ድሮ አጼ ምኒልክ ወደ ወላይታና ደቡብ ሲዘምቱ ሰራዊታቸው ይከትምበት ከነበሩት የሶዶ ጉራጌ ቦታዎች ውስጥ ቆንዳልቲቲ እና ኬላ የታወቁት ናቸው ። ሌሎችም አሉ።
እኔ ልጅ ሆኜ እዚህ አካባቢ ታዋቂ የነበረው የሱተን ሰኞ ገበያ ነበር። በኬላ መውረጃ ያሉት ተራሮች በዝንጀሮ የተሞላ ስለነበር በጣም ያስቸግሩ ነበር።
ዛሬ ኬላ ከተማ ለመሆን እየታተረች ነው ። ይህ ቪዲዮ የከተማው ቅዳሜ ገበያ እለት ነው ።
አጼ ምኒልክ ድንኳን የጣሉበት ቦታ ተከቦ ይታያል፣ የምኒልክ ሰፈር ይባላ! አጠገቡ የአጼ ምኒልክ ጠጅ ቤት ይታያል! ጉድ ነው!!!