Page 1 of 1

Axumezana & sarcasm are allegedly Fano: --- > Abiy Ahmed Mekelle arming Fano?! hahaha

Posted: 20 Dec 2023, 10:14
by Abere
Axumezana & sarcasm are allegedly Fano: --- > Abiy Ahmed Mekelle arming Fano?! hahaha
ጉድ ያለው ገንፎ አድሮ ይፋጃል ሆነ እኮ ነገሩ። ይህ ፍራቻ ፋኖን ወያኔ አስመስሎ ለፓለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም እንደሆነ ግልጽ ነው። ሌላ አንድ ግልጽ የሆነው ጉዳይ የአብይ አህመድ 1ቁጥር ጥላት እና የፍርሃት ምንጭ ግብጽ ወይም ኤርትራ ወይም ወያኔ ሳይሆን አማራ ፋኖ መሆኑን ነው

ከዚህ ባሻገር ደግሞ ትልቁ የአብይ አህመድ ወይም ኦሮሙማዎች የረዥም ጊዜ ስጋት አንድ ወቅት ላይ አማራ እና ትግሬ በአንድነት በመቆም የግፍ ፈረስ የሆነውን ኦነግ ለመጣል የጋራ መስዋዕትነት ይከፍላሉ ይህን ለማድረግ ደግሞ ከአሁን የተሻለ ሌላ ጊዜ አያገኙም በማለት ነው። የትግራይ እና የአማራ ህዝብ ከእንቅልፋቸው በመንቃት የውድቀታቸው ምንጭ የሆነውን የጎሳ ፓለቲካ እና ክልል ሊደመስሱት ይችላሉ ነው። በእርግጥም ወያኔ የጫረችው ጦስ ሊፈታ የሚችለው የጎሳ ክልል በማፍረስ እና ሁሉም እኩል አገሬ ብሎ መኖር ፤ ተንቀሳቅሶ ሃብት ማፍራት ሲችል ብቻ ነው። አማራ እና ትግሬ ባለሙት አዲስ አበባ ከተማ እንኳን መኖር አለመቻላቸው የሚያሳየው የኦሮሙማ ልክ ያጣ ብልግና ነው። ይህ አስቀያሜ ትርዒት ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የአማራ እና የትግራይ ህዝብ ያውቅብኛል በሚል ፍርሃት ኦሮሙማዎች እንደሚጠመዱ ግልጽ ነው።

የሚያስቀው ድራማ ግን ወያኔ እና ፋኖ ተባበሩብኝ መሳሪያ ከመቀሌ አማራ ክልል እየገባ ነው የሚለው ነው።