝብት ስንልስ?

የሚሉሽ ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ!

"ታዘበ" refers to an event or situation that is seen by others and may be either positive or negative. "ዘበት" refers to anything that will not be achieved regardless of circumstances.

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 02 Jun 2024, 22:15
by Horus
almaze wrote:
02 Jun 2024, 21:53
Horus wrote:
02 Jun 2024, 21:43
ታዘበ ስንል ምን ማለታችን ነው? ዘበት ስንልስ ምን ለማለት ነው? ትዝብት ስንልስ?

የሚሉሽ ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ!

"ታዘበ" refers to an event or situation that is seen by others and may be either positive or negative. "ዘበት" refers to anything that will not be achieved regardless of circumstances.
ታዲያ እንዴት ነው አንድ ቃል ሁለት የተለያዩ ትርጉሞች የሚኖሩት? አንዱ ማስተዋል ነው አልሽ፤ አንድ ሰው አስተውሎ ነገሩ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ሲተች ወይም ሂስ ሲያደርግ ነው አልሽ። ሌላው ግን አንድ ነገር በፍጹም ሊሆን አይችልም ማለት ነው አልሽ ። የቱ ነው ትክክል?

ለምንድን ነው አንድን ኦብዘርቨር ታዛቢ የምንለው?

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 02 Jun 2024, 22:41
by almaze
"ታዘበ እና ዘበት" These two terms have no relationship as they are spelled differently and carry different meanings. Could you be more specific when these two words have the same meaning in a sentence?

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 03 Jun 2024, 00:09
by Horus
almaze wrote:
02 Jun 2024, 22:41
"ታዘበ እና ዘበት" These two terms have no relationship as they are spelled differently and carry different meanings. Could you be more specific when these two words have the same meaning in a sentence?

ተሳተሻል ። ሶስቱም ቃላት አንድ ናቸው ።

ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ቃሉት በጣም አሳስተው ነው የተጠቀሙት ።

(1) ታዛቢ ማለት ኦብዘርቨር ማለት አይደለም። ኦብዘርቨር ተመልካች ወይም አስተዋይ ማለት ነው። ተመልካች ወይም አስተዋይ ስራው ሁልግዜ የሌላ ሰው ስህተት ወይም መጥፎ ስራ ማየት አይደለም ።

(2) ታዛቢ ማለት ሃያሲ (ክሪቲክ) ማለት ነው ። የሃያሲ (ሂስ አድራጊ) አድራጊ ስራ ሁልግዜ የሌላውን ሰው ስሀተትና መጥፎ ነገር ማየት ነው።

(3) ታዛቢ የሚለው ቃል የመጣው ሂሳዊ (ሂሳቢ)፣ ሃሳዊ (ሃሳቢ) ከሚለው ነው ። ከዚያም ተሃሳቢ ፣ ተሃዛቢ ሆነ ። ስለዚህ ታዛቢ ማለት ሂሳዊ፣ ሂስ የሚያደርግ ሰው ማለት ነው ። ስራውም አንድ ነገር ስህተት ወይም መጥፎ መሆኑ ማሳየት ነው ።

(4) አንድ ነገር ትዝብት ነው ማለት አንቺ አንዳልሺው ፍጹም የማይሆን ነገር ነው ማለት ሳሆን ፍጹም የተሳሳተ ነገር ማለት ነው ። ግን ብዙ ትክክለኛ ትርጉም አያውቀውም። ልክ በገዛ ዳቦዬ ልብልቡን አጣሁት እንደ ሚባለው ።

በገዛ ዳቦዬ ልብልቡን አጣሁን ማለት የዳቦዬ ልብ (ውስጡን) አጣሁት ማለት አይደለም ። የዳቦው ውጭ ወጩን የተቃጠለውን (በሳት የተለበለውን) እንኳ አጣሁት ማለት ነው!

ልክ ይህ ነገር ፍሬ ከርስኪ እንደ ሚባለው ። ፍሬከርስኪ ስህተት ነው ። የሆድ ፍሬ ቁም ነገር ማለት ነው ። ትክክለኛው ፍሬ ፈርስኪ ነው ። ፍሬ ፈርስ ነው፣ ፍንዲያ ነው ማለት ነው ።

ልክ እዚህ ፎረም ላይ ነጋ ጠባ እንደ ሚቀባጥሩት ፍሬ ፈርሶች ማለት ነው :lol: :lol:

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 03 Jun 2024, 14:40
by Naga Tuma
Horus wrote:
03 Jun 2024, 00:09

(3) ታዛቢ የሚለው ቃል የመጣው ሂሳዊ (ሂሳቢ)፣ ሃሳዊ (ሃሳቢ) ከሚለው ነው ። ከዚያም ተሃሳቢ ፣ ተሃዛቢ ሆነ ። ስለዚህ ታዛቢ ማለት ሂሳዊ፣ ሂስ የሚያደርግ ሰው ማለት ነው ። ስራውም አንድ ነገር ስህተት ወይም መጥፎ መሆኑ ማሳየት ነው ።
ሆረስ፥

ድንቅ ጥያቄ ነዉ። የኣንተ ነገር ያስባለኝ። ለምን በለኝ።

የእላ ፊ እላሜን ጽንሰ ሀሳብ በተግባር ለማሳየት እየሞከርኩኝ ነዉ።

እላ ፊ እላሜ ሶስት እርከኖች ኣሉት። ስቴፕ የሚባለዉን ነዉ እርከን ያልኩኝ።

የመጀመርያዉ እርከን ያስተዋሉትን ዕዉነት በኣድናቆት ማክበር ነዉ።

ሁለተኛዉ እርከን የታዘቡት ስህተት ካላ ማሳየት ነዉ።

ሶስተኛዉ ስህተቱን ማረም የሚችል ሂስ መስጠት ነዉ።

በዚህ ሶስት እርከኖች ነዉ የጀመርኩኝ።

ያደነቀኝ ሃሳዊ ያልከዉ ቃል ነዉ። በኦሮምኛ ሃሳ ማለት ዉይይት እንደማለት ነዉ።

እስከ ኣሁን ሃሳ፣ ሀሳብ፣ ሂስ፣ ህሳብ መቀራረባቸዉን ኣላስተዋልኩም። ይደንቃል።

የኣንተ ነገር ያስባለኝ ምናልባት ሃሳ ኦሮምኛ ተዉሶት ነዉ እንጂ የራሱ ቃል ኣይዴለም እንደምትል ገምቼ ነዉ።

ኦሮምኛ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ሸዋ ያልደረሰ ስለነበረ ከዛ በፊት ከዛ ኣልፎ ነበር ብሎ ማዉራት ያሳፍራል ብለህ ታዝበሀኝ ነበር።

እኔ ደግሞ ምናልባት የአባ ባህሬይን ጽሑፍ እንደ ምሉዕ የኣንትሮፖሎጂ ስራ ወስደህ ይሆናል ብዬ ታዝቤህ ነበር። ስሙ ዉስጥ ያለዉን አባ የሚል ቃል እሱ ከእነሱ ወስዶ ይሁን ወይም እነሱ ከእሱ ወስዶ ይሁን መጽሓፉ ማብራራቱን ኣላዉቅም።

የየትኛችን ትዝብት ዘበት እንደሆነ ለኣንትሮፖሎጂስቶች መተዉ እንችላለን።

ያለኝ ሂስ ኦሮምኛ ቃላትን የበለጠ ብታጠና የበለጠ ምሉዕ ምሁር ያደርግህ ነበር ነዉ።

የኢትዮጵያ ቶማስ ጀፍርሰን ነህ እላለሁ። ብዙ ያጠና ነበር ኣሉ፣ እስልምናን ጨምሮ። በድብቅ እስላም ሆነ ተብሎ እስከመታማት ደርሶ ነበር ኣሉ።

ጥናቱ እስከ አቴና ድረስ ነበር ኣሉ። የኣፍሪካዉ ጥንታዊት ግብጥ ስልጣኔ የአቴና ስልጣኔን ቀድሞ የነበረ፣ ምናልባትም የወለደ፣ ቢሆንም እስከ አቴና ድረስ ኣጥንቶ፣ የቀደማትን አክናተንን ሳያጠና፣ የኣፍርካን ስልጣኔ ሳያጠና በመርከብ ተጭነዉ አሜሪካ የደረሱትን ኣፍርካዊያንን ከኣሜሪካ ፖለትካ ኣገለለ።

ይህ ለሃሳ፣ ሂስ፣ ዘበት፣ ትዝብት ማብራርያ መጣጥፍ ኣይሆንም?

