Page 1 of 1

ለአብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ማለት የአራት ኪሎ ስልጣኑ ብቻ ነው

Posted: 08 Sep 2023, 01:43
by TGAA
ለአብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ማለት አራት ኪሎ ብቻ ነው ፤ አራት ኪሎ ስልጣኑ ሲነቃነቅ ፤ የአብይ ደጃፍ በኢትዮያ ባንዲራ ያሸበርቃል ፤የኢትዮጵያን ባንዲራ የያዙ ወታደሮች ስለጀግንነታቸው ይዘመርላችዋል ፤ አብይ ደጃዝማቸ አባ ነፍሶ ይሆናል አዳነች አቤቤ ጣይቱ ቡጡል በፊት ለፊታችን ትቀየራልቸ ፤ ፋናና ኢቢስ ኢትዮያዊ የጦር ጅግኖችን ከየቦታው ሰብስበው ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ ፤ ወያኔዎች ወደ አዲስ አበባ ሲገሰግሱ የሆነው ይሄው ነው ፤ አሁን ደግሞ ፋኖ ትጥቅ እያስፈታ ወደ አራት ኪሎ ግቤ ነው ብሎ ሲገሰግስ አብይ ፤ አዳነች ፤ሽመልስ የሰሞኑ የኢትዮጵያዊነት ሰባኪዎች ናቸው ፤ አንዴ አሞኝኝ ህፍረቱ ያንተ ነው ሁለቴ ካሞኝሀኝ ሀፍረቱ የኔ ነው እንደሚባለው ፤ የጓዳ ጸረ ኢትዮጵያዊያን የደጃፍ ኢትዮጵያዊያንን በዚህ አምስ አመት ብዙ ግዜ ተሸውደን አሁን መልካቸውን ሳይሆን ታኳቸውን አይተን መናገር የምንችል አዋቂዎች ሆነናል ; ኢትዮጵያኖች እንዳትሞቱ ሳይሆን ስትሞቱ መቃብራችሁ ላይ ዛፍ እንተክልላችኋለን ብለው የተመጻደቁብን ኢትዮጵያን ጀግኖችን አወድሰው አያሳሳቱንም፤ ቤት እናትና ህጻን ላይ እየደረመሱ ከህገወጥ ድህነት ወደ ህጋዊ ድህነት አሸጋግረናችኋል ብለው ሲሳልቁብን የነበሩ አሁን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ብለው አያወናብዱንም ፤ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ተከፍለው የኦሮምያን የብሄራዊ መዝሙር በሊላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር መዘመር አለበት ብለው ፖሊስ እየላኩ ኢትዮጵያዊነት ሲያሳድዱ የነበሩ ፤ አሁን አዲስ ጸበል ተጠምቀዉ አራት ኪሎ ላይ ለመንጠልጠል ከኛ በላይ፤ ኢትዮጵያዊ የለም ብለው ድራማ ቢሰሩ በአንድ አመት ውስት እንኳን ያደገ ጨቅላም ይህንን ስራቸው አይረሳም ፤ ጮሌው በሻሻ ግን ኢትዮጵያዊያን ትውስታቸው የጥቂት ግዜ ነው ብሎ ስለሚያስብ በዛሬው ቀን ሀገር በመሰዋአትነት ትጽናልቸ እያለ በሬዲዮና በቲቪ የህዝቡን ጆሮ ያደነቁራል ፤ ሀገር በመስዋትነት ትጸናልቸ ነገር ግን አራት ኪሎ አይደለም ሀገር ፟የበሻሻው ጮሌ ፤ ሀገር ማለት ኦሮሞ ጠል እያልክ የሰደብከው አዲስ አበቤን ፤ ለሀገሩን ለማጽናት የዘመተው ፋኖ አሁን በጸረ አማራነት ያለ የሌለ ጦርህን የዘመትክበት ኢትዮጵያዊ ፤ በጉጂ ፤ በጉራጌ የምትዘምትባችዋ ኢትዮጵያን ናቸው ፤ ሀገር ማለት አራት ኪሎ ከመሰለህ ምን ያህል እንደተሳሳትክ በቅርቡ ትረዳዋልህ ፤ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !