Page 1 of 1

ቤት የእግዚአብሄር ነው ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚአብሄር ነው !!!

Posted: 21 Nov 2023, 03:22
by Horus
:lol: :lol: :lol: ኢሬቻን የፈለሰፈው ንጉስ አጼ 480 አመት ኖሮ ሞተ

Re: ቤት የእግዚአብሄር ነው ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚአብሄር ነው !!!

Posted: 21 Nov 2023, 09:01
by Axumezana
እንደ፥ ሀሳዊ፥ ቄስ፥ ግርማ፥ ያሉ፥ የበግ፥ለምድ፥ የለበሱ፥ ተኩላዎች፥ የኢትዮጵያን፥ ታሪክ፥ እንደገና፥ መሰረት፥ በሌለው፥ የፈጠራ፥ ታሪክ፥ ለመፃፍ፥ እየተውተረተሩ፥ ሲሆን፥ አማራ፥ ከሱዳን፥ መጤ፥ መሆኑን፥ አጋንንታዊው፥ አምልኮ፥ እሬቻን፥ የሁሉ፥ ኢትዮጵያውን፥ በአል፥እንደነበር፥ ነግረውን፥ አድዋንና፥ አዲግራትን፥ ለኤርትራ፥ ሰጥተን፥ አሰብን፥ መረከብ፥ አለብን፥ ብለው፥ እየተሳለቁ፥ ነው። እባብን፥ ልቧን፥ አውቆ፥ እግር፥ ነሳት፥ እንደሚባለው፥ ትግራይን፥ ለመበተን፥ እንደማይችሉ፥ ይወቁት።

Re: ቤት የእግዚአብሄር ነው ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚአብሄር ነው !!!

Posted: 21 Nov 2023, 15:21
by Naga Tuma
እግዝኣብሔር ሰዉን ገብረ ካላለ ለምንድነዉ ሰዉ ሰዉን ገብረእግዛብሔር የሚለዉ?

Re: ቤት የእግዚአብሄር ነው ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚአብሄር ነው !!!

Posted: 21 Nov 2023, 15:29
by Kara
Axumezana wrote:
21 Nov 2023, 09:01
እንደ፥ ሀሳዊ፥ ቄስ፥ ግርማ፥ ያሉ፥ የበግ፥ለምድ፥ የለበሱ፥ ተኩላዎች፥ የኢትዮጵያን፥ ታሪክ፥ እንደገና፥ መሰረት፥ በሌለው፥ የፈጠራ፥ ታሪክ፥ ለመፃፍ፥ እየተውተረተሩ፥ ሲሆን፥ አማራ፥ ከሱዳን፥ መጤ፥ መሆኑን፥ አጋንንታዊው፥ አምልኮ፥ እሬቻን፥ የሁሉ፥ ኢትዮጵያውን፥ በአል፥እንደነበር፥ ነግረውን፥ አድዋንና፥ አዲግራትን፥ ለኤርትራ፥ ሰጥተን፥ አሰብን፥ መረከብ፥ አለብን፥ ብለው፥ እየተሳለቁ፥ ነው። እባብን፥ ልቧን፥ አውቆ፥ እግር፥ ነሳት፥ እንደሚባለው፥ ትግራይን፥ ለመበተን፥ እንደማይችሉ፥ ይወቁት።
እንኳን ከዘመነ ወያኔ ወደ ዘመነ ጋላ በሰላም አሸጋገረህ NOW YOU KNOW WHAT WE ARE DEALING WITH :?: :idea:

Re: ቤት የእግዚአብሄር ነው ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚአብሄር ነው !!!

Posted: 22 Nov 2023, 11:59
by Naga Tuma
Kara wrote:
21 Nov 2023, 15:29
Axumezana wrote:
21 Nov 2023, 09:01
እንደ፥ ሀሳዊ፥ ቄስ፥ ግርማ፥ ያሉ፥ የበግ፥ለምድ፥ የለበሱ፥ ተኩላዎች፥ የኢትዮጵያን፥ ታሪክ፥ እንደገና፥ መሰረት፥ በሌለው፥ የፈጠራ፥ ታሪክ፥ ለመፃፍ፥ እየተውተረተሩ፥ ሲሆን፥ አማራ፥ ከሱዳን፥ መጤ፥ መሆኑን፥ አጋንንታዊው፥ አምልኮ፥ እሬቻን፥ የሁሉ፥ ኢትዮጵያውን፥ በአል፥እንደነበር፥ ነግረውን፥ አድዋንና፥ አዲግራትን፥ ለኤርትራ፥ ሰጥተን፥ አሰብን፥ መረከብ፥ አለብን፥ ብለው፥ እየተሳለቁ፥ ነው። እባብን፥ ልቧን፥ አውቆ፥ እግር፥ ነሳት፥ እንደሚባለው፥ ትግራይን፥ ለመበተን፥ እንደማይችሉ፥ ይወቁት።
እንኳን ከዘመነ ወያኔ ወደ ዘመነ ጋላ በሰላም አሸጋገረህ NOW YOU KNOW WHAT WE ARE DEALING WITH :?: :idea:
Are you suggesting that contrary to his now not too old conviction, he has learned that he can live as the same citizen as you in the same country Ethiopia? Or that you had the luxury or willful ignorance to have to deal with that?

