ወደ ጥያቄዉ ሳልገባ በፊት ሶስት መሠረታዊ ግንዛቤዎቼን ላስቀምጥ።
ኣንደኛ በሶስት ቀላል መስፈርቶች አፋን ኦሮሞ በመባል የሚታወቀዉ ቋንቋ በአለም ላይ ከሚታወቁት ብዙ ቋንቋዎች ወይ ይበልጣል ወይ እኩል ነዉ።
ሁለተኛ ኢትዮጵያ ተብላ ለረጅም ግዜ የታወቀች ሃገር የብዙ የሰዉ ጎሳዎች ሽብርቅ ነች ብዬ ኣስባለሁ።
ሶስተኛ ከረጅም ታሪክ በላይ አደዋ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ይህን ሽብርቅ ኣንድ ወገን ወይም ወገነ ኣድርጓል ብዬ ኣስባለሁ።
ከሆነ ይህን ቀላል ጥያቄ ምን ይመልሳል?
ለበርካታ ዓመታት ይህቺን ታሪካዊ የሰዉ ጎሳዎች ሽብርቅ ተሻሽላ ትደግ እና ተናግታ ለኦሮሞ የምትሆን ኣዲስ ሃገር ትወለድ በሚል ክርክር ተሽመድምዳ እንደነበር ኣስታዉያለሁ። ብዙዎች ነበሩ ይህን መሽመድመድ ያስተዋሉት።
ኢትዮጵያ እያለሁ ነበር የመጫ እና ቱለማ መሪ የነበሩት ኮሎኔል አለሙ ቅጤሳ ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ ኣይገነጠልም ብሎ ቪኦኤ ላይ ሲናገሩ የሰማሁኝ።
መጫ እና ቱለማ እስከዛሬ ስሙን ያልቀየረ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ኣንጋፋ ድርጅት ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
በእኔ ግምት ኢትዮጵያን ኣሽመድምዷት ከነበረዉ ክርክር ተሻሽላ ትደግ የሚለዉ አስተሳሰብ ኣፈትልኮ ሲወጣ ነዉ ከመሽመድመድ የወጣችዉ። ለዚህ ደግሞ ዕዉቀት ከድንቁርና ተበጥሮ ነዉ።
ዛሬ ከርቀት ሳነብ የሰዉ ጎሳዎች ሽብርቋ ኢትዮጵያ ዉስጥ ኦሮሞ ስልጣን በዛበት እንጂ ኣነሰበት የሚል ያለ ኣይመስለኝም።
ቢሆንም ሽብርቋ ዉስጥ የጎሳዎቿ ማንነት ዉዥንብር ዉስጥ ተሽመድምዳ ያለች መሆኑን ነዉ የማነበዉ።
ሽብርቋ ከዚህም መሽመድመድ ወጥታ በርታ ማደግን የምትቀጥለዉ ማንነቷን በዕዉቀት ኣበጥራ ዕዉቀት ኣፈትልኮ ሲወጣ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ለዚህ ነዉ ኦሮሞ ማን ነዉ ብዬ የዕዉቀት ጥያቄን የምጠይቀዉ።
ልጅ ሆኜ መደበኛ ትምህርት ያልተማሩ ኣባቶች እና እናቶች የአከባቢዎቸቸዉን ጎሳዎች ኣበጥረዉ እንደምያዉቁ ኣዉቃለሁ። ገበሮዎች እና ቦረናዎች በሚባሉ ጎሳዎች የሚታወቁ ናቸዉ።
እ ኣ አ በ1991 ትግርኛ ተናጋሪ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ታጥቀዉ አከባቢዉ ሲደርሱ ሌላ ጎሳ አከባቢዉን ወረረ ብሎ ነዉ ብዙዎች ኣብረዉ የተነሱት።
ከዛ መነሳሳት በኋላ ነበር ኣጭር የትግል መንገድ ላይ ካየሁዋቸዉ ሰዎች ዉስጥ የተወሰኑትን ብዙ ግዜ የማስታዉሰዉ። በግለሰብ ደረጃ እኔን ከመነሳሳት ያረጋጋኝ እና ሰላማዊ ትግል ያስጀመረኝ የቻርተሩ መፈረም ነበር።
መንገድ ላይ ተገናኝተን የቻርተሩ መፈረም መንገዳችንን ከለያየዉ ዉስጥ ነጋሳ ኩምሳ የሚባል ሰዉን ኣስታዉሳለሁ። ከዛ በኋላ የት እንዳለ ኣላዉቅም።
ትግል ብሎ ሲጥር ሶስት ወራት ሳይሞሉ ሰዎች ሁለቴ ታዝበዉት እንደነበረ ኣስታዉሳለሁ።
የመጀመርያዉ ሰዎችን ሰብስቦ ስያስተምር በርካታዎች ማንነቱን እና ባህሪዉን ታዝበዉ እንደነበር ኣስታዉሳለሁ። በተለይ ኣብሮን የነበረ የምስራቅ ወለጋ ሰዉ ፌዝን ኣልረሳም።
ከዛን ቀን በኋላ ተመልሶ ስያስተምር ማየቴን ኣላስታዉስም።
ሁለተኛዉ ሰዎች በጣም የታዘቡት የማይገባዉ ስጦታ ተሰጠዉ ብለዉ ነዉ። የሰጪዉንም ማመዛዘን ችሎታ ጭምር ነበር የታዘቡት።
እኔ አላማ ብሎ ለሚታገል ክብር ኣለኝ። ስህተትን ኣስተዉሎ ካረመ ይመሰገናል።
ይህን ታሪክ እዚህ የማነሳዉ ለኣንድ ጥያቄ ብቻ ነዉ።
ነጋሳ ኩምሳ ኦሮሞ ነዉ? ነጋሳ ኩምሳ ኦሮሞ ካልሆነ ኦሮሞ ማን ነዉ?
