Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42545
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ዛሬ በጉራጌ ምድር የእናቶች ቀን ነው! አሽትሮት፣ አስተረ፣ ብስቆት ይባላል! መልካም የደስታ ክብረ ባህል ለናቶቻችን !!!

Post by Horus » 27 Jan 2024, 14:52

ጉራጌ ለእናቶች ብቻ ሳይሆን ለመላ ሴቶቹ እጅግ ከፍተኛ አክብሮትና ዋጋ የሚሰጥ ሕዝብ ነው! ይህ እሴት በዚህ በእኛ ዘመን በጣም ጠንክሮ በመትግበር ላይ ነው!!

የቃል ትርጉም፤
ዉሳቻ = የሴቶች የእንሰት መፋቂያ ደቦ ። የእያንዳንዱ ቤት እንሰት መፋቅ በዉሳቻ (የሴቶች ደቦ) ነው የሚከወነው ። የዚያን ቀን ባለዉሳቻዋ ሴት ሙሉ ድግስ ደግሳ ሴቶች እየበሉ እየጠጡ እየተዘፈነ ነው ሲሰሩ የሚውሉት ። ልክ እንደ ማህበር ዉሳቻ ለባለተራው ይዞራል ። በጉራጌ አብዛኛ ስራ በማህበር ነው የሚሰራው ። ምሳሌ
ከብት ማገጃ የልጆች ማህበር ዎጀ ይባላል (ከብት በተራ ነው የምናግደው)
እንሰት መቆፈሪያ ማህበር ድድቅ ይባላል
እርሻ ማረሻ ያው ደቦ ነው
እንሰት መፋቂያ ዉሳቻ ይባላል
እያለ ይቀጥላል!!!