እንደ ሚታወቀው ጨፌ የኦሮሚያ ክልል መስብሰቢያ አዳራሽ ነው። ነገር ግን ለምንድን ነው ይህን ቃል መጠቀም የፈለጉት? በእኔ ግምት ይህ የነሱ ባህላዊ መሰብሰቢያ ሜዳ ጋር አንድ ለማድረግ ይመስላል ። ነገር ግን ለምንድን ነው መሰብሰቢያ ሜዳን የሚያመለክት የኦሮምኛ ቃል ያልተጠቀሙት? ምናልባት ጨፌ የተዋሱት የሴም ቃል መሆኑን ዘንግተው ይሆናል ።
ኦሮሞች ጨፌ የሚሉት ቃል የሴም ሕዝቦች ጨፋ ይሉታል ። ቃሉ ከጥንታዊት የፊኒቄ (ፊኒሺያዊ) ሕዝቦች ጀምሮ በሁሉም የሴም ቋንቋዎች ውስጥ በሰፌው ጥቅም ላይ ያለ አልፎ ተርፎም በኢንዶ ኢሮፒያን ስረ ቃላት ያለ ነው ።
በአንድ ቃል ጨፋ ማለት ከእጅ መዳፍ ጀምሮ ማንኛውም ጠፍጣፋ ነገር መግለጫ ቃል ሲሆን ጨፋ ለጥ ያለ ሜዳ ማለት ነው ። ፍላት ነገር ሁሉ ጨፋ ነው ። ለምሳሌ ጠፍጣፋ፣ ሳፋ ሳህን፣ የምግብ ማቅረቢያ ጣባ፣ ጥፍጥፍ ቂጣ፣ ቻፓታ የሚባለው ጠፍጣፋ ዳቦ፣ እያለ ብዙ ብዙ አግባቦች ያሉት እጅግ ጥንታዊ የሴም ቃል ነው ጨፋ ማለት ። ዛሬ ሜዳን ጨፋ ብለው የሚጠሩት ጉራጌዎች ናቸው ።
ጨፋ በጉራጌ ከብት ማገጃ፣ ፈረስ መጋለቢያ፣ ገና መጫወቻ ፣ የጥምቀት ታቦት ማውጫ ለመሳሰሉ ሕዝባዊ ትዕይንቶ እንጂ ለሽምግልና፣ ለገር ጎርደና፣ ለጉባኤ መሰብሰቢያ ቦታ አይደለም ። ጨፋ ትልቅ ለጥ ያለ ጠፍጣፋ ሜዳ ነው ።
ይህን ጉዳይ እዚህ የማሳየው ኦሮሞች ከሴም ቋንቋ ለምን ተዋሱ ለማለት አይደለም፤ ሕዝቦች አንድን ባህልም ሆነ ቴክኖሎጂ ከሌላ ሕዝብ ይዋሳሉ ። ነገር ግን ያን የተዋስነው ቃልም ሆነ ባህል በሃቀኝነትና በማመስገን መዋሳችንን መግለጽ ያንድ ሕዝብ መልካም ካራክተር ነው ።
የሌሎችን ቋንቋና ባህል ወስዶ እንደ ራስ መቁጠር ብቻ ሳይሆን የተዋሱትን ባህል ትርጉም ሳያውቁ የተለየ ለመምሰል መሞከር ብሎም በተዋሱት ባህል ላይ ጥላቻን መፍጠር የቆሙበትን ምንጣፍ እንደ መጎተት ይቆጠራል ።
ለማንኛውም ጨፌ ድብን ያለ የሴም ቃል እንጂ ኦሮሞኛ እንዳልሆነ እንዲታወቅ ነው ።
ሆረስ ኃይለ ብርሃን