Page 1 of 1

EBRAHIM FURNITURE! ተግባረ እጅ የሌለው ሕዝብ ካልቸር የለውም!

Posted: 08 Apr 2024, 22:08
by Horus
በሰው ልጆች አለም ውስጥ ያለው ሰውና የሰው ስራ (የሰው ቢሄቪየር) ብቻ ነው። ይህ ካልቸር እንለዋለን። የሰው አለም ማለት የሰው ካልቸር አለም ነው ። የሰው አለም የተፈጠረው በሰው እጅ ነው ። ካልቸር የእጅ ስራ ነው ። ተግባረ እጅ የሌለው ሕዝብ ካልቸር የለውም።


Re: EBRAHIM FURNITURE! ተግባረ እጅ የሌለው ሕዝብ ካልቸር የለውም!

Posted: 09 Apr 2024, 01:06
by Horus
አለም የተሰራው ከሁለት ነገር ነው ፤ ከፍጥረት ሥራና ከሰው ሥራ! የሰው ሥራ ሁሉ ፣ ሰው ሰራሽ ነገር ሁሉ በአንድ ስም ይጠራል፤ ካልቸር ይባላል ። አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ የሚለየው ብቃት ወይም ስልጣኔ ካልቸር ብቻ ነው ።