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 03 Jun 2024, 15:10
by Horus
ናጋ፣
ምርምርክን ቀጥል አንድ ቀን እውነት ጋ ትደርሳለህ ። ዛሬ በሌላ ጽሁፍ ስለ ተጠመድኩኝ ዝርዝር መልስ ልሰጥህ አልችልም ። ያልከው ግን ስህተት ነው ፤ ሂስና ትዝብት ከውይይት ጋር ፈጽሞ አይገናኝም ። የቃሉ ስር 'ሳሃተ' እና 'ሃሰት' ስህተትና ውሸት ነው ። ስሀተት ማለት ዉሸት ማለት ነው !!! ሰላም ዋል!!

ለመማር የምታደርገውን ጥረት እደግፋለሁ! ግን አይምሮህ ክፍት አይደለም! ወይ የራስክን አፋን ኦሮሞ አጥና ወይም ግዕዝ አጥና ! መነሻህ ያ መሆን አለበት ። ያየህው ቃል ሁሉ ኦሮሞኛ ከመሰለህ አንተ ተማሪ ሳይሆን ባንጎልህ ወስጥ ያለውን ሃሳብክን ብቻ የምታይ ሰው ትሆናለህ ። ያ ደሞ አዲስ ነገር መማር የማይፈልግ የራሱን ምስል ለማረጋገጥ የሚለፋ ሰው ነው ።

መጀመሪያ እውነትን ፍለገህ አግኛት ፣ እሷ ወደ ትክክለኛ ዲስከቨሪ ትመራሃለች ።

Re: ዘበት ምን ማለት ነው?

Posted: 03 Jun 2024, 15:51
by Naga Tuma
Horus wrote:
03 Jun 2024, 15:10
ናጋ፣
ምርምርክን ቀጥል አንድ ቀን እውነት ጋ ትደርሳለህ ። ዛሬ በሌላ ጽሁፍ ስለ ተጠመድኩኝ ዝርዝር መልስ ልሰጥህ አልችልም ። ያልከው ግን ስህተት ነው ፤ ሂስና ትዝብት ከውይይት ጋር ፈጽሞ አይገናኝም ። የቃሉ ስር 'ሳሃተ' እና 'ሃሰት' ስህተትና ውሸት ነው ። ስሀተት ማለት ዉሸት ማለት ነው !!! ሰላም ዋል!!

ለመማር የምታደርገውን ጥረት እደግፋለሁ! ግን አይምሮህ ክፍት አይደለም! ወይ የራስክን አፋን ኦሮሞ አጥና ወይም ግዕዝ አጥና ! መነሻህ ያ መሆን አለበት ። ያየህው ቃል ሁሉ ኦሮሞኛ ከመሰለህ አንተ ተማሪ ሳይሆን ባንጎልህ ወስጥ ያለውን ሃሳብክን ብቻ የምታይ ሰው ትሆናለህ ። ያ ደሞ አዲስ ነገር መማር የማይፈልግ የራሱን ምስል ለማረጋገጥ የሚለፋ ሰው ነው ።

መጀመሪያ እውነትን ፍለገህ አግኛት ፣ እሷ ወደ ትክክለኛ ዲስከቨሪ ትመራሃለች ።
ይሀዉ ደግሞ እንደገና፣ ምናልባት በችኮላ፣ እራስህ ተሳስተህ ሌላዉን ተሳስተሃል ብለህ ለትዝብት ስትተርፈ።

እኔ ያልኩኝ ሃሳ የምባል የኦሮምኛ ቃል ወደ ኣማርኛ ቢተረጎም ዉይይት የሚላዉ የኣማርኛ ቃል ሊሆን ይችላል ነዉ እንጂ ሃሳ እና ዉይይት ተወራራሽ ቃላት ናቸዉ ኣይዴለም። እንደገና ኣንብብ እና ኣንተም ተማር።

እነዚህን ሁለት ቀላል ጥያቄዎች መልስ።

1)ኛ ሃሳ የታወቀ የኦሮምኛ ቃል ነዉ። ኣይዴለም ማለት ትችላለህ?

2)ኛ ሃሳ፣ ሀሳብ፣ ሂስ፣ እና ህሳብ ተቀራራቢ ቃላት ናቸዉ። ኣይዴለም?