Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የ ሰላም ሚንስትር ዴታ ኦቦ ታዪ ደንደአ ስለሰላም በመናገራቸው በ አብይ አህመድ በተፃፈ ቀጭን ትእዛዝ ከስልጣን ተባረሩ ፡)

Post by Za-Ilmaknun » 11 Dec 2023, 12:12

የ ኦህዴድ አገዛዝ አንድ ሁለት እያለ የራሱን ደንገጡሮች እየበላ ነው፡፡ ለማስመሰል የተደራጀውና በ ብአዴኑ ምስለኔ ፡ ብናልፍ አንዱአለም የሚመራ የሰላም ሚኒስትር፡ ዛሬ ሚኒስትር ዴታው እንዲባረር የሆነው ፡ የሚኒስትር መስሪያቤቱ ስራውን ለመስራት በመሞከሩ ነው፡፡

ከ ጦርነት ውጭ ወደ ዉጭ ያለው ኦሮሙማ ትግራይን ካወደመ በሁዋላ፡ አሁን ደሞ አማራውን ለማድቀቅ ፡ የድሮን መአት እያወረደበት ቢሆንም፡ ጀግናው ፋኖ ግን ግትልትሉን ሰራዊት መሬት ላይ እያራወጠው ነው፡፡

የታዪ ደንደአ የስንብት ማስታወሻ፡-

ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ::

እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!

ታዬ ደዳዓ

@showapresa


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የ ሰላም ሚንስትር ዴታ ኦቦ ታዪ ደንደአ ስለሰላም በመናገራቸው በ አብይ አህመድ በተፃፈ ቀጭን ትእዛዝ ከስልጣን ተባረሩ ፡)

Post by Za-Ilmaknun » 11 Dec 2023, 19:53

The Oromo PP is fragmented and is in the course of implosion. The party's immersion in grand corruption and its apparent disregard to human rights is creating a strong schism that can possible rapture the country. The PM is deluded in to believing that the unrelenting bombing of the amhara people will hand him over the key to solve his mismanagement of the country.


Post Reply