Re: ቤት የእግዚአብሄር ነው ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚአብሄር ነው !!!

Posted: 22 Nov 2023, 15:04
by Za-Ilmaknun
Now the "House of Federation" is engaged in reversing high court decisions even when the decison is related to a business agreement entered between a federal agency and citizens.

https://www.ethiopianreporter.com/124234/

ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ የ40/60 ኮንዶሚየኒየም ተመዝጋቢዎች የተወሰነው ፍርድ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተሻረ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ወስኖ የነበረው ፍርድ፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ተሻረ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው የሦስተኛ ዓመት የአንደኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ በወሰነው መሠረት፣ ፍርድ ቤቶች ያስተላለፉትን ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ቤቶች እንዲሰጡ የሚለው ውሳኔ የተወሰኑ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎችን የሚጥሱና ተቀባይነት የላቸውም በማለት በሙሉ ድምፅ ሽሮታል።

በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተፈርሞ ኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተጻፈው ሪፖርተር የተመለከተው ደብዳቤ፣ በ2005 ዓ.ም ወጥቶ የነበረውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የዕጣ ድልድል ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ቅድሚያ የሚሰጠው መመርያ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንደሚያስፈልገው በምክር ቤቱ ታምኖ እንዲታይ ይገልጻል፡፡

‹‹ሕገ መንግሥታዊ የአካታችነትና የፍትሐዊነት መርህን የጣሰ›› ሲል የመመርያውን አንድ አንቀጽ የገለጸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ፣ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቁጠባ ቤቶች ዋነኛ ዓላማ 40 በመቶ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ከባንክ በተመቻቸ 60 በመቶ ክፍያ በመደገፍ እንዲያገኙ ማስቻል እንደሆነ ነው የሚያስረዳው፡፡

ሆኖም አንደኛው የመመርያ አንቀጽ ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የሚያደርግ ሲሆን፣ ይህም ድንጋጌ መግባቱ ‹‹የመመርያውን ግልጽ ዓላማና መንፈስ ያልተከተለ›› ሲል ደብዳቤው ያስረዳል፡፡ ‹‹ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ቅድሚያ መስጠት በመርሐ ግብሩ ለተመዝጋቢዎች እኩል ዕድል ለማሰጠት የታለመውን መሠረታዊ ዓላማ የጣሰ ነው፤›› ሺል ደብዳቤው ያብራራል፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሐ ግብርን የሚያስፈጽመው መመርያ በሰጣቸው መብት መሠረት ሙሉ ለሙሉ የሚጠበቅባቸውን ቁጠባ ከቆጠቡ በኋላ፣ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው የጠበቁ 761 ቆጣቢዎች በዕጣ ማውጣት መርሐ ግብሩ ላይ ቅድሚያ ሳይሰጣቸው 40 በመቶ ከቆጠቡት ጋር እኩል ነበር የተሳተፉት፡፡

ለዚህም ነበር 761 ተመዝጋቢዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝን በመክሰስና እስከ ሰበር ድረስ በመድረስ ሊፈረድላቸው የቻለው፡፡ በፍርድ ቤቶች ተወስኖ የነበረው እየተገነቡ ያሉና ዕጣ ያልወጣላቸውን ቤቶች፣ ከዚህ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ተመዝጋቢዎች እንዲተላለፉ ነበር፡፡

በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ የነበረው የከተማ አስተዳደሩ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ከአንድ ዓመት በፊት ለሕገ መንግሥታዊው ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አቤቱታ አቅርቦ፣ ጉባዔው ጉዳዩን በመመርመር በዚህ ዓመት መስከረም ወር ምክር ቤቱ ሲከፈት ውሳውን አሳልፏል፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መርሐ ግብር ለማስፈጸም ወጥቶ በነበረው መመርያ ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ የሚያሰጠውን አንቀጽ፣ ከመስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹ኢሕገ መንግሥታዊ›› በመባሉ እንደማይሠራ ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርም አውጥቶት የነበረው የዚህ መመርያ ድንጋጌ፣ ደብዳቤው ከደረሰው ከኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ እንዲያሻሽልና ውጤቱን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቅ ያሳስባል፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤውን በግልባጭ ለሁሉም የክልልና የከተማ አስተዳደሮች አሳውቋል፡፡