Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42649
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የዲክታተሩ ፍጹም ችግር

Post by Horus » 26 Oct 2023, 00:36

በእኔ ግምት አቢይ አህመድ የዲክታተሩ የመጨረሻ መፍትሄ አልባ ችግር ላይ ይመስለኛል ።

ኒኮሎ ማኪያቬሊ የሜዲችን መስፍን ሲያማክር (ያቢይ አማካሪ ሌንጮ ማለት ነው) መስፍኑ የጠየቀው ነገር ትዝ አለኝ ። መስፍኑ ይጠይቃል፤ ' ኒኮሎ ግዛቴ እንዲሳካልኝ ብወደድ ነው የሚሻለው ወይስ ብፈራ?' ይለዋል ። ኒኮሎ ይመልሳል፤ 'መስፍን ሆይ ቢቻል ፣ ቢቻል ብትወደድ፣ ያ ካልሆነ መፈራት አለብህ' አለው።

የዛሬው አቢይ አህመድን ያስጨነቀው ይህ ጥያቄ ነው ። ሰውዬው እንኳንስ በሕዝቡ በራሱ ታዛዥ አሽከሮች አይወደድም፣ በፍጹም። ያ ካልሆነ ደሞ በሕዝቡም ሆነ በአሽከሮቹ መፈራት አለበት ። ዛሬ ላይ የአማራ ሕዝብ ባስነሳው አቢይን አለመፍራት አገር አቀፍ መንፈስ ሳቢያ አቢይ በህዝቡ አይፈራም ለማለት ይቻላል። አሁን የቀሩት የራሱ ተቀጣሪ አሽከሮች ናቸው ።

ጥታቄ፤ ስንቶቹ የብልጽግና አሽከሮቹ ሰውዬውን ይፈሩታል (ማለትም ፈርተው ትዕዛዝ ይፈጽማሉ?) አቢይን እንዲህ እንደ ህጻን የሚያነጫንጨውና እንደ ዱርዬ አሽከሮቹን በስድብ የሚያዋርዳቸው የማይፈሩት አሽከሮች ቁጥር ስለበረከተ ነው ። ይህ ቁልፍ ሁኔታ ነው ።

ከዚህ በኋላ አንድም አሽከር በሙሉ ልብ ትዕዛዝ አይፈጽምም ። ሁሉም በመባረር ፣ በመዋረድ ፣ ወይም በመቀጣት ፍርሃት ውስጥ ስላሉ ማለት ነው። ዲክታተሩ በራሱ አሽከሮች አለመፈራትን በገንዘብ ኃይል በጉቦና ማማለል ሊፈታው አይችልም ። ገንዘብ የሚሰጠው ለመወደድ ነው፣ አሽከሮቹ የሚፈሩት ሲቀጣቸው ነው።

በአንድ ቃል ዲክታተሩ ሊፈታው የማይችለው ችግር ላይ ደርሷል ። አሁን እየገዛ ያለው በማስፈራራት ነው ። እስከ መቼ?

ነገና ከነገ ወዲያ ሰዉ ተገድዶ ሰልፍ እንዲወጣ ይደረጋል፤ በዚያ ሰልፍ ውስጥ የምናየው የሕዝቡ ስሜት ሃቁን ይነግረናል ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42649
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የዲክታተሩ ፍጹም ችግር

Post by Horus » 26 Oct 2023, 01:43


Post Reply