አበረ ፤ አንድ ሁለት ነገር ላጫውትህ
Posted: 11 Jan 2024, 01:46
ከታች በምታየው ታሪካዊ ቪዲዮ ውስጥ ጊዮርጊስ አራዳ ፍርድ ቤት በር ላይ ሁለት ሁለት ሰዎች እጃቸው አብሮ በሰንሰለት (ከፍ) ታስረው ታያለህ ። ከፖሊስ ጋር የታሰሩት ብዙዎቹ በወንጀል ክስ ላይ ያሉ ናቸው ።
በፍትሃ ብሄር ጉዳይ የተካሰሱ እና ከሳሹ ከተፈረደለት ተከሳሹ እዳውን (መቀጮውን) እስከ ሚከፍል ድረስ ከከሳሹ ጋር እጅና እጅ ይታሰር (ይታበት) ነበር ። አበተ አሰረ ማለት ነው። ያ ተከሳሽ የከሳሹ እስረኛ ወይም እብት (እስር) ነበር ። ዛሬ መብት የሚባለው ትልቁ የሕግ ቃል 'የከሻሽ እብት፣ የከሳሽ መብት ' ይባል የነበረው ነው ።
ደሞ ተከሻሹ ከተከሳሹ ተላቅቆ የሚከፍለውን እዳ ገንዘብም ሆነ ከብት እስከ ሚያፈላልግ ሌላ ዘመድ ወይም ጓደኛ ተውሶ ያመጣና በሱ ምትክ ይታሰርለት ነበር ። ይህን የተውሶ እብት ወይም መታበት ነው ዛሬ ዋስ (መዋስ) የምንለው የሕግ ቃል ።
ቋንቋ የአንድን ሕዝብ ታሪካና ካልቸር ደብቆ የያዘ ምስጢረኛ ነው ።
መብትና ዋስ የመጡት በዚህ መልክ ነው !!