Page 1 of 1

ኣስደናቂ ገጠመኝ የዛሬ 33 ዓመት

Posted: 27 May 2024, 16:29
by Naga Tuma
ተማሪ ነበርኩኝ። ለዘመቻ ትምህርት ተቋርጦ ነበር።

ለድሬ ብቁ ነኝ ብዬ ለብላቴ ብቁ ኣይዴለም ኣስብዬ ለጉዞ ዝግጁ ነበርኩኝ፣ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር።

ስድስት ኪሎ ካምፓስ ለፈለጉት ዶርም ነበረዉ፣ ብቁ ላልነበሩት።

ስሙን የማላስታዉስ ዶርም ዉስጥ ለመኖር ፍቃድ ነበረን።

ወደ ግዮርጊስ መሄጃ ቁልቁል የሚወርድ መንገድ ከጀርባዉ የሚታይ ዶርም ዉስጥ ነበርኩኝ።

የዛሬ 33 ዓመት ምሽት ላይ አዲስ አበባ ዉስጥ ይረጩ የነበሩትን ምልክቶች ከሩቅ ኣይተን ዶርሙ ጀርባ ላይ ቆመን ኣየን።

ኣስደናቂዉ ገጠመኝ ወደ ግዮርግስ አከባቢ እያየን አፍንጫችን ስር ያየነዉ ነዉ። ዶርሙ ፊት ለፊት፣ ከመንገዱ ባሻገር፣ መለስተኛ ቪላ የሚባል ነበር።

ሳናስበዉ አንድ ሰዉ ከቪላዉ ወጥቶ በረንዳዉ ላይ ቆሞ እጆቹን ከፊትለፊቱ ወደ ጎኖቹ ዝርግት ኣደረጋቸዉ። ኣልቋል የሚል ዐይነት ምልክት መሆኑ ገባኝ።

ያ ሰዉ ማን እንደሆነ፣ ያ ቤት የማን እንደሆነ እስከ ዛሬ ኣላዉቅም።

ያንን ገጠመኝ ግን ሁሌ ኣስታዉሳለሁ። እግሮቼ እየተዘጋጁ አፍንጫዬ ስር ኣልቋል ትለኛለህ፣ ሞኝህን ፈልግ፣ ብዬ ፈገግ ኣልኩ በዉስጤ።