አብይ አህመድን በዘጠኝ ሚዛኖች፤ ከቁጣ እስከ ሀሳዊ መሲህነት! By Dr Mesganaw Andualem
Posted: 10 Sep 2023, 07:57
አብይ አህመድን በዘጠኝ ሚዛኖች፤ ከቁጣ እስከ ሀሳዊ መሲህነት!
By Dr Mesganaw Andualem
*
1) አብይ አህመድ እንደሰው
የመደበኛ ሰው ባህርይ አይታይበትም፡፡ መደበኛው ሰው ያዝናል፤ በተለይ በራሱ ጥፋት በሚከሰት ችግር ያዝናል፡፡ ይሄ ሰውየ ግን የሀዘን ስሜት የለውም፡፡ አምስት አመት ሙሉ እንደታየው አንድ ቀን አዝኖ እና ተክዞ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ይልቅም ሁልጊዜ እንደሳቀና እንዳላገጠ ነው የሚታየው፡፡ በርሱ ችግር ከ 1.5 እስከ 2 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ሞቷል፤ እስከ 8 ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቅሏል፤ ከ20 ሚሊዮን በላይ በረሀብ እየተሰቃየ ይገኛል፤ አብዛኛው የአገሪቱ ህዝብ የረሀብ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡ ነገር ግን አብይን አያሳስበውም፡፡ በየሄደበት ፌሽስታ፣ ሳቅ እና ግልፈጣ ነው፡፡ ይሄ ባህርይው ከመደበኛው የሰው ልጅ ባህርይ የወጣ ያደርገዋል፡፡
2) አብይ እንደ ጥቃቅን ብልጠቶች ባለቤት
መሰረታዊ የሆነ የማገናዘብ እና የመተንተን ችግር አለበት፡፡ ትናንሽ እና ለእሱም ለህዝቡም የማይጠቅሙ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ አገር አመራር ማለት ህጻናት እርስ በርስ እንደሚሸዋወዱት፤ ወይም እንደሚበሻሸቁት ተራ ነገር አድርጎ ይቆጥራል፡፡ ሰውነት ማለት ተንኮልና ሼር ብቻ ነው ብሎ ያስባል፡፡ አርቆ ማሰብና ታጋሽነት ባህርይ አይታዩበትም፡፡
3) አብይ እንደ በቀለኛ
አብይ ቂመኛና ቁጡ እንደሆነ የተቸውን ግለሰብ ሁሉ አስሮ የሚያሰቃይ መሆኑ ምስክር ነው፡፡ በመሪነቱ የሚመጣበትን ትችት እንደ ግል ጥቃት የሚቆጥር ደካማ ባህርይ ያሳያል፡፡ በቀለኛነት ደግሞ በበቂ ሁኔታ ያለማደግ ምልክት ነው፡፡ ሆደሰፊነት በተፈጥሮ የሚገኝ ቢሆንም በመማርም ይበልጽጋል፡፡ አብይ በሁለቱም መንገድ ይሄን ባህርይ አላገኘም፡፡
4) አብይ እንደ መሪ
በራሱ የአመራር ችግር ሳቢያ አምስት አመት ሙሉ ህዝብ ላይ እሳት ሲያዘንብ አንድም ቀን ሀላፊነት ወስዶ አያውቅም፤ ይቅርታም ጠይቆ አያውቅም፣ የተጎዱ ሰዎችን ጎብኝቶ አያውቅም፣ ስለተጎዱ ሰዎች አዝኖ አያውቅም፣ ምንም አይነት ችግር የመፍታት ምልክት አሳይቶ አያውቅም፣ ጥፋቱን ለማረም ዝንባሌ አሳይቶ አያውቅም፤ የያዘውን ስልጣን ህዝብ ለመጥቀም ሳይሆን ለመጉዳት ይጠቀምበታል፤ የያዘውን ስልጣን የግል ንብረት ብቻ አድርጎ ይቆጥራል፣ እስካሁን በፈጠረው ችግር ምክንያት ከስልጣን መውረድ ቢኖርበትም አላደረገውም፤ ስልጣንን ይወዳል፣ ነገር ግን ከስልጣን ጋር የሚመጣውን ሀላፊነት ለመቀበል ዝግጁ አይደለም፡፡ ባጭሩ ምንም አይነት የመሪነት ባህርይ አሳይቶ አያውቅም፡፡ አገር አመራር እንኳን ከታሪክ ከልጅነቱ ጀምሮ ካገለገለው ወያኔ አልተማረም፡፡ ክፉው ወያኔ የተሻለ እንደነበር እንድናስብ ያደረገን አብይ ምን ያህል የዘቀጠ ቢሆን ነው?!
