ሰለሞን ካሳ ባዘጋጀው ኢንተርቪው ላይ፣ ወንፊቱ ዓብይ አምስትና ስድስት በአለም ተፅዕኖ የፈጠሩ ስዎችን ጠቅሶ፣ የኮሌጅን ዲግሪ ፋይዳነት በድፍረት ሲያጣጥል ሰምቼ፣ ይሄ ሰው ምን ዓይነት ንፍጣምና ፅንፈኛ እንደሆነ ገባኝ። እንዴ እነ አይዛክ ኒውተን (Issac Newton)፣ ሜሪ ኩሪ (Marie Curie)፣ ቻርለስ ዳርዊን (Charles Darwin)፣ ጄምስ ዋትሰን
(James Watson)፣ ጄምስ ዋት (James Watt)፣ ካርል ቤንዝ (Karl Benz)፣ ሁጎ ጄንከርስ (Hugo Junkers)፣ ግሬስ ሆፐር (Grace Hopper)፣ ሎዊ ፓስተር (Louis Pasteur)፣ ቲም በርነርስ-ሊ (Tim Berners-Lee)፣ ጃመስ ዴይሰን ((James Dyson)፣ ሼርሊ ጃክሰን (Shirley Jackson)፣ ማርቲን ሉትር (Matin Luther)፣ ማርቲን ሉትር ኪንግ (Martin Luther King)፣ ኔልሰን ማንዴላ (Nelson Mandela) ፣ ማሃትማ ጋንዲ (Mahatma Gandhi) ወዘተ እኮ እስከ ዶክትሬት የተማሩና ዓለምን የለወጡ ታላላቅ የከፍተኛ ትምህርት ውጤቶች ናቸው።
ነገሮችን በራሱ ዱቄታም የትምህርት ውጤትና ፅንፈኛ መነፅር ስለሚመለከተው፣ ሁሉንም ሳይንቲስቶች ሰብስቦ አንድ ትንሽ የአስተሳሰብ ቋት ዉስጥ ከተታቸው። ይኼ የመነጨው ደግሞ ከጠባብነትና ድንቁርና አስተሳሰብ ነው። አማራዎች እንደዚህ ናቸው፣ ኦሮሞዎች እንደዚያ ናቸው፣ ትግሬዎች አመላቸው እንደዚህ ነው፣ የጉራጌዎች ደግሞ እንደዚያ ነው በማለት ህዝቦችን በአንድ ላይ ለመፈረጅ ከሚደረገው የፅንፈኞችና የድውዮች አስተሳሰብ ጋር የተያያዘ ነው። ዓብይ ስዎችን በአንድነት ከሚፈርጁትና ከምጠየፋቸው እርኩሶችና መሃይሞች አንዱ ነው።