Page 1 of 1

ስለ ቅርብ የኢትዮጵያ ታሪክ ወይም የታሪክ ገድሎች ጥያቄዎች

Posted: 03 Mar 2024, 03:30
by Naga Tuma
ከእነዚህ የኢትዮጵያ የቅርብ ታሪኮች ወይም የታሪክ ገድሎች የትኛዉ የበለጠ ኣሳማኝ ነዉ?

የ1896 እ ኣ አ የአድዋ ድል
የ1963 እ ኣ አ የኣፍሪካ ኣንድነት ድርጅት ምስረታ ጉልህ ተሳትፎ
የ1991 እ ኣ አ ቻርተር

እስቲ ኣንድ በኣንድ በድምጽ ብልጫ እንገምት። ለሶስቱም ጥያቄዎች ድምጽ መስጠት ኣንድ በኣንድ ቀጥለዉ ይመጣሉ።

Re: ስለ ቅርብ የኢትዮጵያ ታሪክ ወይም የታሪክ ገድሎች ጥያቄዎች

Posted: 07 Mar 2024, 15:56
by Naga Tuma
ዝም ብዬ ሳስብ እና ሳሰላስል የአድዋ ድል እና የኣፍሪካ ኣንድነት ድርጅት ምስረታ የኢትዮጵያ ሚና በኢትዮጵያ፣ በኣፍርካ፣ እና በአለምኣቀፍ ደረጃ ጉልህነት የቻርተሩን ጉባዔ የምያሳንስ ይመስለኛል።

እኔ የጉባዔዉ ግዜ ያለ አቅሜ ዱላ ፈላጊ ነበርኩኝ። ጉባዔዉን በቲቪ ኣልተከታተልኩትም። በሬድዮ ኣልሰማሁትም።

ቻርተሩ መፈረሙ ነዉ ወደ ሰላማዊ ትግል የመለሰኝ።

ስለዚህ የእኔ ስለቻርተሩ ማሰላሰል ሚዛናዊነት የጎደለዉ ሊሆን ይችላል።

ታሪኩ እንዴት ነዉ በጥልቀቱ የሚጻፈዉ?