Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ባለ መስቀሉና ከሱ ቀጥላ ያለችው ግን . . . .

Post by sarcasm » 27 Dec 2023, 22:14

ባለ መስቀሉና ከሱ ቀጥላ ያለችው ግን ወንዶች ናቸው?


የአማራ ክልል መንግስት ያደረገውን የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና መስጠት ተጀመረ
****************************



የአማራ ክልል መንግስት ያደረገውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የገቡ ታጣቂዎች በዘጠኝ የተሃድሶ ማዕከላት ስልጠና መጀመራቸውን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ከ700 በላይ ታጣቂዎች በጠዳ ተሃድሶ ማዕከል ዛሬ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል።
በዚህ ወቅት የተገኙት የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ በሪሁን መንግስቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር መንግስት በተደራጀ አግባብ ህግ የማስክበር ስራ እያከናወነ ነው።

እስካሁን በተከናወኑ ተግባራትም በየአካባቢው ሰላም በማስፈን የተሻለ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።

ህግ ከማስከበር ስራው ጎን ለጎንም በተሳሳተ መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎችን በማወያየት ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ይፋዊ የሰላም ጥሪ የተቀበሉና የሰላም አማራጭን የተከተሉትን ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡትን የተሃድሶ ስልጠና እንዳጠናቀቁ ሰላማዊ ህይወት የሚጀምሩበት ሁኔታ በአፋጣኝ የማመቻቸት ስራ ይከናወናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በተሳሳተ መንገድ ችግር ወስጥ የገቡ ወገኖች ሰላማዊ አማራጭ እንዲከተሉ የሰላም ጥሪው እድል መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አላምረው አበራ ናቸው።

የተሃድሶ ሰልጣኞች በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መርህ በመከተል ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

የሰላም ጥሪውን ተቀብለውና በድርጊቱ ተፀፅተው የሚገቡ ወገኖች የበደሉትን ህብረተሰብ በልማት መካስ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የተሃድሶ ስልጠናው ለአስር ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ የክልልና የዞን አመራር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

Please wait, video is loading...