Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
-
Contact:
Post
by Assegid S. » 01 Dec 2023, 20:35
ኣንባቢ በራሱ ቤት ተርጉሞ ... እኔም በራሴ ቤት ዘረፍኩ ወይንም ሰረቅሁ ያልኩትን ቅኔ ይረዳው።
ነገር ግን ... ምንም እንኩዋን '
ተው ስማኝ እያለው' የሚለው ግልፅ ሓሳብ '
ኣምላክን እየለመነው' በሚል መንፈስ የቀረበ ቢሆንም ... ገበሩ (ውስጡ) ግን የት እና እንዴት እንደሰማሁት በደንብ የማላስታውሰው፥ ነገር ግን የትግል መዝሙር ነው ብዬ የማስበው ሓረግ ነው። እንደ እድል ሆኖ ተከታይ ስንኞቹን ባላስታውስም "
ተው ስማኝ ሃገሬ ... ኧረ ስማኝ ሃገሬ " የሚል እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።
-
sarcasm
- Senior Member
- Posts: 11594
- Joined: 23 Feb 2013, 20:08
Post
by sarcasm » 01 Dec 2023, 22:20
Apparently, they say there are two sides to every story. Here's the other side of the story.
"ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (ከኢዴፓ መስራች መስጋቾች አንዱ)
ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!
በሰሜን ወሎ የወያኔ አስተዳደር እየተመሰረተ ነው… #የወሎ_የክልልነት_ጥያቄ_እውን_ይሆናል!
መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁሙን ካነሳ ወዲህ እርምጃ ይወስዳል ብለን ብንጠብቅም በሰሜን ወሎ የጁ-ራያ ግንባር ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ በሰሜን ወሎ ችግሩ የከፋ ሆኖ ሳለ ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ወያኔ፡- ከዚህ በፊት በቆቦና በሌሎች የራያ አካባቢዎች ህዝብ እየሰበሰበች ከንቲባ እያስመረጠች የራሷን አሻንጉሊት አስተዳደር መፍጠሯ ይታወቃል፡፡ (A state within a state)
አሁን ደግሞ መርሳ፣ መሐል አምባ (ሱዳን ሰፈር) እና ሊብሶ ከተሞችን ተቆጣጥራ ህዝቡን ሰብስባ የቀበሌ አስተዳደር እያስመረጠች ነው፡፡ በመጋዘን ያለውን የእርዳታ እህል ለህዝብ በማከፋፈል “መንግስት ነኝ” እያለች ነው፡፡
#ወሎ_በአማራ_ክልል_መንግስት_ተክዷል!!! እነሆ ዘመዶቻችን በወያኔ አስተዳደር፤ እኛ በፌዴራል መንግስት አስተዳደር ስር ሆነናል፡፡ ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ራ
ሱን የቻለ ክልል እንዲሆን የወሎ ምሁራንና ብልጽግና ውስጥ ያላችሁ የፖለቲካ ልሂቃን በያለንበት መምከር ይገባናል፡፡
በአማራ ክልል ሸፍጥ ወሎ በልማት ወደኋላ እንዲቀር መደረጉ ሳያንስ አሁን ይባስ ብሎ በጠላት ኃይል እንዲተዳደር ተፈርዶበታል፡፡ ታዲያ እንዴት ሆኖ፣ በየትኛው የሞራል ህግ ነው መቀመጫውን ባህር ዳር ባደረገው “የአማራ ክልል” ስር ሆነን የምንቀጥለው?
ይህ የችግር ጊዜ ያልፋል! - እንተያያለን!!!
Please wait, video is loading...
