Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC:-ኬሪያ ኢብራሂምን እና ሙሉ ገብረእግዚአብሔር ከህወሓት ፓርቲ ተባረሩ

Post by Za-Ilmaknun » 23 Feb 2024, 14:21

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በጦርነቱ ወቅት ለፌደራል መንግሥቱ እጅ ሰጥተው ምሥጢር አሳልፈው ሰጥተዋል ያላቸውን ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ከፓርቲው ማባረሩን አስታወቀ።

ህወሓት ከድርጅቱ ያባረራቸው ሁለቱ ሴት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ ከጦርነቱ በፊት በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩት ኬሪያ ኢብራሂም እና ሙሉ ገብረእግዚአብሔር ናቸው። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሐሙስ የካቲት 14/2016 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ኬሪያ ኢብራሂም እና ሙሉ ገብረእግዚአብሔር “ለጠላት እጃቸውን ሰጥተው ምሥጢር አሳልፈው ሰጥተዋል” ተብለው በድርጅቱ ደንብ መሠረት ከማዕከላዊ ኮሚቴ እና ከህወሓት አባልነት እንዲባረሩ ወስኗል።

What is next? :|

https://www.bbc.com/amharic/articles/crg76jeznd3o