Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4615
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ስለ ፋኖ ያለኝ አመለካከት....ፋኖ ግዴታ ኢትዮጵያን አዳኝ ሊሆን አይችልም ... የኤርትራም ጠባቂ ሊሆን አይችልም

Post by Abaymado » 11 Feb 2024, 12:15


ከስድስት ዓመት በላይ ER ላይ አንደመቆየቴ አና ስለ አማራ ብዙ በመፃፌ : አንዲሁም በተለይ ለጥቂት ግዚያት ስለ አማራ ፅፌ ስለማምላቅ አንዲሁም ሁሉም የራሱን መላ ምት ሲሰጥ አንደመቆየቱ አኔም የራሴን አመለካከት ማጋራት ፈልግሁ:: ብዙዎች የፋኖ ትግል የእነሱንና የሚወክሉትን የሚደግፍ ሲመስላቸው ፋኖ ጀግና እያሉ ሲያወድሱ: ደሞ በሌላ ጎኑ የፋኖ ትግል ለእነሱ ፋይዳ አንደሌለው ሲረዱ ፋኖን ብቻ ሳይሆን መላ አማራን መሳደብ ስራቸው አርገው ይዘውታል::

ፋኖ ጠንካራ አና ደካማ ጎን አለው::
ከደካማ ጎኑ ብጀምር:
1- በየቦታው አየተገኙ መግለጫ መስጠት ስራቸው ሆኗል:: ዝም ቢሉ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ::
2- ፋኖ ራሱ ሰሜን ሸዋ ደራ ክልል ገብቶ የኦሮሞን ሰራዊት አጥቅቶ ተቆጣጥረያለሁ ካለ በህዋላ : ግን የኦሮምያ ኃይል ገብቶ ከተማውን ማቃጠሉ ይታወቃል:: ይህ ለምን አስፈለገ? ይህን ቦታ ለምን ለወራሪው አሳልፈው ሰጥተው ሕዝቡን ለጥቃት ያጋልጣሉ?

ጠንካራ ጎኑ ግን አዚህ መዘርዘር ይከብዳል:: አማራ ማንነቱን አግኝቷል:: ጦርነት ማንነትን ያስከብራል::ፋኖ አማራን አስከብሯል:: የፋኖ ትግል አገሪቷ ላይ የሚያመጣው ተፅኖ ቀላል አይደለም::

የኦሮሞን ጥጋብ አስተንፍሶታል:: ባብዛኛው በሚባል መልኩ በሌሎች ክልሎች የነበረ የአማራ ግድያና መፈናቀል ቆሟል ማለት ይቻላል::
መንግስት ራሱን አንደገና አንዲፈትሽ አርጎታል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራ ነፃ ያወጣናል ብሎ ካሰበ ተሳስቷል:: አማራ የራሱ አላማ አለው ብዬ አስባለሁ:: ሲተርፍ ግን ኢትዮጵያን ይታደጋል::
አማራ ዋናው አላማው
1- ማንም አንደማይገዛው ማረጋግጥ
2-የተወሰደበትን መሬት ከአጁ አንዳይወጣ ማረግ
3- የአማራ መፈናቀልና ሞት አንዲቆም ማረግ ሌሎችም
4- በይ አንጂ የበይ ተመልካች አለመሆኑን ማሳየት እና ሌሎችም ናቸው::

ትግራይን በተመለከተ :
ከትግራይ ጋር ማበር የሚባለው ነገር ተቀባይነት አይኖረውም:: ለምን? ለዚህ ሁሉ መዘዝ ተጠያቂው ወያኔ በመሆኑ ነው::

ወያኔ :
1-አገሪቷ ወደብ አልባ አንድትሆን ያረገ ነው::
2-አማራን አጎዳለሁ ብሎ በማሰብ ለኦሮሞ የማይታወቅ ክልል ሰጥቶታል:: ይህ ነው አሁን መስዋትነትን አያስከፈለ ያለው::

ትግራይ በጣም ችግር ላይ ናት አናም ማምለጫው መንገድ በመተባበር ስም ፍላጎታቸውን ማሳካት ነው::

ኤርትራ

shabo ፋኖ የኤርትራ ዘብ አንዲሆን ይፈልጋሉ:: አማራ የማንም ጠባቂ አይደለም:: አኛ የምናምነው ሰጥቶ በመቀበል ነው::

አናም አማራ ለማንም ኃይል ታዛዥም ሆነ ተገዝ አይደለም::

Axumezana
Senior Member
Posts: 19086
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ስለ ፋኖ ያለኝ አመለካከት....ፋኖ ግዴታ ኢትዮጵያን አዳኝ ሊሆን አይችልም ... የኤርትራም ጠባቂ ሊሆን አይችልም

Post by Axumezana » 11 Feb 2024, 15:00

ፋኖ፥ ሌሎች፥ የኢትዮጵያ፥ ህዝቦችን፥ አስተባብሮ፥ አገር፥ መምራት፥ ይችላል። ዋናው፥ አላማ፥ መሆን፥ ያለበት፥ እርሱ፥ ነው። ከርስት- ደም፥ አልጋ፥ ከማስመለስ፥ በላይ፥ ማሰብ፥ ይገባል።

1- ማንም አንደማይገዛው ማረጋግጥ
2-የተወሰደበትን መሬት ከአጁ አንዳይወጣ ማረግ
3- የአማራ መፈናቀልና ሞት አንዲቆም ማረግ ሌሎችም
4- በይ አንጂ የበይ ተመልካች አለመሆኑን ማሳየት እና ሌሎችም ናቸው::

Post Reply