Page 1 of 1

የእንቆቅልሽ ጫወታ፥ የኣንድ ግዜ ጩሀት እንቆቅልሽ

Posted: 08 Jan 2024, 01:05
by Naga Tuma
በልጅነት በርካታ ባህላዊ ጫወታዎችን ኣስታዉሳለሁ። እንቆቅልሽ ኣንዱ ነዉ። ጅሚ ጅምዮ ሌላ ነበር። እንዴት እና መቼ እንደተጀመሩ ባላዉቅም ለልጅ ኣዕምሮ ጥሩ ጫወታዎች ናቸዉ።

ድሮ ይህ ቅኔ፣ ያ ቅኔ እንል ነበር። ኣሁን መቀኘትም በደንብ እየተለመደ ነዉ።

የዛሬ ሃያ ዓመታት ገደማ ኣንድ ሰዉ ተነስቶ ጮሀ። ኣሁን ታሪክ ሆኖ ለእንቆቅልሽ ጫወታ የሚበቃ ይመስለኛል።

እስቲ ለሚከተለዉ የጩሀቱ እንቆቅልሽ ትክክለኛዉን መልስ ምረጡ።

አረት ሰዎች ሰማን ኣሉ።

ኣንደኛዉ ወይም ኣንደኛዋ ፍጹም ኣልረሳህም ኣለ ወይም ኣለች። ጾታ ኣልታወቀም።

ሁለተኛዉ ሰዉ የሚጮሀዉን ሰዉ በመሃል ኣቋረጠዉ እና ኣጭር ጥያቄ ጠየቀዉ። በማህበረሰብህ ባህል እባብ እንዴት ነዉ የሚታየዉ ብሎ።

ጩሀቱን በመሃል ያቆመዉ ቶሎ ኣጭር መልስ መለሰለት። ኡማ ዋቃት። ቱቀን መሌ ነመ ህን ቱቁ ይባላል ብሎ። የዋቃ ፍጡር ነዉ። ካልነኩት ኣይነካም ይባላል እንደማለት ነዉ።

በጎ አባባል ነዉ ብሎ ጩሀቱን ኣስቀጠለዉ።

ሶስተኛዉም ጩሀቱን በመሃል ኣስቁሞት ጩሀትህን ሰምቻለሁ፣ ቀጥልበት፣ ተመልሼ እመጣለሁ ብሎ ሄደ። እሺ ኣለዉ። በዛዉ ቀረ።

አረተኛዉ ያበግናቸዋል ኣለ።

ማናዉ የጩሀቱን እንቆቅልሽ የፈታዉ ወይም የፈታችዉ?

Re: የእንቆቅልሽ ጫወታ፥ የኣንድ ግዜ ጩሀት እንቆቅልሽ

Posted: 09 Jan 2024, 01:18
by Naga Tuma
ብዙዎች እንደምያዉቁት እዚህ ኣሜሪካ ትምህርት ቤት ከተለያዩ ሃገሮች የመጡ ተማሪዎች ያጋጥማሉ።

እነዚህ ተማሪዎች ሲገናኙ ስለ ሃገሮቻቸዉ ይጠያየቃሉ። ያወራሉ።

የሁለት ተማሪዎችን አስተያየት እና ጥያቄ ብዙ ግዜ ኣስታዉሳለሁ።

ኣንድ የኣሜሪካ ተማሪ፣ በእድሜ የገፋ፣ ያለኝን ሳስታዉስ ሁሌ ይገርመኛል። ከኢትዮጵያ ነኝ ስል ያልከሳ ሰዉ ባለመሆኔ ተገርሞ ነበር ኣለ። ወፍራም የሚባል ቁመና ኣልነበረኝም። ቢሆንም እንደዛ ሲል አንገት ኣስደፋኝ።

ሌላ ከደቡብ አሜሪካ የመጣች ተማሪ ሃገርህ ለምን ኋላ ቀር ሆነች ብላ ጠየቀችኝ። ሌሎች ተማሪዎች ፊት።

ባህር ኣቋርጦ የመጣዉን የጣልያን ጦር እና አደዋን ቶሎ ኣስታዉሼ ከሩቅ የመጣን ጠላት ስናይ ኣብረን እንዋጋቸዋለን፣ ጠላት ከርቀት ካላየን እርስ በእርስ እንጣላለን፣ ብንተባበር እናድጋለን ብዬ መለስኩኝ። እንደ ቀልድ። ኣሳቃቸዉ። እኔም ፈገግ ኣልኩኝ።

በመሃል የሚሰማ። በመሃል የተሰማ። በመሃል ያልተሰማ።

ሃገር የምትቆመዉ በትግል ነዉ።
ሃገር የምትቆየዉ በትግል ነዉ።
ሃገር ቀጥላ የምትዘልቀዉ በትግል ነዉ።

Re: የእንቆቅልሽ ጫወታ፥ የኣንድ ግዜ ጩሀት እንቆቅልሽ

Posted: 12 Jan 2024, 01:25
by Naga Tuma
በስትድ ያለዉን ትክክል ነህ ማለት የምትችለዉ ሆረስ፣

ሰምቼሃለዉ፣ እመለሳለሁ ብሎ በዛዉ የቀረዉ ለምን ሰምቼሃለሁ እንዳለ፣ ለምን እመለሳለሁ እንዳለ፣ ለምን በዛዉ እንደቀረ እሱ ነዉ የምያዉቀዉ።

ኣንተ መገመት ትችላለህ?