የፖለቲካ ፊዝ ( Political satire)
Posted: 18 Nov 2023, 02:09
የፖለቲካ ፊዝ ( Political satire) እንደ ፖለቲካ የሰነበተና ያረጀ ነው ፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ ፍዝ እንደ አቃቂር ማውጫ ለመጠቀም ነው እንጂ የፖለቲካ ቦታን አይዝም ፤ ፖለቲካ ሳይንስም ነው ደግሞም ቁም ነገር ነው ፤ አሁን እየገዘፈና እየተቀጣጠለ ያለው ያማራ ትግል የብዙ ዘመናት ግፍ ህልውና ላይ የተጋረጠን አደጋ ለማሰወገድ አስፈላጊውን መስዋትነትን ከፍሎ የኢትዮጵያንም የስርአት ሰብአዊና ፍትሀዊ ወደ ሆነ ማማ ላይ ለማውጣት የሚደረግ ትልቅ ትግል ነው፡ በአብይ የሚመራው በአጠቃላይ የጸረ ሰሜን በተለይ ደግሞ ጸረ አማራ ፖለቲካን አቃሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው ፤ አብይ ለአምስት አመት ሲያራምድ የነበረው ፖለቲካ ኢትዮጵያ እየዘፈነ በአንደኛ ደረጃ የወያኔን ጉልበት ማምከን ነበር ፤ ይህንን ለማድረግ አማራንና ኢርትራን ተጠቅሞ አሳክቷል ፤ አሁን ደግሞ ወያኔዎችን ከጎኑ አድርጎ አምራን ከዚያ ደግሞ ኢርትራን አመክናለሁ ብሎ እየተፍጨረጨረ ነው፤ ይህ አይሳካለትም ነገር ግን የኢትዮጵያ አንጡራ ተጠቅሞ ህዝብ ለመጨፍጨፍ ወደኋላ እንደማይል በቅርቡ በፓርላም ዲስኩሩ በግልጽ ተናግሯል ፡ ስለዚህ ትግሉን ማቅለል አያስፈልግም ፤ ፖለቲካዊ ፌዝ ቦታ ቢኖረውም ፖለቲካ ግን አይደለም ፡ ይህ ነው 360ና ወደ አበበ በላይ ጋር የሚወስደኝ ፡፡ 360ዎች ገና ህዝቡ የአብይን አታላይ ፖለቲካ ሳይገባው እራሳቸውን ነጥለው በመሄድ ብቸኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ልሳን ከሆኑ ቆይተዋል ፤ በአሁኑም ሰአት ትልቅ የኢንፎርሜሽን መስመር በመሆን የአማራ ህዝብ ትግል ድምጽ ሆነዋል ፤ በዚህም ሊመስገኑ ይገባል ፤ ነገር ግን 360 ሀብታሙም ሆነ አበበ በለው ማወቅ ያለባቸው የሚከሄደውን የህዝብ ትግል ለመርዳት በጠላት ላይ ድራማ በመስራትና በማጣጣልና ፤ የአማራ ድልን በአግባቡ እንደመግለጽ የብርሀኑ ጅላን ፤ የአብይን ስም እያነሱ የሰፈር መበሻሽቅ አይነት ፖለቲካ ውስጥ መግባት የለባቸውም ፤ ትግሉን የሚረዳውም አይደለም ፤ ዜናዎች እና ትንተናዎች ትክክለኛና የሚከፈለውን መስዋእትነት ትክክለኛ ግንዛቤ በሚሰጥ መልኩ መሆን አለበት ፤ ኮመዲውን ለኮሜድያን መስጠት ያስፈልጋል ፤ የፖለቲካ ፊዝ መድረክ ስጥቶ ማስተናገድ ይቻላል ፤ ነገር ግን ዩቲዩቡን ከዳር እሰክዳር በሳቅ ሞሙላት ( ሀሳቡ የጠላትን ሞራል ለመጉዳት ቢሆንም ) ሲበዛ ግን ትግሉ እየከፈለ ያለውን ወደፊት የሚከፍለውንም ሚዛንና ግንዛቤ ያሳጠዋል ፤ መሳይ መኮንን በዚህ በኩል የዜና አቀራረቡ ፤ የሚያቀርባቸው ትንተናዎች ፤ የሚጋብዛቸው ፖለቲከኝች እንዲሁን የሚያደርገው አግባብ ያለው አእምሮን በሚፈትን መልኩ የሚቀርቡ ትያቄዎች ሞያዊ ተክህኖ ያላቸው ናቸው ፤ በዚህ ላይ በአማራ የሚገኝ ድሎችን በአግባቡ የሚዘግብበት መንገድ ጋዜጠኝነት በምን አይነት እውቀት መያዝ እንዳለበት የሚያሳዩ ናቸው ፤ አሁንም ሀብታሙና አበበ ለትግሉ እያደረጉትን አስተዋጾ አሁንም የሚያደርጉትን በማደነቅ ነው፡ ወደፊትም ትልቅ አስተዋጾ ያደርጋለው ዋናው ቁም ነገር የፖለቲካ ሳታየርና ፓለቲክ የተለያዩ ስለሆነ ሁለቱን ደባልቀን አሳሳች ግንዛቤ እንዳይኖረን እንጣር ነው ፡፡