Page 1 of 1

ዉይይታችን ከደጃ ኒዉስ ዘመን እስከ መረጃ ፎረም

Posted: 28 Feb 2024, 07:21
by Naga Tuma
ኢትዮጵያኖች ኢንተርኔት ዉስጥ ሲወያዩበት ያየሁኝ የመጀመርያዉ መድረክ ደጃ ኒዉስ ይባል ነበር። ካልዘነጋሁ።

ያን ዉይይት እንደ ድሮ ዘመን ዉይይት ነዉ የማስታዉሰዉ።

እዚህ አሜሪካ ትምህርት ቤት ነበርኩኝ። ኣልፎ ኣልፎ ግዜ ሳገኝ ኣነበዉ ነበር።

ኣንድ የማልረሳዉ ዉይይት ነበር።

ኣንዱ ተሳታፊ ኣወትሮ የኢትዮጵያ ይህ ችግር ያ ችግር እያለ ሲጽፍ ስለ ችግሯ ላይ ሳይሆን መፍትሄ ላይ ለምን ኣታተኩርም ለማለት እኔም ፎረሙ ዉስጥ ገብቼ ሀሳብ ለመስጠት ከጅሎኝ ነበር።

እኔ ለማለት የፈለኩኝን አስተሳሰብ ሌላ ተሳታፊ ጽፎ ኣነበብኩኝ። መልካም አስተሳሰብ ነዉ፣ ተነቧል ብዬ ኣለፍኩኝ።

የተሳታፊዉ የመድረክ ስም ገብርዬል እንደነበረ ነዉ የማስታዉሰዉ። ዘንግቼም ሊሆን ይችላል።

በኣጭሩ የሰጠዉ አስተሳሰብ ነጥቡ ወይም በእንግሊዘኛ ዘ ፖይንት ስለችግሯ ብቻ ማዉራት ሳይሆን ስለ መፍትሔ መወያየት ነዉ የምያስፈልገዉ የሚል አይነት ነበር።

ኣልፎ ኣልፎ ግዜ ኣግኝቼ ያዛን ፎረም ዉይይት ሳነብ የዚህ የሰዉ ጎሳ፣ የዛ የሰዉ ጎሳ ኣዙሪት እዛ ፎረም ላይ መጀመሩን ኣስታዉሳለሁ።

ያንን ኣስተዉዬ እዚህ ኣዙሪት ዉስጥ ኣልገባም ብዬ የነበርኩበት ትምህርት ላይ ትኩረቴን ኣበዛሁ።

ተሯሩጬ ሌላ ድፓርትመንት ድረስ ሄጄ በርካታ የኢንደስትርያል ኢንጂነርንግ ኮርሶችን ወሰድኩኝ። ለማግኘት ባልጠይቅም ለተጨማሪ ድግሪ የምያበቃ ያህል።

ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ የኢኮኖሚ ስንቅ ይሆነኛል ብዬ። ለሃገር ይጠቅማል ብዬ።

እንደዛ እየተሯሯጥኩ ነዉ ኣንድ ቀን እኩለለሊት ገደማ ከቢሮ ወደ ቤት ስሄድ ዉስብስብ የሆነ ኣዲስ የሂሳብ ቀመር የተገለጠልኝ። ቦታዉ፣ ትልቅ የመኪና ማቆምያ፣ ሁሌም ኣይረሳኝም።

ኣዲሱን ዉስብስብ የሂሳብ ቀመር አሰራሩን ጨርሼ ሳቀርብ ዉስብስብነቱ የገባቸዉ የአሜሪካ ፕሮፌሰሮች ኣንድ አጭር ጥያቄ ጠየቁኝ።

ቀላል ጥያቄ ነዉ ብዬ መለስኩኝ። መለስኩኝ ካልኩኝ በኋላ ኣልመለስክም አይነት ጥያቄ መልሰዉ ጠየቁኝ። የመጀመርያ መልሴን እያብራራሁኝ እንደዛ መልሰዉ መጠየቃቸዉ ዉስጤን ከነከነኝ።

