Fasil Yenealem
"ጃርቶች ከጮሁ እዛ አካባቢ ምርት አለ ማለት ነው " ይላል ዲያቆን ዳንዔል ክብረት:: አንድ ተራ ሰው እንዲህ ቢል አይገርመኝም:: አንድ የሃይማኖት ሰው ነኝ የሚል እንዲህ ሲል ግን የውድቀታችንንና የኪሳራችንን ደረጃ ያሳያል:: እንዴት በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረው የሰው ልጅ ሞት እንደ ምርት ይታያል? አገዛዙ በምን አይነት ጨካኝ ሰዎች ነው የተሞላው ? ነው ወይስ ስልጣን ሰውን ሁሉ ጨካኝ ያደርጋል? እንዲህ አይነቱ ንግግር የሰውን ልጅ በበረሮ መስለው ጭፍጨፋ ከፈፀሙት ሁቱዎች በምን ይለያል?
ዳንዔል እያለ ያለው እኮ የአማራ ህዝብ ሰው ሳይሆን ጃርት ነው ነው:: እየገደልክ ከምረው እያለ ነው:: በእርሱ አይን የሰው አስከሬን ምርት ነው:: ለነገሩ አልፈርድበትም : ባለፉት አምስት ዓመታት የእርሱ መንግሥት ያመረተው ትልቁ ምርት የሰው እልቂት ነውና::
Re: ዳንኤል ክብረት: የአማራ ሕዝብ ሰው ሳይሆን ጃርት ነው
ዳንኤል ክብረት በመላው የአማራ ክልል ላይ በሄሌኮፕተር ፀበል መረጨት አለበት እያለ ነው :: ይሄ መፍትሔ ነው ትላላችሁ ?