Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

እውነት ነው እንዴ?

Post by Assegid S. » 29 Jan 2024, 09:19

ቡና እና ወሬ እንደወረደ የሚወዱት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ ኣቦይ ስብሓት ነጋ ... የፕሪቶሪያን ውል አስመልክተው ሲናገሩ ... ስምምነቱ ተደራዳሪዎቹ ገና ከመሰብሰቢያው ኣዳራሽ ሳይወጡ፣ ከተፈራረሙበት ጠረፔዛ ላይ ሳይነሱ ሙሉ በሙሉ ተተግብሯል እያሉ ነው። በእርግጥ ትግርኛውን ባልሰማውም ... እንደ ኣማርኛ ትርጉሙ ዘገባ መሰረት ... ኣቦይ ስብሓት "ስምምነቱ ጊዜ መግዣ እንጂ ምንም ውል የሌለው ባዶ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። ታዲያ ለምንድነው እነዚህ ሰዎች በነጋ በጠባ "የፕሪቶሪያ ውል ይተግበር! ራያ ይመለስ! ወልቃይት እንደ ቀድሞ በህወሃት ታጋይ ይታረስ!" እያሉ የሚያደነቁሩን? ስምምነቱ ዜሮ ነው ከተባለ ... በቃ በዛው ደቂቃ ተተግብሯል ጩኸት አያስፈልግም ማለት ነው።