መልሴ እንዳላጠገባቸዉ ተያይተዉ ተዉኝ። የበለጠ ከነከነኝ።

ጥያቄያቸዉ ይህን ዉስብስብ የሂሳብ ቀመር ይዘህ ወደ ኢትዮጵያ ብትመለስ ስራ ላይ ማዋል ትችላለህ ወይ ነዉ።

የእኔ የስራ ልምድ ያነሰዉ አካደሚክ ኣጭር መልስ ኣዎ ይቻላል ነዉ። ተጨማሪ ማብራርያዬ ኢትዮጵያ ስታድግ ለምን ኣይቻልም ነዉ።

ቆይቼ ሳሰላስል የጠበቁት መልስ ዉስብስብነቱ ስራ ላይ ለማዋል ኣስቸጋሪ ነዉ ማለትን ነዉ።

ስለ ዉስብስቡ ኣዲስ የሂሳብ ቀመር ኢትዮጵያ ዉስጥ ስራ ላይ ማዋል መቻል ጥያቄያቸዉ እና መልሴ ግዜ ይፍታዉ።

ሰንብቼም ዶክተር አለማየሁ ብሩ የሚባል የማላዉቀዉ ሰዉ ጽሁፍ ዉስጥ ከዛ በፊት ሰምቼ የማላዉቀዉን የድሮ ታሪክ በኣጋጣሚ ኣነበብኩኝ። በገን ዱኤ አርጌ ኣልኩኝ፣ ለራሴ።

እኔም ፎረም ዉስጥ ብቅ ብዬ አስተያየቴን ማካፈል ከጀመርኩኝ ሰንብቻለሁ።

ዓመታት ኣልፈዉ ኣበረ እዚህ ፎረም ላይ ስለዛዉ የድሮ ታሪክ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ጽፎ ኣነበብኩኝ። ተመሳሳይ የድሮ ታሪክ የጻፉት ዶክተር አለማየሁ ብሩ እና አበረ ተወያይተዉ ስለድሮ ታሪክ ተመሳሳይ ታሪክ የጻፉ ኣይመስለኝም።

የዚህ አስተያየት ዋና አላማ ዉይይታችን ከደጃ ኒዉስ ዘመን እስከ ዛሬ መረጃ ፎረም ድረስ ምን ያህል የጥራት እድገት ኣሳይቷል ነዉ።

ደጃ ኒዉስ ላይ ይጽፍ የነበረ ጋብርዬል ዛሬ እዚህ ፎረም ላይ ብቅ ብሎ ቢወያይ ምብ ያህል የጥራት ወይም ኳልቲ ልዩነት ልያሳይ ይችላል? እዛ ላይ ይሳተፉ የነበሩ ሌሎችም እንደዛዉ።

መልሱን ለሁላችንም እተዋለሁ።

ኣንድ የታዘብኩኝን ግን ላካፍል።

እንደ እኔ አስተያት የኣብዛኛዉ ኢትዮጵያዊያን የፖለትካ ጥያቄ የስርዓት ጥያቄ ነዉ። መጀመርያ ምንም አይነት ስርዓት ይሁን ስርዓት ይኑር ነዉ። ስርዓት ሲኖር ወደ ተሻለ ስርዓት መሻገር ይመጣል።

ስርዓት የሌለበት ሃገር ነዉ ኣቀንቃኝ ተነስቶ ሌንጭ አጀጀ ህን ፉዸቱ ብሎ አደባባይ የሚወጣዉ።

ገብቶት ይሁን ሳይገባዉ የዚህ ፎረም ዘመን ነጥቡ ወይም ፖይንቱ ምንድነዉ ብሎ ወድያዉ ነዉ የጠየቀዉ።

ገብርዬል የደጃ ኒዉስ ዘመን ነጥቡ ችግሩ ሳይሆን ስለመፍትሔ መወያየት ነዉ ካለበት ቀን ጀምሮ ዘመን እዚህ መረጃ ፎራም ላይ ነጥቡ ምንድነዉ ብሎ እስከ ጠየቀበት ቀን ድረስ ዉይይታችን እና የመወያየት ችሎታችን ምን ያህል የጥራት እድገት ኣሳይቷል?

