Page 1 of 1

⇝⇝ What Happened 3 Days Before The Algiers Agreement Was Signed ❓❓❓

Posted: 10 Nov 2023, 10:40
by Fiyameta
What many people don't know is that..... the Algiers agreement that was signed on December 12, 2000, at Algiers, Algeria, was initially scheduled to be signed 3 days prior on December 9, 2020. And the reason being.....

The 3 day delay was requested by the TPLF who knew beforehand that, one the agreements were signed, the border commission's decision would not be in their favor, so they wanted those 3 days to make a last ditch effort to capture the Eritrean port of Assab hoping to gain an upper hand in the Algiers' negotiations. Did the plan work?

The then TPLF's commanding General Bacha Debele have since described the events of those 3 days of war at the Assab front as "ተጨፈጨፍን". That pretty much sums it up, and there's nothing more to add to that.


:shock: :shock:

ወያኔ አሰብን ለመያዝ ያደፋፈረው ዋናው ምክንያት፤

"ጠላት በቡሬ ግንባር እንጠቃለን ብሎ ስለማይገምት በቂ ዝግጅት አይኖረውም። ከጅቡቲ መንግስት ጋር ስለተነጋግርን ሃይላችን በቀላሉ በጅቡቲ መሬት ማስጠጋት ለዉጊያም ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንችላለን" የሚል ነበር።

በዚሁ መነሻና ገለጻ ላይ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር። ለምሳሌ የ36ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል መሃመድ ኢሻ፣ የ39ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ወንደሰን ተካ፣ የ14ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ወዲ አባተ ያነሱት ጥያቄ፣

"እስካሁን ባደረግናቸው ዉጊያዎች ሁሉ ሻእቢያን ከያዘው ምሽግ እንዲያፈገፍግ አደረግነው እንጂ፣ በእቅዳችን ያስቀመጥነውን ተግባራዊ አላደረግንም። ለዚህም ብዙ ኪሳራ ከፍለንበታል። በኪሳራው ምክንያትም የጦሩ ሞራል መጥፎ ሁኔታ ይገኛል። የቡሬ አየር ጠባይም ሆነ መሬቱ በጣም አስቸጋሪ ነው። በቂ የሎጂስቲክ ዝግጅት የለንም። ድንገተኛ ድል እናገኛለን ብለን ድንገተኛ ሽንፈትም ሊከተል ይችላልና ቢታሰብበት? ስለ ጠላት እስካሁን የተናገራችሁት ሁሉ ልክ አልሆነም። እና አሁንስ ምን ያህል ትክክል ናችሁ?" የሚል ጥያቄ አንስተው ውይይት አደረግን።

በመጨረሻ አሳማኝ ነጥቦች ባይቀርቡም፣ የማይቀየር የመንግስት ዉሳኔ ነው ተብሎ "አሰብን መያዝ!" የሚለው እቅድ ፀደቀና ዉጊያው ተካሄደ።

የቡሬ ግንባር ላይ ታደሰ ወረደ ተመደበ። የተሰጠው ትእዛዝ አሰብን ከያዘ በሁዋላ የቀይ ባህርን ዳርቻዎች እያጠቃ፣ ምፅዋን እንዲቆጣጠርና እዚያው ሆኖ ቀጣዩን ግዳጅ እንዲጠባበቅ ነበር።

ዉጊያው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ቢሆንም፣ እንዲያዉም ከሌሎች ዉጊያዎች ሁሉ የከፋ ዉጊያ ሆነ። ሻእቢያ በበርካታ ዉጊያዎች የሚጠቀምበትን ወደ መግደያ ቦታ እያስገባ የመምታቱን ስልት ቡሬ ላይም ስለ ደገመው ከፍተኛ እልቂት ተቀብለን አሰብን የመያዙ እቅድ ከሸፈ....