5) አብይ እንደ ጸረ ኢትዮጵያ
አብይ ጸረ ኢትዮጵያ ነው፡፡ ጸረ ኢትዮጵያነቱን ደግሞ ሆነ በሎ በማወቅ የሚሰራው ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ምሰሶ የሆኑ ጉዳዮችን ሲያፈራርስ አገሪቷን እንደሚጠላት ማሳያ ነው፡፡ በወያኔ ቤት ማደጉ ለዚህ አስተዋጾ ማድረጉ አልቀረም፡፡ በተለይ ግን የኦነግ ጸረ ኢትዮጵያ አስተሳሰብ አራማጅ መሆኑ በጸረ ኢትዮጵያነት እንዲሰለፍ አድርጎታል፡፡
6) አብይ እንደ ጸረ አቢሲኒያ
ኦነግ የተፈጠረው ከታሪክ በመጣላት መሆኑ ይታወቃል፡፡ አቢሲኒያ ወይም አበሻ ብለው የሚያስቡት በዋነኝነት አማራ/አገው፣ ትግሬ፣ አፋርና ጉራጌን ነው፡፡ አብይም ስልጣን በያዘ ሳምንት ነበር በዚህ አካባቢ ላይ ሳይውል ሳያድር ማሴር የጀመረው፡፡ ያሰበውንም አሳክቷል፡፡ ኦነግ አበሻ የሚላትን ጠላት የተባለች አበሻ አካባቢና ህዝብ አውድሟል፤ ህዝቡን በገፍ አፈናቅሏል፤ በወረራ ንብረቱን ሁሉ አውድሟል፤ ምድር ላይ ያለን ግፍ ሁሉ እየፈጸመበት ይገኛል፡፡ መሪ ከሆነ ጀምሮ እስካሁን ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ አበሻን ሞራሉን ይነኩልኛል፤ መሰረቱን ይንዱልኛል ያላቸውን ነው፡፡ ይሄ ስራው አብይን የኦነግ አስተሳሰብ ቁንጮ ወኪል ያደርገዋል፡፡
7) አብይ እንደ ጨካኝ መሪ
መጀመሪያ አካባቢ ስልጣን ላይ እንደወጣ አንዱ ወንድማችን “አብይ ዝቅ ሲል መለስ፣ ከፍ ሲል ሂትለር ነው” ብሎታል፡፡ ክፋትና ጠማምነትን ከመለስ፣ ጭካኔን ከሂትለር ወስዷል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አብይ ያለ ጨካኝ መሪ ተከስቶ አያውቅም፡፡ የሁሉም ያለፉት መሪዎች ጭከና ቢደመር እንኳ የአብይን ሩቡን አያክልም፡፡ ለዚህም የታሪክ ሰነዶች ዋቢ ናቸው፡፡ ለሚጨፈጭፋቸው ሰዎች “ለአስከሬናቸው ዛፍ ጥላ እንትከልላቸው” ብሎ ለማላገጥ ምላሱ የታዘዘለት ብቸኛው መሪ አብይ ነው፡፡ በተግባር ለስልጣኑም ሆነ ለምኑም ስጋት ያልሆኑትን በጅምላ በመጨፍጨፍ አጠገቡ የሚደርስ መሪ አልተገኘም፡፡ መሪነት ማለት ጨካኝነት ነው ብሎ እንደሚያምን ስራው ምስክር ነው፡፡
) አብይ እንደ ‘ሮቦት’
ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ስናይ አብይ የኢትዮጵያ ጠላት አገር ኢትዮጵያዊ አስመስሎ የሰራው ሮቦት ይመስላል፡፡ ይሄ ሁሉጊዜም ምንም አይነት የሀዘን ስሜት አሳይቶ ስለማያውቅ ስሜት አልባ ሮቦት እንደሆነ ነው የሚታየኝ፡፡ ወደስልጣን ሲመጣም እየፈገገ፣ ህዝብ እያስጨረሰም እንደፈገገ አለ፡፡ የተለየ ስሜት አሳየ ከተባለም ቁጣ ነው፡፡ ሰው የሰራው ማሽን በመሆኑ ሳቅና ቁጣ የተባሉትን ስሜቶች ብቻ ነው የሰሩለት፡፡ ሀዘኔታ፣ ርህራሄ፣ ጸጸት የመሳሰሉትን ስሜቶች አልሰሩለትም፡፡ በዚህም ይሄ ሰው በእውነት ሰው መሆኑን እንድጠራጠር ያደርገኛል፡፡ ብቻ ሮቦት መሆኑ ቢያከራክርም ሀዘኔታ፣ ጸጸት፣ ርህራሄ የመሳሰሉት ባህርያት የሌሉት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
