Page 1 of 1

ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 01:40
by Horus
ጥምቀት ቅዳሜ ነው! ፈረንጅ ኤፒፋኒ ሲሉት ግእዝ ቦ ፈነወ ይለዋል! እኛ ደሞ ኤቦ ፈና እንለዋለን!

ጥምቀት ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለም የተገለጸበት ቀን ክብረ ባህል ነው ። በተለምዶ የእንግሊዝኛው ቃል ግሪክኛ ነው ተብሎ ተወስዷል ።

ነገር ሁለቱም ቃላት ኤፒ (ቦ/ኤቦ) እና ፋኒ ( ፈና/ፋና) የግእዝ ቃላት ናቸው !

ቦ መሆን፣ ሆነ ማለት ነው ። ስረ ቃሉ ጥንታዊ የግብጽ ቀምጥ/ኮፕት ቃል ነው ።

ባህ፣ ፋህ ፣ ፋህና ፣ ፈነው በራ፣ ተገለጸ፣ ታየ ማለት ሲሆን ዛሬ ፋኖ ፣ ፋኖስ ወዘተ የምንለው ቃል ነው ።

ሌላው ቀርቶ 'ፈያ' (ውብ፣ ያማረ ) የሚሉት ቃል ፈና ከሚለው እንደ ብርሃን የበራ የሚለው ቃል ነው ! በዚሁ የክስታኔኛ ቋንቋ 'ፈፋ' እጹብ ድንቅ፣ ታይቶ የማይታውቅ፣ አስገራሚ ማለት ነው ።

ይህ እጹብ ድንቅ ክብረ ባህላችን መንገዱ ሁሉ የጠፋው ኦርሙማ ባለግዜ እጁን ባያስገባበት ይመከራል !

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 02:07
by Horus

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 02:13
by Horus

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 02:36
by Horus
ይህን ስሙ! AMOR FATI :!: :!: :!:

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 08:37
by Assegid S.
Horus wrote:
15 Jan 2024, 01:40

ባህ፣ ፋህ ፣ ፋህና ፣ ፈነው በራ፣ ተገለጸ፣ ታየ ማለት ሲሆን ዛሬ ፋኖ ፣ ፋኖስ ወዘተ የምንለው ቃል ነው ።

ሰላም ሆሩስ - የቃላቶችን ውርስና ርቢ አስመልክቶ ለምትሰጠን አስተምሮታዊ ገለፃ ሁላችንም ባለውለታዎች ነን ብዬ አስባለሁ ... ስለዚህም እናመሰግናለን። እዚህ ላይ ተያይዞ ጠባ የሚለውስ ቃል ታየ ወይንም ተገለጠ እንደማለት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል? ባህ ከሚለው ቃል ጋር ተዛምዶ ማለቴ ነው? በተለምዶስ መስከረም ሲ-ጠባ የሚለው አገላለፅ ትክክል ነው? ወይንስ መስከረም ሲ-ባህ ነው ትክክለኛው አገላለፅ?

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 09:53
by Horus
Assegid S. wrote:
15 Jan 2024, 08:37
Horus wrote:
15 Jan 2024, 01:40

ባህ፣ ፋህ ፣ ፋህና ፣ ፈነው በራ፣ ተገለጸ፣ ታየ ማለት ሲሆን ዛሬ ፋኖ ፣ ፋኖስ ወዘተ የምንለው ቃል ነው ።

ሰላም ሆሩስ - የቃላቶችን ውርስና ርቢ አስመልክቶ ለምትሰጠን አስተምሮታዊ ገለፃ ሁላችንም ባለውለታዎች ነን ብዬ አስባለሁ ... ስለዚህም እናመሰግናለን። እዚህ ላይ ተያይዞ ጠባ የሚለውስ ቃል ታየ ወይንም ተገለጠ እንደማለት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል? ባህ ከሚለው ቃል ጋር ተዛምዶ ማለቴ ነው? በተለምዶስ መስከረም ሲ-ጠባ የሚለው አገላለፅ ትክክል ነው? ወይንስ መስከረም ሲ-ባህ ነው ትክክለኛው አገላለፅ?
Assegid S.,

እኔም አመሰግናለሁ! ግሩም ምርምርና ጥያቄ ነው ።

(1) ትክክል ነህ፤ 'ጠባ' መጣ፣ ተከሰተ፣ ታየ፣ ሆነ ማለት ነው ። ከላይ እንደ ጠቀስኩት በግእዝ 'ቦ' ሆነ ማለት ነው ። ለምሳሌ 'ጽባህ' (ኮከበ ጽባህ እንደምንለው)፣ ጥዋት (ንጋት እንደምንለው) ማለት ነው ።

ታዲያ ለምንድነው 'መጣ' ፣ 'ጠባ' ፣ 'ወጣ'፣ 'ጠዋት' እያሉ ቃላቶቹ የተለያይዩት? ብለው ስትጠይቅ ... በሁለት ምክኛቶች ነው ። አንዱ የቃሉ ንባብ አቅጣጫ፤ ሌላው የፊደሎች ድምጽ ልወጥ (shift) ማድረግ ነው ። ስለዚህ ...

