Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42567
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አበረ ፤ የሚያጠግብ እንጀራ ምጣድ ላይ ያስታውቃል!

Post by Horus » 01 Jan 2024, 13:35

ፋኖ ቩካ ነው!
ፋኖ ENDF ይሆናል ያልኩት ዝም ብዬ በስመነጋ አልነበረም!
የኢትዮጵያ ንፋስ እየነፈሰ ያለው ወደ ፋኖ ነው በቃ!


Abere
Senior Member
Posts: 15358
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አበረ ፤ የሚያጠግብ እንጀራ ምጣድ ላይ ያስታውቃል!

Post by Abere » 01 Jan 2024, 14:10

ሆረስ፥

____ በእርግጥም ፋኖ በአስተማማኝ ሁኔታ እያሳዬ ያለው ወታደራዊ ብቃት፤ ስነ-ምግባር፤ብስለት እና አገር ወዳድነት የሚያረጋግጠው መጭውን እውነት ነው። ፋኖ የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ የመሰረት አለት ነው።

____ይችን አገር ግን በእውነትም እግዚአብሄር እየጠበቃት ነው። በእርግጥ የጠፋው ህይወት፤ሃብት እና ጊዜ ይቆጫል - ያሳዝናል። ግን ምን ማደረግ ይቻላል - ሰይጣን ከገባ የግድ ሰይጣኑ መወገድ አለበት። በቅድስት አገር እስራዔል እየሆነ ያለው እንድሁ ነው። ቅዱስ ባለበት ሰይጣን አይጠፋም እንድሉ። ይህን ያልኩበት ወያኔ ሊቀ ሰይጣን ነበር። በወያኔ አቅም የህዳጣን ግዞቷን ዝንተ አለማዊ ለማድረግ ከሰማይ በታች ያልሞከረችው ያልነደፈችው አልነበረም - በጦር እስከ ከሚሳይል በድፕሎማሲ እስከ ዓለም ዳርቻ ተስፋፍታ ታጥቃ ነበር። የእርሷ 100% ጠላት ደግሞ አማራ ነበር። አማራ አሽሙር እንጅ ኢትዮጵያን እጠላለሁ ላለማለት የተጠቀመችው ዘደ ነው። እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሄር እንዳለው ያልታጠቀው አማራ በእግዜር ክህነ-ጥበብ ባዶ እጁን ገጥሟት በ3 ቀን ድል ነሳት - የታጠቀችውን ማረካት። ይህም ፋኖ ባይሰማራ ይህኔ ኢትዮጵያ ቅርጫ ተበልታ አልቃ ነበር። ይህ እግዜር ኢትዮጵያን ይጠብቃል። የወያኔ ቀስት ሰበረ። አንድ ሰይጣን ሲወጣ ብቻውን አይደለም በርካታ ሰይጣኖች አብረውት አሉ። አሁን እግዚአብሄር 2ኛውን ኦነግ የሚባለውን ሰይጣን በማውጣት ስራ ላይ ነው። ሰይጣናት በየዋሃን ላይ መከሩ፤ በየዋሃኑ መስዋዕትነት ላይ በደቡብ አፍሪካ ዕጣ ተጣጣሉ - ይህም የእግዜር ስራ ነው። ሌላ ሰይጣን የሚያጠምድበት ቀጭን መንገድ። አሁን የዳዊት አምላክ የተገፋውን የኢትዮጵያን ህዝብ ወገነ - ፋኖ የበለጠ ገፋው አቀጣጠለው። ለ 7 ቀን ሲያስቡት እነርሱን ለቁርስ አደረሳቸው - የጉግ ማንጉግ ወረሙማ ትጥቅ በደጁ የመኸር ነዶ አደረገለት። ነፍሰ ገዳዮች በወለጋ፤አሩሲ፤ወዘተ ህጻናት የጨፈጨፉ ወረሙማ ሄሮድያን የንጹሃን ደም ጠርቷቸው አማራ ዘንድ ሄዱ በዚያ ደመ -ከልብ በመሆን የውሻ ሞት በየሚዳው ሞቱ። ይህ ሁሉ እግዚአብሄር የተገፉን የሚደግፍ በእና ኢትዮጵያ ሀገረ እግዜር በመሆኗ ነው። ኢትዮጵያ ወደ እግዚአብሄር እጆቿን ትዘረጋለች፤ ጠባቂ መከላካያ ሃይል ይሰጣታል። ይህ ምድራዊው ፋኖ ህግ እና መንግስት ለማስከበር እየተወለደ ነው።

Post Reply