ኣሁንም መልሱን ለሁላችንም እተዋለሁ።

መዘንጋት የማንችለዉ የኣብዛኛዉ ኢትዮጵያዊያን የሆነ የስርዓት ጥያቄ ነዉ።

ስርዓት ሲኖር ኣልታዘዝም ባይ ኣይኖርም። ልዘዝ ባይም ኣይኖርም። ስርዓት ኣዛዥ፣ ሁሉም በስርዓት ስር ታዛዥ ይሆናሉ።

የሰዉ ልጅ ዋነኛ ስልጣኔ ይህ ኣይዴለም? ስርዓትን ከሰዉ በላይ ማድረግ፣ ሰዉን ከስርዓት በታች ማድረግ፣ እና ስርዓትን መተግበር?

የገዳ ስርዓትን የወለደዉ ስርዓት ኣልበኝነት ኣይዴለም? የጥንት ግሪክ ስልጣኔ የተዋሰዉ ስርዓትን ኣይዴለም?

አሜሪካ የደረሱት ኣዉሮፕያዊያን ኣጥንተዉ የተከሉት ስርዓትን ኣይዴለም?

ከኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ትምህርት ቤቶች የበለጠ ትምህርት ያገኘዉ ከቦረናዎች ነዉ ያለዉ ዶክተር ገመቹ መገርሳ ከሁሉ በላይ ከቦረናዎች የተማርከዉ ምንድነዉ ቢባል ምን ይላል?

ስለ ስርዓት ምንነት ከእነሱ ምን ተምሯል?

የደርግ ዘመን ምን ኣስተምሯል? መንግስቱን በመቃወም ትንሹ መንግስቱ መሆንን ነዉ?

ካልተሳሳትኩ ተፈሪ በንቲ፣ ኣማን ኣንዶም፣ እና ኣጥናፉ ኣባተ መሪዎች ነበሩ።

እስቲ የሩቅ ሃገሮቹን ማርክስ፣ ኤንግልስ፣ እና ሌኒን ከማለት ሃገር በቀሉን ሱንሱማ ብላችሁ ወልስማን ኣዳምጡ ቢባሉ የሚበጅ ኣልነበረም?

የጥንት የጥንት ነዉ። ገዳን ያዋለዱት ዘመናዊ የፖለትካ ሳይንስ የተማሩ ኣልነበሩም። ስርዓትን የተዋሱት የጥንት ግሪክ መንገደኞች የፖለትካ ሳይንስ የተማሩ ኣልነበሩም።

የጥንት ግሪኮችን ስርዓት ኣጥንተዉ አሜሪካ ዉስጥ የተከሉት የፖለትካ ሳይስንስ ፕሮፌሰሮች ኣልነበሩም።

ታድያ ምን ያህል ኣለማወቅ ወይም ኣለማስተዋል ነዉ ዛሬ ኢትቶጵያ ዉስጥ ስርዓት ማለትን የማያስችለዉ?

ኣንድ ግዜ መንገድ ላይ የተገናኝን የኣየርላንድ ሰዉ ሙሴ በዘመኑ ምድር ላይ ከሁሉ በላይ ገናና ነበር ኣለኝ። እኔ ሰምቼ ኣላዉቅም ነበር።

አሜሪካ ሃገር ነኝ ብላ ከተቋቋመች ገና ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት ኣልሞላትም። ሙሴ የኖረዉ ከሶስት ሺህ ዓመታት በፊት ነዉ።

ኣህጉር ያህል መሬት ቀምታ፣ የኣህጉር ያህል ሕዝብ ኣጥፍታ፣ ከሌላ ኣህጉር ሕዝብ በጅምላ ኣፍና ወስዳ፣ የጥንት ስርዓትን ኣጥንታ ተክላ ዘ ግሬተስት ካንትሪ ኢን ዘ ህስትሪ ኦፍ ማንካይንድ እንባላለን።

በኢትዮጵያ ሁለት ሺህ አስራ ስድስት ዐመተ ምህረት ኢትዮጵያዊን ስለ ስርዓት ሰልጥን እንበል፧

I am not a student of providence. Sometimes, I wonder if it isn’t providential that Ethiopia would be extricated from about two thousand years of protracted identity struggle, about five hundred years of brutal struggle, and about a century of ignorance of its ancient civilization by some quarters in its own.