Page 1 of 1

እላ ፊ እላሜ

Posted: 05 Jan 2024, 19:12
by Naga Tuma
አፋን ኦሮሞ ዉስጥ ጥልቅ የሆኑ አስተሳሰቦችን ከምያንጸባርቁት ዉስጥ እላ ፊ እላሜ ኣንዱ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

እላ ማለት እይ ወይም ተመልከት ማለት ነዉ፣ በኣድናቆት ጭምር።

እላሜ ማለት እስቲ ስማ ወይም እስቲ እይ እንደማለት ነዉ። ከግሰጻ ጋር። ይታረም እንደማለት ነዉ።

ከዚህ የበለጠ ወይም የጠለቀ ማብራርያ ይኖረዉ ይሆናል። እኔ የገባኝን ያህል ነዉ የሞከርኩኝ። የምሞክረዉ።

በእንግልዘኛ እላ Look! ማለት ይሆናል። እላሜ Look here እንደማለት ይሆናል።

ለዚህ ጥልቅ አስተሳሰብ ግልጽ ምሳሌ ይሆናል ብዬ የማስብ የሽግግር ግዜ ኦቦ ሌንጮ ለታ ሲናገር በዜና የሰማሁኝ ነዉ።

ቃል በቃል ባይሆንም ኣንድ ቀን የሰማሁትን ንግግሩን በደንብ ኣስታዉሳለሁ።

መማር እንፈልጋለን። ከዚህ የተማርነዉ ምንም የለም ነበር ያለዉ።

የተናገረዉ ከማስታዉሰዉ ከተለየ ስህተቱ የእኔ ማስታወስ ይሆናል።

መማር እንፈልጋለን ማለቱ በኣድናቆት እላ ያምያስብል ነዉ። ያስባለኝ ነዉ። መማር እንፈልጋለን የሚል ባለስልጣን የተለመደ ኣልነበረም። ኣላስታዉስም ነበር። እናስተምራችሁ ባይ ባለስልጣን ነበር የስልጣን ባህሉ።

መማር እንፈልጋለን ማለቱን ሰምተህ እላ ብለህ ኣጣጥመህ ሳታበቃ በፍጥነት ከዚህ የተማርነዉ ምንም የለም ማለቱን ስትሳማ በቅጽበት አረ እባክህ የምያስብል ነበር። ያስባለኝ ነዉ።

በእላ ፊ እላሜ መማር እንፈልጋለን ያልከዉ እላ ያስብላል። ከዚህ የተማርነዉ ምንም የለም ያልከዉ እላሜ ያስብላል። ለምሳሌ ከዚህ ምንም የተማርነዉ ዬለም ከማለት ከእኛም እንድትማሩ እንመክራለን ብትል ኖሮ ይሻል ነበር ማለት ነዉ።

ሀሳብ የሰዉን ኣዕምሮን በቀላሉ ይረታል። በቀላሉም ግትር ያደርገዋል።

ሁሉም ሰዉ በተለያየ ደረጃ ኢጎ የምትባል ነገር ኣለዉ። በኣማርኛ ወይም አፋን ኦሮሞ ትርጉሙን ኣላዉቅም። ምናልባት ከማን ኣንሼ ይገልጸዉ ይሆናል።

እላ ስለ ግል ሳይሆን ስለ ሌላ ነዉ። ከማን ኣንሼ ስለ ሌላ ሳይሆን ስለ ግል ነዉ። ይህቺን ልዩነት ብቻ ማስተዋል መግባባትን የምያበዛ ይመስለኛል።

ጥልቅ ባህል ያለዉ ሕዝባችን እላ ፊ እላሜ ይላል። ስለ ግል ሳይሆን ስለ ሌላ ያወሳል። እኛ ትምህርት ቤት ደርሰን ከማን ኣንሼ እንላለን። ስለ ሌላ ሳይሆን ስለ ግል እናወሳለን። ሁሌ ባይሆንም ብዙ ግዜ። ለክርክር የሚበቃ ግዜ። ለክርክር የበቃ ለክርክር መቀጠል ይበቃል።

በተለይ ብዙ ሳይለፉበት ኣዲስ ሀሳብ ሲሰሙ ሳይገባቸዉ ግትር የሚሆኑ ይበዛሉ። በጥበብ እንዲገባቸዉ ማድረግ ይቻላል።

የኣጋጠመኝ ምሳሌ ኣለ። በለዉጥ ግዜ የነበረ ዕድር እንድመራ ተመርጬ የመተዳደርያ ደንብ ኣዘጋጀሁለት። አባላቱ ሀሳብ በመስጠት ማሻሻል ይችሉ ነበር። ጥቂቶች ሀሳብ በመጨመር እንዲሻሻል ኣድርገዋል።

