የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ "የሚከፈለኝ ደመወዝ አንድ ኩንታል ጤፍ አይገዛም፡፡ 100 ኪሎ ጤፍ ለመግዛት የሚከፈለኝ ደመወዝ ስለማይበቃኝ ተጨማሪ ገንዘብ ተበድሬ ነው የምገዛው፤
Posted: 05 Dec 2023, 12:14
This is the naked truth about the OPDO regime and why the country is ruffled with so much grand corruptions. Every indications are that the regime is rotten to the core and soon shall be collapsing..
በኑሮ ውድነት ምክንያት የሚከፈላቸው ደመወዝ አላኖር ያላቸው ከ25 መቶ በላይ ሠራተኞቹ በአንድ ዓመት ውስጥ ሥራቸውን መልቀቃቸውን ጠቅሶ መፍትሔ ይሰጠኝ ሲል፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለፓርላማ ጥያቄ አቀረበ፡፡ኮሚሽኑ የተሰጠው ኃላፊነት ትልቅና አገራዊ ፋይዳ ያለው ሆኖ እያለ፣ ለሠራተኛው የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛ በመሆኑ በየጊዜው እየለቀቀ መሆኑን ጠቅሰው፣ ‹‹ምናልባት የቀሩትም ሠራተኞች ሥራ ፍለጋ ላይ ይሆናሉ ብዬ እገምታለሁ፤›› ብለዋል።
የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለ2016 በጀት ዓመት የተመደበለት ዓመታዊ በጀት 62 ሚሊዮን ብር መሆኑንና ከዚህ ውስጥ 25 ሚሊዮን ለደመወዝ ሲያውለው ቀሪውን ለፀረ ሙስና ትግል የተመደበ የሥራ ማስኬጃ ስለመሆኑ አስረድተው፣ የሙስና ሥጋት ከፍተኛ በሆነበት አገር ውስጥ ባልተሰጠ በጀትና በሌለ ገንዘብ እንዴት አድርጎ ሥራውን በሚፈለገው መጠን እንዲሠራ ይጠበቃል? ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
https://www.ethiopianreporter.com/124526/