9) አብይ እንደ ሀሳዊው ክርስቶስ
በመጽሀፍ ቅዱስ የተገለጸው ዋናው ጸረ ክርስቶስ አስመሳይ ነው፡፡ ለሰባት አመት ከተለያዩ ሀይሎች/አገሮች ጋር የሰላም ስምምነት ይፈርማል፡፡ ሰላም አመጣ ተብሎ የሚወደድና የሚወደስ ነው፡፡ ሶስት አመት ተኩል ሲሆን ግን የፈረመውን ውል አፍርሶ በዋና ባህርይው ይገለጥና አምልኩኝ እስከማለት ይደርሳል፡፡ ይህ አውሬው እየተባለ የሚገለጸው የመጨረሻው ዘመን መሪ በመጀመሪያ አለምን በማሳሳት የራሱ ተከታይ ያደርጋል፡፡ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስት ድረስ ምልክቶችን ያደርጋል የተባለ ነው፡፡ በጭካኔው ደግሞ ከዚህስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል በሚል አለም የሚከተለው ነው፡፡
አሁን አብይ ዋናው ጸረ ክርስቶስ አይደለም፡፡ ግን ከጸረ ክርስቶሶች አንዱ ነው፡፡ በማታለል መጣ፡፡ ክርስቲያን የተባሉትን ሁሉ የእርሱ ተከታይ አደረገ፡፡ እርሱን የሚከተሉ፣ የሚቀበሉ፣ ሌላው እንዲቀበለው ግፊት የሚያደርጉ፣ የሚነቅፈውን የሚተቹና የሚሳደቡ ሰዎች በክርስትና ስም ይንቀሳቀሳሉ፡፡ አብይ እንደማሳያ ቢወሰድ እነዚህ አብይን የተቀበሉት ሰዎች ዋናው ሃሳዊ ሲመጣም ለመከተልና ለመታለል ቅርብ እንደሆኑ ያረጋግጣል፡፡
ዋናው ጸረ ክርስቶስ ከ3.5 አመት በኋላ የገዛ ቃሉን እንደሚያጥፈውና እስራኤልን ከቦ እንደሚጨፈጭፈው፤ አብይም የኖቤል ተሸላሚ የሆነበትን የሰላም አምጭነት ሚና በሶስት አመት ተኩል ረስቶ ኢትዮጵያም አፍሪካም አይተውት የማያውቋቸው ጦርነቶችን የከፈተ ሰው ነው፡፡
ዋናው ሀሳዊ መሲህ እሳት እንኳ ከሰማይ እስኪያዘንብ ድረስ የሚያደርግ ነው፡፡ አብይም በእጁ ያለውን ድሮንና ሌላ ነገር ያልታጠቀ ህዝብ ላይ እንኳ ለማዝነብ ወደኋላ የማይል፣ ለጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ልዩ ፍቅር ያለው ነው፡፡ በ3.5 አመት አሳሳች መልኩን ቀይሮ በእውነተኛ ማንነቱ የተገለጠ ሰው ነው፡፡
ሀሰተኛው ክርስቶስ በክርስትና ስም እንደሚመጣው ሁሉ ይሄም በክርስትና ስም እየማለ የመጣ ሃሳዊ ነው፡፡ መሪ ከሆነ ጀምሮ አንድም የእውነተኛውን ክርስቶስ ስራ አልሰራም፡፡ ይልቅም ጭካኔ፣ ማስመሰል፣ ደም ማፍሰስ ነው ስራው፡፡ መጽሀፉ ሌባው ሊያርድና ሊሰርቅ ነው የሚመጣው እንዳለው ነው፡፡ በምንም መልኩ ሌላውን በሰይፍ የሚቀጣ የክርስቶስ ጠላት ነው፡፡ ክርስቶስ ሰይፍህን ወደሰገባህ መልስ ብሏል፡፡ ይሄ ደግሞ በተቃራኒው ከሰይፍም ድሮን የሚታጠቅ ነው፡፡
አብይ ልክ እንደ ዋናው ሀሳዊ ራሱን ከፍ ከፍ ማድረግ ይወዳል፡፡ ይሄም በዋናው ሀሳዊ ውስጥ የሚያድረው በልኡል እመሰላለሁ፤ ወደላይም ከፍ ከፍ እላለሁ፤ ከደመናዎች በላይ ዙፋኔን እሰራለሁ ብሎ በመፈንቅለ እግዚአብሄር ወደታች የወረደ ነው፡፡ ለራሱ መውደቁ አንሶ አዳምና ሄዋንን የተሰጣቸውን ኑባሬ ትተው የፈጣሪን ችሎታ እንዲመኙ ያሳሳተ ነው፡፡