(2) በኢትዮጵያ የሴም ቋንቋዎች ውስጥ አንድ ብዙ የማይታወቅ የቃላት አነባበብ አቅጣጫ አመሰራረት አለ ። እሱም አንድ ቃል ተመሳሳይ ትርጉም ይዞ ከግራ ወደ ቀኝ ይነበባል፤ ከቀኝ ወደ ግራ ይነበባል ። ይህ የመጣው ብዙ የሴም ቋንቋዎች አረብኛ ጭምር ከቀኝ ወደ ግራ ስለሚነበብ ነው ። የጥንት ግብጽ እንዲያውም ከላይ ወደ ታች ነበር የሚጻፈውና ሚነበበው ፣

ለዚህ ነው ለምሳሌ 'ወጣ' እና 'ጠባ' አንድ የሆኑት ።

(3) ሌላው አንድ ትልቅ የሁሉም ቋንቋዎች ባህሪ አለ፤ እሱም የፊደላት ድምጽ መለዋወጥ ነው ። ለምሳሌ 'በ' = 'ወ' = 'መ' = 'የ' ። 'ከ' = 'ቀ' = 'ሸ' = 'ሰ' 'ሀ' እያለ ሺፍት ያደርጋል ። የዚህ ምክንያቱ የተለያዩ ሕዝቦች (ጎሳዎች) የተለያየ የጉሮሮ ተፈጥሮ ስላላቸው አንዱ ጎሳ የሚችለውን ድምጽ ሌላው አይችለውም ።

ስለሆነም 'ባህ 'bha' ወደ 'pha' ም 'በ' = 'ፈ '፣ 'ረ' = 'ለ' ... ወዘተ ። ስለዚህ ነው 'በ' 'ወ' የሚሆነው ፤ 'ጠ' = 'ጸ' = 'ሰ' የሚሆነው ።

ስለ ቴክኒካል ዝብዝቡ ይቅርታ! ሰላምዊ የጥምቀት ክብረ ባህል ይሁንልን!

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 11:31
by Assegid S.
Horus wrote:
15 Jan 2024, 09:53

[/color][/b]
ወንድም Horus - ይቅርታ ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባህና እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ለጥያቄዬ መልስ ብቻ ሳይሆን ተጨማሪም ዕውቀት አግኝቻለሁ። ድሮ ልጅ እያለሁ በኣካባቢው ሳልፍ ስሙ ግራ ያጋባኝ የነበረው የኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት ስያሜም በእርግጠኝነት የገባኝ የኣንተን thread ሳነብ ነበር። ከዛ በፊት ግን ትግርኛ ስያሜ ይመስለኝ ነበር 8) ጽባህ በትግርኛ ነገ ነው የሚለውን ቃል ስለማውቅ። የነገ ኮኮብ እንደማለት .... የነገ ሰው እንደምንለው 8)

አንዳንዴ ባለማወቅ ዘመነኛ ወይንም የኣራዳ ቋንቋ (በተለምዶ street slang) ነው ብለን የምናስበው ... በደንብ ሲፈተሽ ቀድሞ የነበረና (ያረጀ?) ልማድም ሊሆን እንደሚችል ተገንዝቤያለሁ። ልክ መጣ የሚለውን ቃል ጣመ በሚለው ተተክቶ የኣራዳ ልጆች መግባቢያ ነው ብለን ስናስብ እንደነበረው ማለት ነው። ስለሁሉም አስተምሮትህ በድጋሚ በጣም እያመሰገንኩ ለኣንተም መልካም የጥምቀት ክብረ በዓል እንዲሆንልህ እመኛለሁ!

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 14:30
by Horus
Assegid S. wrote:
15 Jan 2024, 11:31

It's my pleasure. 'ታየ' ልክ እንዳልከው የጠባ፣ የጸባ ቤተሰብ ነው ። 'ተገለጸ' የሚለው ቃል ግን ግንዱ 'ቀረጸ'፣ 'ጸነሰ'፣ 'ቀረሰ'፣ (ቅርጸ ሰጠ/formed ሆነ) የሚለው ነው ። ጥንስስ ፣ ጀነሲስ የምንለው ማለት ነው ።

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 15 Jan 2024, 17:27
by Assegid S.
Horus wrote:
15 Jan 2024, 14:30
Assegid S.,

It's my pleasure. 'ታየ' ክል እንዳልከው የጠባ፣ የጸባ ቤተሰብ ነው ። 'ተገለጸ' የሚለው ቃል ግን ግንዱ 'ቀረጸ'፣ 'ጸነሰ'፣ 'ቀረሰ'፣ (ቅርጸ ሰጠ/formed ሆነ) የሚለው ነው ። ጥንስስ ፣ ጀነሲስ የምንለው ማለት ነው ።
በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ Horus 8)

Re: ጥምቀት ምን ማለት ነው?

Posted: 16 Jan 2024, 03:01
by Horus
ፈጣሪ ብርሃን ነው! ደሞ በጥምቀት ይገለጻል !