Page 1 of 1

ፈርጄ ብዙው የአማራ ፋኖ ትግል---> ፋኖ የተሳፋፊ ወራሪ የውጭ እና የውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች መቅሰፍት። የወደፊቱ የአገር መከላካየ ኃይል

Posted: 27 Feb 2024, 17:53
by Abere
ፈርጄ ብዙው የአማራ ፋኖ ትግል---> ፋኖ የተሳፋፊ ወራሪ የውጭ እና የውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች መቅሰፍት። የወደፊቱ የአገር መከላካየ ኃይል

በርካታ የኢትዮጵያ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች የፋኖ ድል ማድረግ የሚያበሳጫቸው እንጅ ከልብ የሚደግፉት አይደልም። የኢትዮጵያ ጠላቶች የመጀመሪያም የመጨረሻውም ጠላታችን ብለው የሚፈርጁት የአማራን ህዝብ። ለበርካታ ዘመናት አውጥተው አውርደው አሰላስለው የተረዱት ቢኖር የአፍሪካ ቀንድ እያሉ በእነርሱ ቋንቋ የሚጠሩት እንደ ፈለጉት ለመንዳት እና ለመግዛት የሚችሉት አማራን በማጥፋት ወይም ተጽኖውን ሽባ በማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ የአማራ ህዝብ ለዘመናት ሲደረግበት የኖረውን እና አሁንም እያሆነ ያለውን የዘር ማጽዳት ከዕቁብ ያልቆጠሩበት ምክንያት ግልጽ ነው። አማራን ለማስፈጀት መሳሪያ እና ገንዘብ የማቀበል ያህል እና ከዚያም በላይ ይመስላል። የአማራ ህዝብ እራሱን በእራሱ ነጻ የማውጣት ትግል ተጧጡፎ መቀጠል ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ጭምር ነው። ትግሉ ፈርጀ ብዙ ነው። የአማራ ጥላቶችም ብዙዎች ናቸው። አማራ ከኦፊሴላዊ ከጥላቱ እራሱን መጠበቅ ይችላል ወዳጅ ከሚመስሉ የውጭ እና የውስጥ አጭበርባሪዎች በበሳል ስልት እና ስትራቴጅ ግን መታገዝ ግድ ይለዋል። ለዚህም አጭበርባሪ ዩቲዩበሮችን እንደ ማሰራጪያ ከመጠቀም መቆጠብ እና የእራሱ ኦፊሴላዊ መገናኛ ብዙሃን መፍጠር የግደታ ነው። ያለ መገናኛ ትግል ጉዞውን እረጅም ማድረግ ብቻ ሳይሆን ጥላት እንደ አረም በቀላሉ ትግሉን ይተበትበዋል።