Page 1 of 1

የስነ መንግስት ሕገ ፍትህ እና ፍኖተ ርትዕ!

Posted: 18 Oct 2023, 01:24
by Horus
እያንዳንዱ ግለሰብ ከሌላው ግለሰብ እኩል ፍጡር ስለሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ እኩል መብት፣ ነጻነትና ሃይል አለው ። ይህን ፍጹም መሰረታዊ የስነ ፖለቲካና ስነ መንግስት ሕግ የማይቀበል የሕዝብ መሪ የአገር አስተዳዳሪ የመሆን ምንም አይነት ብቃት የለውም ። ከማንኛውም ያገርና ሕዝብ አስተዳደር ሃላፊነት መወገድ አለበት ።

የአንድ አገርም ሆነ ማንኛውም ማህበራዊ ድርጅት የግለሰቦች ፖለቲካዊና ሕጋዊ እኩልነት የአንድ ስነ መንግስትና ስነ ስርዓር የመጨረሻው የማይጣስ የፍትህ ዶግማ ነው ። በፍትህ ዶግማ ላይ ያልተመሰረተ ስነ መንግስት የግፍና የሕገ አራዊት ስርዓት ነው ። ነጻ ሕዝብ ይህን በመሰለ ስነ መንግስት ውስጥ በፍጹም መኖር ወይም ይህን ለሰው ልጆች የማይመጥን አገዛዝ እምቢ ማለት የተፈጥሮ መብትና ግዴታቸው ነው ።

ፍትህ በሌለበት ሁሉ ግፍ አለ ።

ሌላው ከፍትህ ቀጥሎ ያለው የማንኛውም ስነ ፖለቲካና ስነ መንግስት የማይጣስ ዶግማ ፖለቲካዊ ፍኖተ ርትዕ ነው። በዘመናችን መልካም አስተዳደር (good governance) የተባለው ጽንስ በፖለቲካ ደላሎችና ዲክታተሮች የረከሰ ቃል ቢሆንም በትክክለኛ ኦሪታዊ (ኦሪጂናል) ትርጉሙ የስነ መንግስት ፍኖተ ር ት ዕ ማለት ነው ። ርትዕ እውነት፣ እውነተኛ ማለት ሲሆን ሌላ ትርጉሙ ጥሩ፣ መልካም፣ ያልቆሸሸ፣ በውሸት፣ በሙስና፣ በግፍና ብልግና ያላደፈ ንጹህ ማለት ነው ።

ስለሆነም የስነ መንግስት፣ የስርዓተ አስተዳደር የእውነት መንገድ ምን እንደ ሆነ የማያውቅና ይህን የሚጥስ የሚገድፍ የስነ መንግስት ፍኖተ ርትዕ የማይከተል የሰዎች መሪ ሊሆን አይችልም ። በታሪክ አጋጣሚና አደጋ የመንግስት ስልጣን ይዞ ከሆነም አንድም በሰላም ካልሆነም በጉልበት ከስልጣኑ መወገድ አለበት ። አንድ የነጻ ሕዝብ ሌላ የተፈጥሮ ምብትና ግዴታ ይህን የመሰለ ውሸተኛና ባለጌ የመሪነት አስመሳዮችን ማስወገድ ነው ።

ርትዕ በሌለበት ሁሉ ሌብነት አለ።

ከፍትህና ርትዕ በተጨማሪ ያሉት ዝባዝንኬዎች ሁሉ ዝም ብሎ የስርዓቱ አሸክታቦች ናቸው ።

ሆረስ ዐይነ ብርሃን

Re: የስነ መንግስት ሕገ ፍትህ እና ፍኖተ ርትዕ!

Posted: 18 Oct 2023, 01:40
by TesfaNews

Re: የስነ መንግስት ሕገ ፍትህ እና ፍኖተ ርትዕ!

Posted: 18 Oct 2023, 01:52
by Horus
TesfaNews wrote:
18 Oct 2023, 01:40
TesfaNews - thanks.

ይቺትልህ አበባ ደሳለኝ ሌላዋ ሂሩት በቀለ ከብዙ አመታት በፊት በሚሊኒየም አዳራሽ!

Re: የስነ መንግስት ሕገ ፍትህ እና ፍኖተ ርትዕ!

Posted: 18 Oct 2023, 02:15
by Horus

Re: የስነ መንግስት ሕገ ፍትህ እና ፍኖተ ርትዕ!

Posted: 18 Oct 2023, 04:08
by TesfaNews
Horus wrote:
18 Oct 2023, 02:15




WEEY GUUD!


Re: የስነ መንግስት ሕገ ፍትህ እና ፍኖተ ርትዕ!

Posted: 18 Oct 2023, 13:37
by Horus
ተስፋኒውስ፣
የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ ድራማ ፌክ ነው ። የሚዲያ ሽፋን በመቆጣጠር ጸጥ ብለው አማራን እንደ ትግሬ ለማውደምና እስትራተጂካሊ ለማዳከም ነው እንጂ እንኳን ኤርትራ ፈስ ለመዋጋት የሚችል ጦር የለውም አቶ አቢይ !

ኤርትራዊያን አንድ መሳሳት የሌለባቸው ነገር አለ ፤ አቢይን እንጂ ኢትዮያን እንደ አገር ሕዝብ ከመስደብና ከማስቆጣት መጠንቀቅና አቢይን ለማስወደግ ለሚታገለው ሕዝብ የቻሉትን ድጋፍ ማድረግ ነው ።

ይህ የኦሮሞች አጀንዳ ነው፣ የዚያ አጀንዳ ትራፕ ወጥመድ ውስጥ እንዳትገቡ። ይህ ጫጫታ ሁሉ በቅርቡ ጸጥ ይላል !