ለማጽደቅ ተሰበሰብን። ኣንድ አባል ኣንድ አንቀጽ ጉድለት ኣለዉ የሚል ሀሳብ ኣቀረበ።

ወድያዉ ኣንብቦ እና የራሱን ሀሳቦች ጨምሮበት የነበረ አባል ጉድለት የለዉም ኣለ። ስብሰባዉን እየመራሁ ጉድለት ኣለዉ እና ዬለዉም የሚል ክርክር ሊነሳ ሆነ። እኔ የጻፍኩት ስለሆነ ጉድለት ኣለዉ ብዬ ኣላሰብኩም።

ስለዚህ ወድያዉ ፈገግ ብዬ ጉድለት የለዉም ያለዉን ኣረጋግቼ ጉድለት ኣላዉ ወደኣለዉ ዞሬ እሺ እስቲ ኣሻሽለዉ ኣልኩት። ለማሻሻል ሲታገል ኣየሁ። ሌሎችም ኣዩት። ኣንድ የሞከረዉ ያልተሻለ ሆነ። ሌሎች ፊት ታግሎ እንደ ነበረ ይሁን ብሎ ሁላችንም ተስማማን። ከፈገግታ ጋር።

ይህ መናገርም የማያስፈልግ ቀላል ምሳሌ ነዉ። አስተሳሰቡ የትም ስራ ላይ መዋል የሚችል ይመስለኛል።

Re: እላ ፊ እላሜ

Posted: 15 Jan 2024, 01:59
by Naga Tuma
ይህን ርዕስ ያስጀመረኝ እኛ ኢትዮጵያዊያን መግባባት ለምን ያስቸግረናል የሚል አይነት ጥያቄ ነዉ።

እላ ፊ እላሜ ጥልቅ የሆነ ባህላዊ አስተሳሰብ ጥሩ መልስ ኣለዉ ብዬ ነዉ ርዕሱን የጀመርኩኝ።

ለምሳሌም ስለ ኣንድ እድር ደንብ ስምምነት ጠቅሻለሁ።

ደንቡ ሳይዘጋጅ በፊት የመሪዎቹ ምርጫ ነበር። የኮሚቴዉ የስራ ድልድል ቀን ከፊቴ ኣይጠፋም፣ እስከነቦታዉ።

በእድሜ፣ በትምህርት፣ እና በስራ ልምድ ከእኔ የሚቀድሙ ነበሩ። ስለዚህ እኔ እንድመራዉ እመረጣለሁ ብዬ ኣልጠበኩም። በዕድሜ፣ በትምህርት፣ እና በልምድ ከእኔ የተሻለ መምራት የሚችሉ ይሁኑ ብዬ ሀሳብ ባቀርብም ወደ እኔዉ ተመለሰ።

ብዙም ሳልቆይ የለዉጥ ግዜ ነዉ እና ቅደምልን ሊሆን ይችላል የሚል ገመትኩኝ። ካዛም በዉስጤ ሰዉ ለዚህም ያመነታል እንዴ ብዬ እሺ ኣልኩኝ።

ያ ግምቴ ትክክል ይሁን ኣይሁን እስከኣሁን ኣላዉቅም።

ደንቡ ጸድቆ፣ ኣንድ ቀን አባል ጎደለብን ብለን ሳንቀመጥ ተሯሩጬ ቶፍል እና ጂ አር ኢ ወስጄ የትምህርት እድል ኣግኝቼ ስወጣ በክብር ሽኙኝ። ተሯሩጬ ጂ አር ኢን ስወስድ ኣንድ ጓደኛዬ ኣታልፍም ኣትልፋ ስለኝ ተገርሜ ኣንተን መሰልኩህ ብዬ መለስኩለት። ተሳስቀን ኣለፍነዉ።

ስምምነት ነበረን። መከባበር ነበረን።

ለትምህርት ስወጣ የዛን ደንብ ቅጂ ወይም ኮፒ ይዤ ነዉ የወጣሁኝ።

ከዓመታት በኋላ እዚህ ኣሜሪካ ዉስጥ ኣንድ ማህበረሰብ ዉስጥ መሳተፍ ከጀመርኩኝ በኋላ ኣንድ ቀን ምርጫ ነበረ። ኮሚቴዉ ዉስጥ እንድገባ ስጠቆም የኣካዳሚ መንገድ ላይ ስለነበርኩኝ ትኩረቴ ወደዛ ስለሆነ እለፉኝ ኣልኩኝ። ሀሳቤን መልሼ መላልሼ ካብራራሁኝ በኋላ እሺ ብለዉ ኣለፉኝ።

