ጉራጌ "አሳምነው...አሳምነው ፅጌ" እያለ የኦሮሙማውን ደም ሲያፈላ ዋለ! ቂቂቂ
Posted: 21 Jan 2024, 09:35
በመላው ኢትዮጵያ ፋኖ ሲከበር እና ሲወደስ ዋለ። ትርክት ተገፍትራ ገደል ገባች። ኢትዮጵያ በልጆቿ ደም ታሪክ ሰራች፣ ዳግም ፀናች።
አሳምነው....አሳምነው ፅጌ!!
አሳምነው....አሳምነው ፅጌ!!
የእርስዎ ስህተት የእኛም ሀዘን ከባድ ነው። ለእይታ ካልሆነ በስተቀር፥ የዓይን እንባ አይደለም የባህርም ውሃ ይህንን ህመም አያስውጠንም፤ ዘላለም አንቆ ከሚቆረቁረን ጉሮሮኣችን ላይ ጥቂት አይገፋውም። ደግሞም፦ ቆሞ የማይሟገቶትን – ነፍሱ ከስጋው የተለየችን ሰው በከንቱ አይክሰሱ። መቼም ቢሆን አይረቱትምና! ምክያቱም፦ ለፍርዱ ጠበቃ የሚያቆመው ከነፍሱ ማደሪያ ከሰማይ እንጂ ከስጋው መቀበሪያ ከምድር ስለማይሆን።
የሰው ልጅ ታሪክን የሚፅፍበት እርሳስ እንጂ የሚሰርዝበት ላጲስ አልተሰጠውም። ከንቱ መድከም ነው። ይመኑኝ ሀቅ ነው! የሰው ልጆች ታሪክ የሚሰራ ጥበብ እንጂ፥ ታሪክ የሚፍቅ አቅም ከአምላክ አልታደልንም። መቼም ቢሆን የልቦለድ ቃላት ጐርፍ በእውነት ካፊያ ላይ ሰልጥኖ የሀቅን ዘር ጠርጎ ወስዶ ከመብቀል ከልክሎ አያውቅም። የእርሶ “fascist” ለእኔና ለብዙዎች የነፃነት fashion እንደነበሩ የሚያውቁበት ጊዜ ሩቅ አይደለም!