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15365
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 02 Dec 2023, 11:28
ዘመኑ ቤተ-መቅደስ እና ቤተ-መንግስት የተሻረጠባቸው ቀሳውስት እና ጳጳሳት የተፈለፈሉብት በመሆኑ፤ የተሰሚነት ግሽበት ጣሪያ የዘለቀ ስለሆነ የወሎ ህዝብ ንግግራቸውን ከመጤፍ አልቆጠረውም። ወሎ ቤተ-አማራ እሳላም ክርስቲያኑ ነጻነቱን በክንዱ እያረጋገጠ ነው።
ስልጣን እና ባለስልጣናት (ምንጫቸው ከህዝብ ባለመሆኑ) የቀለሉበት ነው፤ስለ ቃላቸው ሳይሆን የእራሳቸው ህይወት ጭዳ እንደ ንግግራቸው ከንቱ እንዳይሆን። ወሎ ቤተ-አማራ እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ የአቡኑ ህይወት በወረሙማ እጅ ነው - ፊዩዙን ነቅሎባቸው ፋኖ ነው ይላል በማለት።
በወያኔ እና ኦሮሙማ በአማራነት እንደ ወሎ ከባድ ሂሳብ የከፈለ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ወሎ ለወያኔ ውድቀት ለኦሮሙማ አብይ ውርደት ትልቁ ምክንያት ነው። ወሎን የነካ የለውም በረካ ይባላል በታሪክ። ከዐጼ ዮሀንስ እስከ ዐጼ ሃይለስላሴ ከዚያም በቅርብ እስከ ትግራይ ወያኔ ድረስ ከወሎ ጋር አተካራ በመግባታቸው የውርደት ሞት እና ሽንፈት ተከናንበው አልፈዋል - ወሎ ግን ቀጥሏል።
አጼ ዮሀንስ ወሎን እጅግ ተገዳደረ እና
የዩሀንስ በቅሎ ብረኪ ብረኪ፤
መተማ ላይ ሂደሽ እንዳት ማረኪ።
እንደ ተባለውም አጼ ዮሀንስ መተማ ላይ ተገደሉ ለመቀጣጫም አንገታቸው ተሰየፈ። አንድ አንድ የታሪካ ጸሀፍት የወሎ ሙስሊሞች አጋጣሚውን ተጠቅመው ተኩሰው ገደሏቸው ይባላል።
ዐጼ ሃይለስላሴ እንድሁ የነበራቸው ፍራቻ እና ጥላቻ በልጅ እያሱ ምክንያት ውሎን በድህነት ማነቆ ጥለውት ነበር። በታሪክ ከፍተኛ ንቅናቄ ወሎ ነበር የተጠነሰሰው ታዲያ ንጉሱ በመጨረሻ ከእያሱ የከፋ ዕድል ደረሳቸው - ሽንት ቤት እርጉም ደርግ ቀበራቸው።
የትግራይ ወያኔ ወሎን ቆርጦ ወደ ትግራይ በመውሰድ ብቻ ሳይሆን በመጨፍጨ አሳልፎም ለኦነግ በወለጋ፤ሀረር፤አሩሲ በማስረድ እጅግ አሰቃየው። በመጨረሻ የወልድያ ፋኖን ያስታውሳሉ። ወያኔን እየገረፈ ወደ መቀሌ አንከሳከሰው - ወያኔ ተሸነፈ ወደቀ።
ጎጃሜን ቡዳ ነው ብላችሁ ስትሉ፤
ትግሬን ወሎ በላው እንግድህ ምን ትሉ።
ተብሎም ተገጠመ። በትግራይ የፈሰሰውን መርገምት ሁሉም ያስታውሳል። ከ ሚልዮን በላይ ያለቀው ወያኔ ወሎ ምድር ገብቶ ነው። አሁን ደግሞ ኦሮሙማ በተራው ሂሳቡን እየከፈለ ነው። ወለጋ የነጻ እርምጃ ሲወስድ የነበረው ኮልኮሌ አሁን ሊጥ እንደ ደፋ ውሻ ወንድ ሳይቀር ሴት እያቀመሰው በየጢሻው እየተደፋ ነው።
Assegid S. wrote: ↑01 Dec 2023, 20:35
ኣንባቢ በራሱ ቤት ተርጉሞ ... እኔም በራሴ ቤት ዘረፍኩ ወይንም ሰረቅሁ ያልኩትን ቅኔ ይረዳው።
ነገር ግን ... ምንም እንኩዋን '
ተው ስማኝ እያለው' የሚለው ግልፅ ሓሳብ '
ኣምላክን እየለመነው' በሚል መንፈስ የቀረበ ቢሆንም ... ገበሩ (ውስጡ) ግን የት እና እንዴት እንደሰማሁት በደንብ የማላስታውሰው፥ ነገር ግን የትግል መዝሙር ነው ብዬ የማስበው ሓረግ ነው። እንደ እድል ሆኖ ተከታይ ስንኞቹን ባላስታውስም "
ተው ስማኝ ሃገሬ ... ኧረ ስማኝ ሃገሬ " የሚል እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።
-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
-
Contact:
Post
by Assegid S. » 03 Dec 2023, 05:45
sarcasm wrote: ↑01 Dec 2023, 22:20
Apparently, they say there are two sides to every story. Here's the other side of the story.
