Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42555
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 11 Jan 2024, 01:46
ከታች በምታየው ታሪካዊ ቪዲዮ ውስጥ ጊዮርጊስ አራዳ ፍርድ ቤት በር ላይ ሁለት ሁለት ሰዎች እጃቸው አብሮ በሰንሰለት (ከፍ) ታስረው ታያለህ ። ከፖሊስ ጋር የታሰሩት ብዙዎቹ በወንጀል ክስ ላይ ያሉ ናቸው ።
በፍትሃ ብሄር ጉዳይ የተካሰሱ እና ከሳሹ ከተፈረደለት ተከሳሹ እዳውን (መቀጮውን) እስከ ሚከፍል ድረስ ከከሳሹ ጋር እጅና እጅ ይታሰር (ይታበት) ነበር ። አበተ አሰረ ማለት ነው። ያ ተከሳሽ የከሳሹ እስረኛ ወይም እብት (እስር) ነበር ። ዛሬ መብት የሚባለው ትልቁ የሕግ ቃል 'የከሻሽ እብት፣ የከሳሽ መብት ' ይባል የነበረው ነው ።
ደሞ ተከሻሹ ከተከሳሹ ተላቅቆ የሚከፍለውን እዳ ገንዘብም ሆነ ከብት እስከ ሚያፈላልግ ሌላ ዘመድ ወይም ጓደኛ ተውሶ ያመጣና በሱ ምትክ ይታሰርለት ነበር ። ይህን የተውሶ እብት ወይም መታበት ነው ዛሬ ዋስ (መዋስ) የምንለው የሕግ ቃል ።
ቋንቋ የአንድን ሕዝብ ታሪካና ካልቸር ደብቆ የያዘ ምስጢረኛ ነው ።
መብትና ዋስ የመጡት በዚህ መልክ ነው !!
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15350
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 11 Jan 2024, 11:11
ሆረስ፤
የደጋጎቹን እና የየዋሃኑን ዘመን ወደ ኋላ መለስ ብለን እንድንቃኝ አደረግኸን። የሚደንቅ ነው። አምላኩን ምስክር አድርጎ በፈሪሃ እግዜር የሚኖር ትውልድ። ያን ዘመን ህግ ጥርስ ነበረው ማለት ይቻላል። ተበዳይ ሳይካስ ቤቱ አይገባም ነበር። ህግ የተሰራው ቀደም ብሎ ነበር፤ ህግም በሚገባ የሚተገበረው በዚያን ትውልድ ነበር።
እንደ እኔ ህግ ጥርሱን አውጥቶ ህግ አልባ ያደረገው ዘመናዊ ትምህርት ተማርን ባዮች ናቸው። ህግን ለማጭበርበሪያ፤ለመስረቂያ፤ ለማወናበጃ ያደረጉት። ህጉ የሚሰራው ለመንግስታዊ ዱርየነት እና ዜጎችን ባርያ ለማድረግ። ዛሬ በአንድ ተራ ኦሮሙማ ከቤቱ ጠዋት ታፍኖ ከሰዐት 7 ሚልዮን ብር ይጠየቅበታል፤ ውሃ ጠማኝ የውሃ ቧንቧ ይግባልን ያለ ህዝብ ጥይት ይጠጣል፤ ወይም ማዳበሪያ ላለ ገበሬ ከቤትህ የደበቅከውን ስንዴ ገበያ ላይ ካልሸጥክ አይሰጥህም ወዘተ።
የህግ አምላክ የሚባልበት ዘመን አልቆ ህግ-ዐልባ ጊዜ ደረሰ። የአፈር መስኮት ቢኖረው ተቆራኝተው የታሰሩት ከሳሽ እና ተከሳሽ ይህን የኦሮሙማ-ወያኔ ዘመን ማየት በቻሉ ነበር።
Horus wrote: ↑11 Jan 2024, 01:46