Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by Assegid S. » 27 Nov 2023, 13:00

https://www.eaglewingss.com/



ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Chuncheon - ከደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ Seoul በኣንድ ሰዓት የየብስ ትራንስፖርት ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ። ከተለያየ ሀገራት የተሰባሰብን ግለሰቦች ትምህርታዊ ጉዟችን መዳረሻ ካደረጋቸው ሀገራት መካከል South-Korea ኣንዷ ነበረችና አጋጣሚውን በመጠቀም የሀገሪቱን ብሔራዊ ሙዚየም በመጎብኘት ላይ ነን። በግሩፕ የተሰጠንን አስጎብኚ ( guide ) በመተው እኔና ሁለት ጎደኞቼ ወደ-ኋላ ቀረት በማለት ... በየቅርሥና ቅርጹ ራስጌና ግርጌ የተለጠፈውን መግለጫ በማንበብ የየራሳችንን ግንዛቤ በመለዋወጥ ላይ ሳለን ...  ከኣስጎብኚያችን ጋር ከፊት የቀደሙት ሌሎች ጎደኞቼና አስተማሪዎቼ ድንገት ወደ-ሗላ በመዞር በኣንድነት ስሜን ጠሩት።  

ፊታቸው ላይ የማየውን ፈገግታ ምንጭ ለማውቅ እኔና ከእኔ ጋር የነበሩት ሁለት ጎደኞቼ ፈጠን ፈጠን ብለን በመራመድ ስንቀላቀላቸው ግን ... በዜግነት ደቡብ ኮሪያዊ የሆነው አስጐብኚ  እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ 'are you from Ethiopia?’ ሲል በመገረም ጠየቀኝ። ነገሩ ትንሽ ግር ቢለኝም ‘አዎን ... ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ስል መለስኩለት። ከዛም ... ከላይ እንደ feature image የተጠቀምኩትን ቅርጻቅርጽ እየጠቆመኝ ... የ'ጥቋቁር' ሰዎቹን ማንነትና በ'ነጮቹ' ሀገር በድል አድራጊነት ኩራት በክብር የቆመውን ወታደር ጀብድ ገለፃ በሚያደርግበት ወቅት ... ከግሩፑ መካከል ኣንድ ኢትዮጵያዊ መኖሬ እንደተነገረውና ጎደኞቼም ይህን ታሪክ "ሊያበስሩኝ" ተሽቀዳድመው እንደጠሩኝ ተረዳሁ።

አስጓብኚው እኔ ከማውቀው በላይ ኮሪያ ሰለዘመተው ስለ ቃኘው Battalion ዘርዘር ባለመልኩ ገለፃውን ሲያቀርብ ...  ነፃ አውጪው ዘማች እኔው እራሴ የሆንኩ መስሎ እስኪሰማኝ ድረስ ... የጎደኞቼና የአስተማሪዎቼ አይኖች ሙሉ በሙሉ ሊባል መሚችል መልኩ እኔ ላይ እንደ ተተከሉ ነበር። ለነገሩ በኣያት ቅደመ-ኣያቶቹ ታሪክ የማይኮራ ኣንድም ባንዳ አልያም እንደ ጥርስ መፋቂያ እንጨት ግንዱ እየተቆረጠ የተራባ  - ዘር አልባ! ነው።

ከሁለት ዓመት በላይ በፈጀው የኮሪያ ጦርነት  ከ 3000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች በጦርነቱ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፥ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ያኔ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ምድር እስክትጠቀለል ድረስ ለመላው ኢትዮጵያዊ  ክብርና ሞገስ የሚሆኑ 536 ዘማቾች ቆስለው 212ቱ ደግሞ ተሰውተዋል - ነፍስ ይማር! ከሁሉ በላይ የሚያስገርመውና ለዛሬ ኣጭር ፅሑፌም መንደርደሪያ ሃሳብ ላደርገው የወደድኩት እውነት ደግሞ ... ኣንድም ኢትዮጵያዊ እጁን ለጠላት ጦር አለመስጠቱና በምርኮኝነት አለመያዙ ነው። ከእኔ ገላፃና ትርጉም በተሻለ የደቡብ ኮሪያ የጦር መታሰቢያ ኢንስቲትዮት እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል፦  
A total of 122 Ethiopian soldiers were killed, and 536 were wounded. There were no prisoners of war.