ይሄ ከሁሉ በላይ እኔ ብቻ ልሁን የሚል ባህርይ ምንጩ ከጥንቱ ዲያብሎስ ነው፡፡ በመሪነትም ሆነ በምንም መንገድ ይሄን ባህርይ የሚያንጸባርቁ ሰዎች (በራሱ በክርስትናውም ውስጥ እኔ ብቻ የሚሉ ሰዎች) ባህርያቸው የሚቀዳው ከዚህ ከራስ ወዳድ ሀሰተኛ የወደቀ መልእክ ነው፡፡ ከስዎች በላይ ለመሆን መጣር፣ ስልጣንን መውደድ፣ ከፍ ብሎ ለመታየት መጣር ምንጫቸው ከአሳሳቹ ነው፡፡ የትክክለኛው ባህርይ ራስን ዝቅ ማድረግ እና ትህትና ነው፡፡ የአለም ገዥዎች በሰረገላዎች ታጅበው በሚሄዱበት ዘመን በአህያ ውርንጫ ሆኖ የመጣው ነው ትክክለኛው፡፡ የዚያኔ ባለሰረገላዎች የአሁኖች ባለጀት፣ ታንክና ድሮኖች ናቸው፡፡
ዋናው ሀሳዊ ሲመጣ አለም እንደሚከተለው፤ የኢትዮጵያና የልብያ ሰዎችም ይከተሉታል የተባለውን ለመረዳት ገና በዚህ በትንሹ ሀሳዊ አብይ ተማርከው የተከተሉትን አማኝ ተብየዎች ማየት ነው፡፡ ዳሩ ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን የተባለውም ለዚያ ነው፡፡ ሁሉም አስመሳዩን ስለሚከተሉ ነው፡፡ ስለዚህ አብይ ማሳያ ነው፡፡ አብይን የሚከተል ሁሉ ዋናው ሲመጣም ለመከተል ቀዳሚው እንደሚሆን ማሳያ ነው፡፡
አብይን የሚከተሉ ሰዎችም ከክርስቶስ በፊት የመጣውን ሀሳዊ እንደተቀበሉ መጽሀፉ ያጋልጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ “ኢትዮጵያ የመጎብኘትሽን ዘመን አስቢ” ሲሉ ነበር፡፡ ይሄ አስተሳሰብ በራሱ ሀሰት ነው፡፡ ይሄ ቃል ለእስራኤል እንጅ ለኢትዮጵያ አልተጠቀሰም፡፡ ሙሴ ነው ያሉም አሉ፡፡ ይሄም ሀሰት ነው፡፡ አብይን እግዚአብሄር ነው የሾመው ሲሉ ጥቅስ ይጠቅሳሉ፡፡ መበለቲቱን አትበድል፤ ደሀውን አትበድል፣ አትግድል፣ አትዋሽ፣ አትስረቅ የሚሉትን ቃላት ግን አያስተውሉም፡፡ ስለዚህ ሀሰተኞች ናቸው፡፡ ጳውሎስ መሪዎች ጨካኝ ቢሆኑ እንኳ ለህግ ተላላፊዎች ነው ቢልም የእነዚህ አብይ ህጻናትን፣ እናቶችን፣ አዛውንቶችን፣ ባጠቃላይ እንኳን ህግ ሊተላለፉ ህግ ለመተላለፍ ሀሳብ የሌላቸውን በጅምላ የሚጨፈጭፍ ነው፡፡
ልብ በሉ፦ በምድር ላይ የእውነተኛው መሲህ ባህርይ ኖሮት የሚመጣ መሪ እንዳለ መጽሀፍ ቅዱስ አይናገርም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ የሚናገረው ራሱ ክርስቶስ ብቻ እንደሚመጣ፣ በመላው አለምም ላይ ሰላምን የሚያመጣ እርሱ ብቻ እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ አማኞች ከክርስቶስ ዳግም መምጣት ውጭ የሚጠብቁት ሌላ መሲህ እንደሌለ ነው፡፡ ከክርስቶስ በፊት የሚመጡ ሃሳዊያን ናቸው፡፡ ምድራዊ ገዥን እንደሚሲህ መቀበል እውነተኛውን እና ሊመጣ ያለውን መሲህ መካድ ነው፡፡
ባጭሩ ሌላ መሲህ ወይም መሲህ መሳይ መሪን የሚሹ ሁሉ ከሀሰተኛው ወገን ናቸው፡፡ እና አብይ አማኝ ነን ያሉትን ሁሉ አስቷል፡፡ ችግሩ ግን የሳተ እንደሳተ አለማወቁ ነው፡፡ መነፈሳዊ ነገር ሲሆን አእምሮ በዚያኛው ሀይል ስለሚያዝ አያስተውሉም፡፡