ከቦረና እና አኙዋ የተወለደ ኢትዮጵያዊ ከሆነ የሰዉ ጎሳዎች ሽብርቋ ኢትዮጵያ አካል የማያደርገዉ ምን ምክንያት ኣለ?
ፕሮፌሰር መረራ ጉድናን ኢትዮጵያ እያለሁ ነዉ ጽሑፉን ያነበብኩኝ። ተገቢ ያልሆኑ ቃላቱ ከብደዉኝ ስለኢትዮጵያ ፖለትካ ትንተናዉን ኣከበርኩኝ።
ኢትዮጵያ እያለሁ በዛ ጽሑፉ ምክንያት መወገድ ኣለበት የሚል መንገድ ላይ ኣጋጥሞኝ በጣም ነቅፌዉ ፊቱን ኣዙሮ ከአጠገቤ ሄደ። ሰዉየዉ የፖለትካ ዶክተሩ ጎሳ ነኝ ባይ ነበር።
እዚህ አሜሪካ ዉስጥ ብያንስ አምስት ግዜ የፖለትካ አመለካከቱን እና ማንነቱን የነቀፉ ኣጋጥመዉኝ ነቅፌኣቸዋለሁ።
የሰፈሩ ሰዉ ፕሮፌሰሩ በማንነቱ ኦሮሞን እወክላለሁ ማለቱ ተገቢ ኣይዴለም ብሎ በንቀት ሲናገር ሰምቻለሁ፣ ኣይቻለሁ።
የአከባቢዉ ሰዎች ማንነቱን ጥያቄ ዉስጥ ስያስገቡ ሰምቼ ነቅፌኣለሁ።
ኦቦ ቡልቻ ደመክሳ የፖለትካ ምሁሩ ከኣቋቋሙት ጋር ተመሳሳይ የሆነ አዲስ የፖለትካ ድርጅት ስያቋቋም እንተርኔት ዉስጥ የተዋወቁኝ የከበርኳቸዉ የአከባቢዉ ሰዉ ስልክ ደዉለዉልኝ ሲጋብዙኝ የነበረዉ ዉስጥ ገብታችሁ ለምን ኣታጠናክሩትም ብዬ ጠየኳቸዉ።
የፖለትካ ምሁሩን ሳይሆን ማንነቱን ሲዘልፉ ታዝቤ በትህትና ስልካቸዉን ኣቆምኩኝ።
የፖለትካ ሳይንስ ተምሮ ለኦሮሞ እታገላለሁ ብሎ ዓመታትን ያሳለፈ ኢትዮጵያዊ የሰፈሩ እና የአከባቢዉ ሰዎች ማንነቱን የሚጠይቁ ከሆነ ኦሮሞ ማነዉ?