Overall, as a unit, the Ethiopians never lost in combat during the war and earned the US Presidential Unit Citation. The Ethiopian soldiers also deducted a portion of their monthly salary to support Korean children orphaned by the war.
(Source: Korean War Memorials)
ደም ፦ ከዘር ወደ ዘር የሚዛወር፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር ፈሳሽ አሻራ ነው። ለዚህም ነው፦ ግማሽ መንፈቅ ሊሞላው ጥቂት ወራት በቀረው የኣማራ ክልል ጦርነት የኦህዴድ ዘረኛ ሠራዊት ኣንድ ፋኖ መማረክ … ከሰማየ-ሰማያት ኮከብ እንደማውረድ ሆኖ የከበደው። ፋኖ ከነፍሱ ይልቅ ለእጁ አብልጦ ይሳሳል። በትግራዩ ጦርነት፦ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከተራ ወታደር እስከ ኮሎኔል፣ ባለሥልጣን ሳይቀር በሰልፍ ደርድሮ  "ተመልከትሉኝ! በብር የምለውጠው ምርኮ" እያለ እንዳልፎከረ፥ ለኦህዴድ ሠራዊት ዛሬ ፋኖ 'መንፈስ' ሆኖበታል … የማይያዝ! የማይጨበጥ!

እናቱ እህ! ብላ አምጣ የወለደችው እና የሰፈር አዋላጅ ማንቁርቱን አንቃ ጎትታ ያወጣችው ወንድ የሚለየው እንዲህ ሜዳው ላይ ሲገናኙ ነው። ፋኖ ፦ በምድር የሰማያዊቷ ከንዓን አምባሳደር ሆኖ የተሾመው ጳጳስ ቤተመቅደሱን ንቆ ቤተመንግስት በሚቀድስበት አሳፋሪ ዘመን … የምስኪኑን ደም፣ የደሃውን እንባ ለመታደግ የተነሳ የኣምላክ ሰይፍ ነው። እናም … "ለእግዜሩም እግዜር ይሰጠው!" ብለን በዚች አጭር ግጥም ብንለያይስ?

*****

እንኳን የሚጨበጥ … የሚያዝ በምርኮ
ጠምዝዘው  የሚያስሩት … በቃጫ፣  ሲባጐ

በዲናር ደልለው  … ቢመኙ ሊስሙት
እንደ አቡኑ መስቀል … ከፍለው ሊሳለሙት
ፋኖ የኣባቱ ልጅ
መች አለውና እጅ?

ይሄ የኣማራ ኩራት … ቃታ ቀለበቱ
አጥልቆባት እሳት … ትፋጃለች ጣቱ!

N.B. ጥራትን ታሳቢ በማድረግ በገላጭ ምስልነት የቀረበው ፎቶ ከግለስብ ካሜራ ሳይሆን ከኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ድህረ-ገፅ ላይ የተወሰደ ነው።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19107
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by Axumezana » 27 Nov 2023, 14:09

ፋኖና፥ ቃኘውን(ከየኢትዮጵያ፥ ጦር፥ የተወጣጣውን)፥ ምን፥ አገናኘው?

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by Assegid S. » 27 Nov 2023, 16:16

Axumezana wrote:
27 Nov 2023, 14:09
ፋኖና፥ ቃኘውን(ከየኢትዮጵያ፥ ጦር፥ የተወጣጣውን)፥ ምን፥ አገናኘው?
ደም! በባንዳነት ያልተበረዘ፣ በቅጥረኝነት ያልተከለሰ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ደም 8)

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by sarcasm » 27 Nov 2023, 16:25

Welcome back to the forum brother Assegid. I think it would be fitting to remind you about about Tilahun's ጃፓኗን ወድጄ on this thread as he was one of the 3000 Ethiopian soldiers stationed in Korea. I don't know where he would fit on this Fano v OPDO narration though.

