Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

እንሾሽላ፤ በጉራጌ ሴት ያላትን ክብር መለኪያ ባህል!

Post by Horus » 11 Sep 2023, 02:02

ዛሬ ላይ ከማኛውም እጅግ ብዙ የጉራጌ ባህላት ምናልባት ከመስቀል ባህል ቀጥሎ ጉራጌን ከዳር እስከ ዳር አይደለም ኢትዮጵያ በመላ አለም እንደ ሱናሚ እንደ ሰደድ እሳት የሰፈነ ባህል ቢኖር እንሾሽላ ነው። ዛሬ እንሾሽላ እራሱ የሰርግ በዓልን እየበለጠው ይገኛል ።

ይህ ባህል ደሮ የልጃገረድ፣ የሙሽሪት ባህል ብቻ ነበር ። አሁን ወንዱ ሙሽራም ሴቷን መፎካከር ጀምሯል ።

ድሮ ድሮ አንዲት ልጃገረድ ከሰርጓ አንድ ወር በፊት ጥፍሯ ይቆረጥ ነበር ። ለምን የሚለው ብዙ ታሪክ አለው፣ እዚያ አልገባም ።

ከዚያም ለ1 ወር ማታ ማታ ሚዜዎችና ጓገኞችዋ ቤቷ እየዘፈኑ የጥፍር ግብዣ ይበላ ነበር ። ዘመዶቿ የሆኑ ሁሉ ምግብ እየደገሱ ያመጡና በየማታው የጥፍር ይዘፈን ይበላ ነበር ።

ከዚያም ሰርጓ እሁድ ሆኖ 3 ቀን በፊት እጅና እግሮቹዋ ላይ እንሾሽላ የሚታሰርላት እለት ነበር ። ያ እለት መላ ዘመድ አዝማዶችዋ ቤቷ ተሰብስበው የእንሾሽላ የቤተሰብ መሰነባበቻ በዓል ተደርጎላት እንሶስላ ይታሰርላት ነበር ። ቀኑ በጣም ሆድ የሚያባባ መሰነባበቻ የነበረ ሲሆን ዘፈን የሚያወርዱላት እናቷ፣ አባቷ፣ አያቶቿ ና አስክስቶቿ ነበሩ ።

ይህ ባህል ቀዝቀዝ ብሎ ከኖረ በኋላ ባለፉት 15 አመታት እጅግ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ የገነነ መላ ጉራጌን ክርስቲያን ሙስሊም ሳይል ስልቴን ጨምሮ የጉራጌ ልጃገረዶች እየነቀነቀ ይገኛል ።

በዚህ ልክ የመግነኑ ምክኛት ሴቶችን እጅክ ከፍ የሚያደርግ፣ የዘር ግንድ ፣ የቤተሰብ ጌታ መሆናቸውን ስለሚያገን ነው ።

ዛሬ ላይ እንሾሽላ ላንዲት ሙሽራ ከሰርጓል በላይ ያማረ ነገር እየሆነ ነው!

ይህ ባህል ወደፊት የሌሎች ብሄረ ሰብ ልጃገረዶች እያማሩበት ቢመጡ አልደነቅም!

በዚህ የአዲስ አመት ዋዜማ እንሾሽላን አስተዋውቃችኋለሁ !

የኬር አክራሚ ለኩልምኛ !!!




Last edited by Horus on 11 Sep 2023, 03:15, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንሾሽላ፤ የጉራጌ ሴት ያላት ክብር መለኪያ ባህል!

Post by Horus » 11 Sep 2023, 02:20



እጅግ የሚገርመው ይህ የጴንጤዎች እንሾሽላ ነው ! ዘፈኑ መዝሙር ነው


Post Reply