"ከዚህ ጦርነት በኋላ ወሎ በአማራ ክልል ስር ሆኖ ሊተዳደር አይገባውም፡፡ ወሎ በአማራ ክልል መንግስት ተክዷል!" ዓብዱራሕማን አሕመዲን (ከኢዴፓ መስራች መስጋቾች አንዱ)
Hello Sarcasm; thanks a lot for the post. ግን ሁሌም የሚገርመኝ ነገር ... እንደ ምስክር የምትቆጥራቸው፣ እንደ ማስረጃ የምታመጣቸው ሰዎች ከኣደርባዮች Depot ኣዴፓ ነው
እስቲ ህልምም ቢሆን እንኳ ለሰከንድ እናልምና ወሎን ወዴት ክልል መውሰድ ፈለገ?
የወሎ ሰው ስነልቦና ከኣማራ ጋር ካልሆነ በስተቀር ከማን ጋር ይጋጠማል? ለማንስ ይቀርባል?
የሁለትና ሦስት ትውልድ ደም ጠጥቶ ህይወት ካጠፋው
ድራኩላ? ስጋና አጥንት በልቶ አካለ ስንኩል ካደረገው
ኣዞ ትህነግ ጋር ወይንስ እርጉዝ በስለት ቀዶ ሽል እያፈሰሰ selfie ከሚነሳው
አጋንንት ኦህዴድ ጋር? የእስላምና ክርስቲያን ሥጋን በክር ለይቶ ቋጥሮ በኣንድ ማሰሮ ቀቅሎ በፍቅር አብሮ የሚበላው ወሎ ለማን ይቀርባል ብሎ አሰበ? ዛሬም ድረስ 'በተቀደሰው ምድሬ እስላም አይቀበረም' ብሎ የሓዘንተኛን ፊት በላብ እና እምባ አያሳጠበ ሦስትና ኣራት ሰዓት በእግር ከሚያስጉዘው ህወሃት ጋር ወይንስ ቤተክርስቲያን በረንዳ ላይ ህፃናትን በካራ ከሚያርደውና ከሚያሳርደው ኦህዴድ ጋር?
ህልም እንደፈቺው ነው ስለሚባል መልሱን ለኣንተ ትቼዋለሁ

መልካም ሰንበት ይሆንልህ ... ወንድሜ Sarcasm
-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
-
Contact:
Post
by Assegid S. » 03 Dec 2023, 06:01
Abere wrote: ↑02 Dec 2023, 11:28
ዘመኑ ቤተ-መቅደስ እና ቤተ-መንግስት የተሻረጠባቸው ቀሳውስት እና ጳጳሳት የተፈለፈሉብት በመሆኑ፤ የተሰሚነት ግሽበት ጣሪያ የዘለቀ ስለሆነ የወሎ ህዝብ ንግግራቸውን ከመጤፍ አልቆጠረውም። ወሎ ቤተ-አማራ እሳላም ክርስቲያኑ ነጻነቱን በክንዱ እያረጋገጠ ነው።
ስልጣን እና ባለስልጣናት (ምንጫቸው ከህዝብ ባለመሆኑ) የቀለሉበት ነው፤ስለ ቃላቸው ሳይሆን የእራሳቸው ህይወት ጭዳ እንደ ንግግራቸው ከንቱ እንዳይሆን። ወሎ ቤተ-አማራ እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ የአቡኑ ህይወት በወረሙማ እጅ ነው - ፊዩዙን ነቅሎባቸው ፋኖ ነው ይላል በማለት።
