Page 1 of 1

ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ ... ሕወሓት መልስ ሰቷል

Posted: 23 Apr 2024, 03:12
by MINILIK SALSAWI
ህወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልጽግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

ከኹለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የተፈረሙት ህወሓት እና ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ውህደት ለመፍጠር ድርድር እያደጉ መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ ዘግባለች።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልጽግናን በመቀላቀል ህወሓት ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን ዘገባው አመለክቷል፡፡

ከብልጽግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን፣ ብልጽግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልጽግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም።

አሁን እየተደረገ ባለው ድርድር ህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የሥራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል ተብሏል። ብልጽግና ግን ህወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልጻል።

የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልጽግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት መነጋገራቸው ተገልጿል።

በህወሓት በኩል ብልጽግናን መቀላቀል “ስህተት ነው፣ አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡ አበንጻሩ "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ጸጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልጽግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው” ብለው የሚያምኑ መኖራቸውንም ዘገባው አመላክቷል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ

Re: ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ

Posted: 23 Apr 2024, 03:54
by Axumezana
1st phase has to be tactical alliance ( until next election) with the objective of saving Ethiopia from disintegration and bringing law and order and peace.

2nd phase Strategic alliance ( 4 years after next election) in which TPLF remains an independent party but in alliance with PP

3rd phase integration ( 10 years from now)

Re: ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ

Posted: 23 Apr 2024, 07:33
by Selam/
ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎም ስልቻ፤ ሲጀመር መቼ ተለያዩና። ወያኔና ኦነግ-ሸኔ ሙሉ በሙሉ መወገድ ያለባቸው የአንድ እናት የአንድ አባት ልጆች ናቸው።

Re: ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ

Posted: 23 Apr 2024, 09:51
by MINILIK SALSAWI
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር "ለመቀላልቀል" ውይይት አላደረግኩም ሲል አስታወቀ። የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉ ...... https://mereja.com/amharic/v2/943009

Re: ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ ... ሕወሓት መልስ ሰቷል

Posted: 23 Apr 2024, 15:11
by Selam/
ብልፅግናና ወያኔ - ሁለት ልፋጫሞችና ከይሲ ፍጥረቶች። እርስ በእርሳቸው ከሚሰዳደቡ ፣ ቢገዳደሉ ይሻላል።




Re: ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ ... ሕወሓት መልስ ሰቷል

Posted: 23 Apr 2024, 15:41
by Digital Weyane
ጌታችን ማይክ ሀመር ከብልፅግና ጋር እንድንደመር ትእዛዝ ከሰጡን፣ በSelam/ ለመደመር ዙጉጁ ነን። :roll: :roll:

Re: ህወሓት ብልጽግናን ለመቀላቀል እየተደራደረ መሆኑ ተሰማ ... ሕወሓት መልስ ሰቷል

Posted: 23 Apr 2024, 16:38
by Selam/
ብቅ ጥልቅ ሻቦ - በጣም ስላሳከከህ የበፊቱ ፅሁፌን በዚህኛው አስተካክዬዋለሁ፥

<> ወያኔ፣ ሻቢያና ብልፅግና ፡ ሶስት ልፋጫሞችና ከይሲ ፍጥረቶች ናቸው። እርስ በእርሳቸው ከሚሰዳደቡ ፣ ተገዳድለው ከምድረ ገፅ ቢጠፉ ይሻላል።
:roll: :roll:
Digital Weyane wrote:
23 Apr 2024, 15:41
ጌታችን ማይክ ሀመር ከብልፅግና ጋር እንድንደመር ትእዛዝ ከሰጡን፣ በSelam/ ለመደመር ዙጉጁ ነን። :roll: :roll: