Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ኢዜማ የምሁራን ማህበር እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም

Post by TGAA » 08 Sep 2023, 02:02

ኢዜማ የጀርባ አጥንት የሌላቸው ፤ በቃላት ስንጠቃ እውነትን ሸፋፍነው የሚያልፉ የአድርባዮች ስብስብ ነው ፤ በዜግነት ስም ጎሰኝነትን የሚያጠናክሩ ፤ ለብሄራዊ አንድነት የሚታገሉትን ከጎሰኞቹ የበለጠ የሚያጠቁ ምሁር የሚባል ስያሜ የማይገባችው በህዝብ ስቆቃን ቃላት በማሽሞንሞን የዚህን ደም መጣጭ ስርአት የሚደግፉ ሞራል ኢትክስ ምን እንደሆነ የማያውቁ ስብስብ ናቸው ፡፡ ስለዚህ እንደ ድርጅት መፍረስ አለባቸው ፡

Horus
Senior Member+
Posts: 42666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ የምሁራን ማህበር እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም

Post by Horus » 08 Sep 2023, 02:14

እኔ እዚህ አሰልቺ ዶክመንት ውስጥ ግብቼ ነጥብ በነጥብ ስህተቶቹን ማሳያ ግዜውም ትግስቱም የለኝም ። ግን ለምንድን ነው ኢዜማ የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን የምሁራኖች ውይይት ፎረም ነው ያልኩት?

ቀረበ የተባለው የፖለቲካ ጥናት ስህተት ነው ። የቀረበው ዶክመንት የፖለቲካ ፍልስፍና አይደለም ። ቀረበ የተባለው ጥናት የፖለቲካ ቲኦሪ አይደለም። ቀረበ የተባለው ዶክመንት የፖለቲካ ስልት አይደለም ። ቀረበ የተባለው ዶክመንት የፖለቲካ ትግበራ ወይም ፕራክቲስ ገለጻ አይደለም ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም ማህበረሰብ ለምንድን ነው አመጸኛ የሆነው? ለምንድን ነው ቅራኔዎቹን በንግግርና ሰላም ሳይሆን በመደባደብና በጦርነት የሚፈታው የሚለው ጥያቄ የሃይማኖት ወይም የታሪክ ጥያቄ ሳይሆን የሳይኮሎጂና የማህበራዊ ስነ ባህሪ ወይም የሶሺያል ቢሄቪየር ጥያቄ ነው ።

የታሪክና ሃይማኖት ጥያቄ ሳይሆን የሶሺያ ሳይኮሎጂ ፣ የሶሺያ ቢሄቪየር ጥያቄ ነው ።

ስለዚህ ክርስትና ሲገባ ምንት ስ ሆነ፤ በ1960ቹ ምንት ስ ሆነ፤ ያለፈው 30 አመት ምንጽጽ ሆነ የሚለው የታሪክ ዝባዝንኬ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለምን አመጻዊ ሆነ ለሚለው መልስ አይሰጥም ።

ስለዚህ የኢዜማ ምሁራን ፎረም አባላት ሲጀመር መጠየቅ ያለት ጥያቄ ምን እንደ ሆነ አላገኙትም ።

የሰዎች፣ የቡድኖች፣ የመደቦች፣ የመንግስቶች ፖለቲካዊ ተግባር ፣ ስራ፣ ባህሪ ነው፤ ቢሄቪየር ነው ። አመጽ ተግባር ነው ። ጦርነት ተግባር ነው ። የሰዎች ባህሪ ነው ። ሰላም (ውይይት) ንግግር ተግባር ነው ፣ ስራ ነው፣ ባህሪ ነው። ስለሆነም አንድ ግላዊም ሆነ ማህበራዊ ኩነት ንግግር መሆኑና ወይም ጦርነት መሆኑ በታሪክ በመመዘገብ ምንም የሚገኝ ፋይዳ የለም ።

ለምንድን ነው የአበሻ ፖለቲካ አመጻዊ የሆነው ለሚለው ጉዳይ መጠየቅ ያለበት ሰዎች በፖለቲካ ጦርነትም ሆነ ንግግር ሲጠመዱ የሚነዳቸው ጥቅም ሞቲቬሽን ምንድን ነው ተብሎ ሲጠየቅ ነው መልሱ የሚገኘው ።

የግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ባህሪን የሚነዱ ፍላጎቶች አሉ! ምንድን ናቸው? ይህ ነው ጥያቄው ።

በአጭሩ ኢትዮጵያዊያን እንደ ግለሰብም ሆነ ቡድን የሚፋጩት ለኃይል ነው፣ ለስልጣን ነው ። ኃይልና ስልጣን የያዙት ሰዎች በሰላምና በፈቃዳቸው ያን ኃይል ከሌሎች ጋር መጋራት አይፈልጉም ።

ግለሰቦችና ቡድኖች የሚፋጩት ለሃብት ነው ። ዛሬ ሃብት የያዙት ቡድኖች በንግግር በሰላም የያዙትን ሃብት (ሪሶርስ) ከሌሎች ጋራ መጋራት አይፈልጉም ።

ክብርም ፣ ዝናም እንዲሁ !!! በነዚህ 4 ፈንዳሜንታል ጽንሰ ነገሮች ፤ ኃይል፣ ሪሶርስ፣ ክብር (የበላይነት) እና ዝና (ታዋቂነት) ሳንሳዊ በሆነ የፖለቲካ ሳይኮሎጂ ጥናት እንደ ማቅረብ አሰልቺ የታሪክ መላምት እንደ ፓርቲ አይዲዮሎጂ የሚያምታቱ የኢዜማ ምሁራን ውዥንበር ኮንፊዩዥን ነው ።

የፖለቲካ ባህሪ መተንተኛ ኮንሴፕት ኃይል (ፖወር) ወይም ስልጣን ነው ። በኢዜማ ዝብዝብ ውስጥ አንዴም አይነሳም !

Horus
Senior Member+
Posts: 42666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ የምሁራን ማህበር እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም

Post by Horus » 08 Sep 2023, 02:42

TGAA፣
እነዚህ የኢዜማ ምስኪን ምሁራን አለመስካቸው ለግዜ ማሳለፊያ የፓርቲ አባል ሆነው መሳቂያ እየሆኑ ነው ።

እነዚህ የፖለቲካ ሲሲ ድመቶች ናቸው ።

ዛሬ አንድ የኦሮሞ ወታደር 'ወደዳችሁም ጠላችሁም የኢትዮጵያ ባለቤት (owner) ኦሮሞ ነው' አለ ። ይህ ነው ፖለቲካ የሚባለው ።

አንድ ሰው ወይም ቡድን ወይም መደብ የፖለቲካ ኃይል ሲጨብጥ ማን ምን ማድረግ/አለማድረግ እንዳለበት ይወስናል ። ማን ምን መሆን እንዳለበት/እንደሌለበት ይወስናል (ልብ በል አባዱላ ደቡብ እንዴት መደራጀትና ምን አይነት ማንነት መያዝ እንዳለበት ሲወስ)። አንድ ኃይል ማን ምን ማግኘት እንዳለበት ቤት፣ ገንዘብ ሃብት ወዘተ ... ይህ ነው የፖለቲካ ጥያቄ እምብርትና ነፍስ!!!! The essence and soul of politics. ይህን ይዘህ የብርሃኑ ነጋ አሰልቺ ፣ ባዶ ፣ ዚዚዚዚ ያስታውክሃል! እነዚህ ድመቶች ናቸው !!! እንኳንስ የፖለቲካ ስልጣን የፖለቲካ አክብሮት አጠገብ አይደርሱም!!! ያሳፍራሉ !!

Horus
Senior Member+
Posts: 42666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ የምሁራን ማህበር እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም

Post by Horus » 08 Sep 2023, 03:09

ፖለቲካ ማለት ይህ ነው ። የኃይል፣ የሪሶርስ፣ የበላይነት ትግል ነው ! ይህ ትግል በንግግር ከሆነ ሰላማዊ ፖለቲካ ይባላል ! ባልስልጣኑ እምቢ ሲል ፖለቲካው በአምጽ ይካሄዳል ! ስለዚህ ጦርነት የፖለቲካ ዘዴ ነው ። ንግግር የፖለቲካ ዘዴ ነው። ፖለቲካ እራሱ የኃይልና ሪሶርስ ባለቤትነት ትግል ነው ! በቃ እዚህ ቪድዮ ውስጥ ትልቁ ፖለቲከኛ ፋኖ ነው! ጦርነት ፖለቲካ ነው !


Post Reply