ከዓመታት በፊት ሰዉ ቤት ተጋብዤ ሰዎች ስለታሪክ ስያወሩ ሰማሁ። በልጅነት ከሰማሁኝ ታሪክ ጋር ያልተጣጣመ መሆኑን ስገነዘብ እያመነታሁ በጣም ቀላል ጥያቄ ጠየኩኝ። ያመነታሁኝ ልታዘቡኝ የሚችሉ እናትም ተጋብዘዉ አጠገባችን የነበሩ ስለሆነ ክርክር ተጀምሮ ይከራከራል እንዳይሉኝ ነበር።
ጥያቄዬ በታሪክ አምስት መቶ ዓመታትን ወደ ኋላ ተመልሶ ስለማወቅ ነበር።
ጥያቄዬ ከሰሙት ዉስጥ ኣንዱ ወድያዉ ፊቱን ከእኔ ኣዞረ። የተማረ ነዉ። እስከመጨረሻ። ጥያቄዬ እንዳልገባዉ ኣስተዉዬ ኣሳዘነኝ።
ሌላዉ ጥያቄዬ ገብቶት ይወያዩ ወደነበሩት ዞሮ ልብ በሉ አይነት ነገር ሲናገር ሰማሁ። መደበኛ ትምህርት መከታተሉን ኣላዉቅም።
ከዛ በኋላ ዉይይቱ መቀጠሉን ኣላስታዉስም።
ጥያቄዬን ሰምቶ ከእኔ ፊቱን ያዞረዉ ከእኔ ርቆ ከዓመታት በኋላ በድንገት ባዕድ ሃገር ኣረፈ የሚል መርዶ ሰምቼ ደነገጥኩኝ። ኣዘንኩኝ። በደመነፍስ ከእኔ ባይርቅ ይተርፍ ነበር ኣልኩኝ።
እስከዛሬ በምን ምክንያት በድንገት እንደኣረፈ ኣላዉቅም። ልብ በሉ ብሎ የነበረዉን ሰዉ ከዛ መርዶ በኋላ ላነጋግረዉ ሞክሬ እስከዛሬ ድረስ ኣልተሳካልኝም።
ከእኔ ከራቀበት ግዜ ጀምሮ በድንገት እስከ ኣረፈበት ቀን ምን ዉስጥ እንዳለፈ ኣላዉቅም።
ከዓመታት በፊት የጠየኩኝን ጥያቄ የሚከተለዉ ቪድዮ መልሶታል።
ይህ የሃገር ሰዉ፣ ከቤተሰቡ ለብቻዉ ተምሮ የወጣ፣ ሁለት ታዳጊ ልጆቹን ባዕድ ሃገር ትቶ ኣረፈ።
መቃብሩ ላይ የኣረፈዉ ጎሳ ወገን ነኝ የሚል ወንድ ልጁ ፊት ጥቁር አፈር ሲወረዉር ኣይቼ በዉስጤ ባህል ዬለሽ ጭንጋፍ ኣልኩት።
በኦሮሞ ስም እታገላለሁ ብሎ በባዕድ ሃገር የወገኑ ጎሳ ነኝ በሚል ጭንጋፍ ወንድ ልጁ ፊት መቃብሩ ላይ ጥቁር አፈር የሚወረዉር ከሆነ ኦሮሞ ማን ነዉ?
ያለፈበትን የፖለትካ መንገድ ባላዉቅም በድንገት ክብሩን ጠብቆ የሄደዉ ከቦረና ተነስቶ ወልሶ የደረሰዉ ሊበን አከባቢ ተወልዶ ያደገ ቢሆንም በየት በኩል ከቦረናዉ ሰዉ ሊበን ጋር እንደሚገናኝ እስከዛሬ ኣላዉቅም።
ከኣሁን በፊት እዚሁ ፎረም ላይ ቦረና ነዉ የኦሮሞ አባት ወይስ ኦሮሞ ነዉ የቦረና አባት ብዬ ጠይቄ ነበር። ኣንድ ያገኘሁኝ መልስ ቦረና ነዉ የኦሮሞ አባት የሚል ነበር።
ታድያ ቦረና የኦሮሞ አባት ከሆነ በልጅ ስም ከመታወቅ ለምን በአባት ስም ኣይታወቅም፧
ኦሮሞ ነኝ ብሎ የሚዘፍነዉ ታደለ ሮባ ከቦረናዉ ሰዉ ሊበን ጎሳ የተወለደ ነዉ?
ቦረና የኦሮሞ አባት ከሆነ፣ ታደለ ሮባ በከፊልም ሆነ በሙሉ ከቦረና ያልተወለደ ከሆን ኦሮሞ ነኝ ብሎ መዝፈን ምን ትርጉም ኣለዉ?
ይህ ሁሉ ጥያቄ መሠረታዊ መልስ ተገኝቶ ኢትዮጵያ በማነንት ጥያቄ ተሽመድምዳ ካለችበት እንድትወጣ ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ የማንነት ጥያቄ ትግል በክርስትና ትምህርት ምክንያት የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመታት ጀምሮ እያዘገመ መምጣቱን ኢትዮጵያን በሰፊዉ ያጠናዉፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ኣስቀምጠዋል።
ከኢትዮጵያ እስከ ግብጽ፣ ሴኔጋል፣ እና ግሪክ በሰፊዉ ኣጥንቷል የተባለዉ ኢትዮጵያዊዉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ሕዝብ በኣብዛኛዉ ኣንድ መሠረት እንዳላቸዉ ለታሪክ ኣስቀምጧል።
ካልዘነጋሁ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢሳቅም ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዳላቸዉ ሰምቻለሁ።
ለዚህ ብዙ ኣመላካቸች ኣሉ። ኣንድ ጎሳ ቆንቆ ሲል ሌላ ጎሳ ቋንቋ ሲል ከጥንት ጀምሮ ባይተዋወቁ ነዉ? ኣንድ ጎሳ አፍ ሲል ሌላ ጎሳ አፋን የሚለዉ ከጥንት ጀምሮ ባይተዋወቁ ነዉ? ከጥንት ጀምሮ የሚተዋወቁ ጎሳዎች ቢሆኑ ኣይዴለም ኼረ እግዝኣብኼር ዉስጥ የተገኘዉ?
ከጥንት ጀምሮ ቢተዋወቁ ከሆነ የሰዉ ጎሳዎች ሽብርቋ ኢትዮጵያ መብራቷ ቀርቶ በጎሳዎች የማንነት ትግል ለምን ትሽመደመዳለች?