በወያኔ እና ኦሮሙማ በአማራነት እንደ ወሎ ከባድ ሂሳብ የከፈለ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ወሎ ለወያኔ ውድቀት ለኦሮሙማ አብይ ውርደት ትልቁ ምክንያት ነው። ወሎን የነካ የለውም በረካ ይባላል በታሪክ። ከዐጼ ዮሀንስ እስከ ዐጼ ሃይለስላሴ ከዚያም በቅርብ እስከ ትግራይ ወያኔ ድረስ ከወሎ ጋር አተካራ በመግባታቸው የውርደት ሞት እና ሽንፈት ተከናንበው አልፈዋል - ወሎ ግን ቀጥሏል።
አጼ ዮሀንስ ወሎን እጅግ ተገዳደረ እና
የዩሀንስ በቅሎ ብረኪ ብረኪ፤
መተማ ላይ ሂደሽ እንዳት ማረኪ።
እንደ ተባለውም አጼ ዮሀንስ መተማ ላይ ተገደሉ ለመቀጣጫም አንገታቸው ተሰየፈ። አንድ አንድ የታሪካ ጸሀፍት የወሎ ሙስሊሞች አጋጣሚውን ተጠቅመው ተኩሰው ገደሏቸው ይባላል።
ዐጼ ሃይለስላሴ እንድሁ የነበራቸው ፍራቻ እና ጥላቻ በልጅ እያሱ ምክንያት ውሎን በድህነት ማነቆ ጥለውት ነበር። በታሪክ ከፍተኛ ንቅናቄ ወሎ ነበር የተጠነሰሰው ታዲያ ንጉሱ በመጨረሻ ከእያሱ የከፋ ዕድል ደረሳቸው - ሽንት ቤት እርጉም ደርግ ቀበራቸው።
የትግራይ ወያኔ ወሎን ቆርጦ ወደ ትግራይ በመውሰድ ብቻ ሳይሆን በመጨፍጨ አሳልፎም ለኦነግ በወለጋ፤ሀረር፤አሩሲ በማስረድ እጅግ አሰቃየው። በመጨረሻ የወልድያ ፋኖን ያስታውሳሉ። ወያኔን እየገረፈ ወደ መቀሌ አንከሳከሰው - ወያኔ ተሸነፈ ወደቀ።
ጎጃሜን ቡዳ ነው ብላችሁ ስትሉ፤
ትግሬን ወሎ በላው እንግድህ ምን ትሉ።
ተብሎም ተገጠመ። በትግራይ የፈሰሰውን መርገምት ሁሉም ያስታውሳል። ከ ሚልዮን በላይ ያለቀው ወያኔ ወሎ ምድር ገብቶ ነው። አሁን ደግሞ ኦሮሙማ በተራው ሂሳቡን እየከፈለ ነው። ወለጋ የነጻ እርምጃ ሲወስድ የነበረው ኮልኮሌ አሁን ሊጥ እንደ ደፋ ውሻ ወንድ ሳይቀር ሴት እያቀመሰው በየጢሻው እየተደፋ ነው።
Hello Abere; thanks a lot for the comment post

አስተያየትህ ግልፅ ነው። ከሃሳብህ ጋርም
ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። እኔ በዚህ post-thread ላይ ቁጭት ለመፍጠርና አጉልቼ ለማሳየት የፈልኩት ካባ ሸላሚዎቹንና መስቀል ተሸካሚዎቹን ባንዳዎች ነው። እነዚህም ቢሆኑ
ጥቂቶች እንጂ ሁሉንም አይወክሉም። ሌላው ቢቀር ... የትላንቱን አባት መልዕክት ማዳመጥ ብቻ በቂ ነው።
አለበለዚያማ ... አንተ የዘረዘርከውን የቀድሞ ገድልና ተጋዳዮች ትተን ... ዛሬስ ቢሆን እነ መሬ ወዳጆ፣ እነ ሓሰን ከሪሙ የት የበቀሉ ?! ነገር ግን .... ከላይ እንዳልኩት ... የእኔ ዋነኛው ፍላጎት ቁጭት በመፍጠር እነዚህ ኣደርባዮች ሃቅ ሃቃቸው እንዲከፈላቸው ማድረግ ነው። ለሰፊና ኣስተማሪ አስተያየትህ በድጋሚ በጣም አመሰግናለሁ።
መልካም ሰንበት ይሁንልህ ... ወንድሜ Abere