ከዛ በኋላ ከተመረጡት ዉስጥ ኣንዱ ደዉሎልኝ ማህበረሰቡን ስለማጠንከር ኣዋየኝ። ደንቡን ኣይቶ መሻሻል እንደምያስፈልገዉ ኣዋየኝ።

እስከዛሬ ድረስ የማስታዉሰዉ የመጀመርያዉ አስተያየቴ ማህበረሰቡ ዉስጥ ገንቢ ዕዉቀት እና ልምድ ካላቸዉ ጋር እንዲወያይ ነበር። በተለይም ኣዋቂ ነዉ ብዬ ያሰብኩትን የኣንድ ግለሰብ ስም ጠቀስኩለት።

እሺ ኣለ። በቅንነት ይለፋ እንደነበረ ነዉ የማዉቀዉ።

የነበረዉን የማህበረሰቡን ደንብ እኔም ኣግኝቼ በቅንነት መሻሻል እንደምያስፈልገዉ ደመደምኩኝ።

ኣዋቂ ነዉ ብዬ እንድያዋየዉ የመከርኩት ሰዉ ኣዋይቶ እሱም በቅንነት ወረ አስ ጅረን አናፍ ዺስ ብሏል ኣለ። እዚህ ያሉትን ለእኔ ተዉልኝ እንደማለት ነዉ። አከባቢዉ ያሉትን ኣማክሮ ለማሳመን ዝግጁ መሆኑ ነዉ የገባኝ። ከእሱ በቀጥታ የሰማሁ ባይሆንም ማለቱን ሰማሁ ያለዉን የማያሳምነኝ ምክንያት ኣልነበረም።

የኮሚቴዉ አባል በቅንነት ሲለፋ ከነበረኝ ደንብ ዉስጥ ሀሳብ ተጨምሮበት፣ የነበረኝን አስተሳሰብም ታክሎበት የተሻሻለ ደንብ ንድፍ ተዘጋጀ እና ለማጽደቅ ዉይይት ተጀመረ። ለሁሉም በቂ የዉይይት ግዜ ተሰጠ።

በመጨረሻም ለማጽደቅ ስብሰባ ተጠራ። ከኣዋቂዎቹ በመጀመርያ የጠቀስኩኝ፣ ተጠይቆ ወረ አስ ጅረን አናፍ ዺስ ብሏል የተባለ፣ ስብሰባዉ ቦታ ስብሰባ የሚመራበት ጉብ ብሎ የተዘጋጀዉ ደንብ ንድፍ ጉድለት ኣለዉ ሲል ሰማሁት። ፊት ለፊቱ ቁጭ ብዬ ነበር።

በተናገረዉ ቃል ኣይባነት ዉስጤ ደንግጦ እያየሁት ድምዜን ዝቅ ኣድርጌ አጭር ጥያቄ በትህትና ጠየኩት። ከዚህ የተሻለ ደንብ ማዘጋጀት ትችላለህ ብዬ።

ምን መልስ እንደመለሰ ኣላስታዉስም። ሁሌ ከፊቴ የማይጠፋዉ ጥያቄዬን እንደሰማ ወድያዉ ዘጠና ድግሪ ፊቱ ወደ ጉኑ መዞሩን ነዉ።

የአካዳሚ መንገድ ላይ ስላለሁ ኮሚቴ አባል መሆኑን እላፉኝ ብዬ መልሼ መላልሼ ስጠይቅ የነበረ ወይም የሰማ ከሆነ፣ ደውዬ ሳይሆን ተደዉሎልኝ ሀሳብህን ስጠኝ ስባል በቅንነት እሺ ብዬ የደወለልኝን እንድያማክር ኣዋቂ ነዉ ብዬ በመጀመርያ የጠቀስኩኝ ግለሰብ ከሆነ፣ ተጠይቆ ወረ አስ ጅረን አናፍ ዺስ ማለቱ እዉነት ከሆነ፣ የተዘጋጀዉን ደንብ ንድፍ ለማንበብ እና ለማሻሻል በቂ ግዜ የነበረዉ ከሆነ፣ ደንቡን ለማጽደቅ በተጠራ ስብሰባ ላይ ጉድለት ኣለዉ ሲል የተሻለ ማዘጋጀት ትችላለህ ተብሎ በትህትና ከተጠየቀ ድንቁርናዉ የት ነዉ?

ስለዚህ ታሪክ ታዝቤ ዝም ብዬ ነበር።

ዛሬም ሰዉ ከቃለ ኣብይነቱ ካልተማረ ወይም ምነዉ እንደዚህ አይነት ቃል ኣባይነት ነዉር ኣይዴለም እንዴ ብሎ የሚመክረዉ ከሌለዉ ሰዉ ምን ይማራል ለማለት ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዕድር ተዘጋጅቶ ኣስማምቶ ቅጂዉን ይዤ የወጣሁኝ ህግ አሜሪካ ዉስጥ ሌላ ያላስማማ ታሪክም ኣለዉ።

ሌላ የአካዳሚ ማህበር ተቋቁሟል የሚል ማስታወቅያ ሳነብ ዘልዬ አባል ኣድርጉኝ ኣልኩኝ።

እሺ ተብዬ እስቲ ደንቡን ላንብብ ኣልኩኝ።

ጠይቄ ብዙም ሳልቆይ እንዳልነበረዉ ግልጽ ሆነልኝ። ኦሮሞን ኣዳን ቡለ፣ ስዳምን ሴራን ቡለ የሚል መልስ ኣግኝቼ።

ኦሮሞ በባህል ይተዳደራል፣ አማራ በሴራ ይተዳደራል እንደማለት ነዉ።

ገርሞኝ ደንብ ኣስፈላጊ ነዉ ብዬ ኣሳምኜ ኣስፈላጊ ከሆነ እኔ ንድፉን ማዘጋጀት እችላለሁ ኣልኩኝ። ምናልባትም ሴረ የሚለዉ ቃል አፋን ኦሮሞም ኣማሪኛም ዉስጥ ያለ ቃል ኦሮሞ እና አማራ ከተባሉ ቃላት በፊት የነበረ ሊሆን ይችላል።

ተስማምተን ከኢትዮጵያ ይዤ የመጣሁትን ደንብ ተንተርሼ ሌላ ደንብ ነደፍኩኝ። ያን ግዜ አከባቢ የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ በዓልን ጨምሮ ሶስት ቀናት እረፍት ስላገኘሁ ሆነ ብዬ ኣስቤበት ሶስቱን ቀናት ተጠቅሜ ኣዘጋጀሁት።

ለመሪዉ ልኬ በአባላቱ መልካም ተቀባይነትን እንዳገኘ ኣስታዉሳለሁ።

ሌሎች የማሻሻያ ሀሳቦችን ኣቅርቤ ነበር። ማስታወቅያዉ እንደተሰራጨ ሌሎች ሁለት ሰዎች ከዛ በፊት ተመሳሳይ ሀሳብ ኣንስተዉ እንደነበረ መጻፋቸዉን ኣንብቤ ስለነበረ ሁለቱም አባል እንዲሆኑ ቢጋበዙ የሚል ሀሳብም ኣቀረብኩኝ።

ቀናት ሳይቆጠሩ እነሱ አባላት ካልሆኑ አባል ኣልሆንም ብሏል የሚል ስሞታ ሌላ ሰዉ ጽፎ ኣነበብኩኝ።

ዘልዬ የገባሁኝ ዘልዬ ወጣሁ። እንደዛ አይነት ጥምዘዛ እኔ ጋ ተቀባይነት ዬለዉም ። እኔ በቅንነት ያልኩኝ አባላት እንዲሆኑ ይጋበዙ ነዉ። ተመሳሳይ ሀሳብ ኣንስተን ነበር ማለታቸዉን ስላነበብኩኝ። እኔ በቅንነት ስላልኩት ሌላ ሰዉ ጽፎ ያነበብኩኝ እነሱ አባላት ከልሆኑ አባል ኣልሆንም ብሏል የሚል ነዉ።

ከወጣሁኝ በኋላ የተጠመዘዘዉን የጻፈዉ እንድመለስ በአካል መጥቶ ጠየቀኝ። መሪዉ ከዛ በፊት የወረቀት ዋስ የሆነልኝ ባለዉለታዬ ቢሆንም በቤተሰብ ደረጃ ከምንተዋወቅ የሃገር ሰዉ ጋር እንደዚህ አይነት ጥምዘዛ ተገቢ ኣይዴለም ብዬ ተሰናበትን።

ሳንሰናበት በፊት ስለደንቡ ተነስቶ እኔ እንደዚህ አይነት ደንብ በሶስት ቀን ዉስጥ ማዘጋጀት ኣልችልም ብሎም ኣስገረመኝ። ከሌላ ሰዉ ድጋፍ ኣግኝተሃል መለቱ መስሎኝ በዉስጤ ሳቅኩኝ።

እነዚህ ሶስት ምሳሌዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ለስምምነት ኣብቅቶ እዚህ አሜሪካ ዉስጥ ሁለቴ ለምን ኣላግባባም ማለት ይቻላል።

የግል የሆነ የፖለትካ አላማ የነበራቸዉ ግለሰቦች ከሆኑ ችግሩ የፖለትካ አላማቸዉ ነበር ማለት ይቻላል።

Re: እላ ፊ እላሜ

Posted: 15 Jan 2024, 02:43
by Axumezana
የኢሳያስ፥ አፈወርቂ፥ ጥምዝምዝ ፥ መልስ ይመስላል፤