እሩቅ ምስራቅ ሳለሁ
ጃፓንዋን ወድጄ . . .

Tilahun Gessesse Japanuan Wedje // ጥላሁን ገሰሰ ጃፓኗን ወድጄ


Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by Revelations » 27 Nov 2023, 16:47

አይ ኤዱ የሕወሃት የበኩር ልጅ! ፋኖ አማራ ብቻ ነው ብለው የነገሩሽን ምነው ብትረሺው:: ቅ ቅ ቅ!

ስለ ጥልሽ ማንነት ግን ትንሽ ብትቆፍሪ ትክክለኛ መሰረቱን ታገኚው ነበረ! ወይንም እውነቱን እያወቅሸው ስታብይ ተኝተሻል:: ቅ ቅ ቅ!




Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by Assegid S. » 27 Nov 2023, 16:57

Hello Brother Sarcasm, thanks a lot for the welcoming and for the post. Actually; they were around 6000 troops that deployed in Korea yet half of them were not sent to the actual war front. I like the song and Japanese girls are beautiful, Barbie with flesh and soul 8)

በነገራችን ላይ ... ቀድሞ የ Korea ስም እንደ አሁኑ በ K ሳይሆን በ C ፊደል የሚጀምር እንደነበር ታውቃለህ? ጃፓኖች ቅኝ ግዛት በያዙዋቸው ወቅት በኣለም አቀፍ መድረክ ላይ በሚኖረው አሰላለፍ ... የእንግሊዘኛውን alphabet መሰረት በማድረግ CJ ፊደል ስለሚቀድም ... ቀኝ ተገዢዋ ሀገር Corea ከቀኝ ገዢዋ Japan ፊት እየተጠራችና እየተሰለፈች መቀጠል የለባትም በሚል ሒሳብ ነው ጃፓኖች C ን ከ J ቦኃላ ወደምትመጣው K በመቀየር Korea ተብላ እንድትጠራ ያደረጉት። ይህ ከፈረሱ አፍ የሰማሁት እውነት ነው።

መልካም ሰንብት ... Sarcasm ወንድሜ 8)

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ፋኖ - የኣባቱ ልጅ!

Post by sarcasm » 27 Nov 2023, 19:58

Revelations wrote:
27 Nov 2023, 16:47
አይ ኤዱ የሕወሃት የበኩር ልጅ! ፋኖ አማራ ብቻ ነው ብለው የነገሩሽን ምነው ብትረሺው:: ቅ ቅ ቅ!

ስለ ጥልሽ ማንነት ግን ትንሽ ብትቆፍሪ ትክክለኛ መሰረቱን ታገኚው ነበረ! ወይንም እውነቱን እያወቅሸው ስታብይ ተኝተሻል:: ቅ ቅ ቅ!



ስለ ፋኖ ታሪክ በጣም ትልቅ ነገር ብለሃል። ብዙዎቻችን ጋር ብዙ እውቀት ማነስና እውነትን መጠምዘዝ እንዳለ ይመስለኛል። ኣብዛኞቹ የፋኖ ሚድያዎች ፋኖ የአማራ ብቻ እንደነበር ሲያወሩ፤ አውቀው እያጠፉ ነው ያሉት ወይስ ባለማወቅ ነው፤ እኔ አላውቅም። ቃላት ትርጉማቸው ከግዜ ቦኇላ ይቀይሩ የለ? ፋኖም ትርጉሙ ቀይሮ ይሆን?

ስለ ጥልሽ ግን ምንም አላቅም። ሰሞኑን ከበላይ ዘለቀ ዘውግ ይቀያየሩ ይሆን?

Please wait, video is loading...

Post Reply