Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15385
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የመከላከያ ሰራዊት ሥነ-ምግባር አሁን በአማራ የሚያሳየውን አይነት ከነበረ ወያኔ በሰሜን ዕዝ ኮማንድ ላይ በደረቀ ሌሊት የወሰደችው እርምጃ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? አስተያዬትዎን ይስጡ።

Post by Abere » 06 Sep 2023, 15:55

የ"መከላከያ ሰራዊት" ሥነ-ምግባር አሁን በአማራ የሚያሳየውን አይነት ከነበረ ወያኔ በሰሜን ዕዝ ኮማንድ ላይ በደረቀ ሌሊት የወሰደችው እርምጃ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? ሌባውን ሌባ ቢሰርቅ ምን ይደንቅ ይሆን? አስተያዬትዎን ይስጡ።


Abere
Senior Member
Posts: 15385
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የመከላከያ ሰራዊት ሥነ-ምግባር አሁን በአማራ የሚያሳየውን አይነት ከነበረ ወያኔ በሰሜን ዕዝ ኮማንድ ላይ በደረቀ ሌሊት የወሰደችው እርምጃ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? አስተያዬትዎን

Post by Abere » 09 Sep 2023, 18:58

የኦነግ መከላከያ ሰራዊት በትክክል በትግራይ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ፤ ስርቆት፤ ሴት የመድፈር ወንጀል መፈጸሙን አሁን ከምናየው ስነ-ምግባሩ አንጻር መረዳት ይቻላል። የወያኔ የመሰሪነት፤ የውሸት እና ወንጀለኝነት ባህርይ ግን ብዙውን የ የኦነግ-መከላከያ ሰራዊት እንሰሳዊ ወንጀል ደብቆታል። በኦነግ መከላከያ ምትክ የአማራ ፋኖ ትግራይ ውስጥ ገብቶ የማረጋጋት ስራ ቢሰጠው የትግራይ ህዝብ ይህን ግዜ ዕፎይታ ላይ ነበር። አስታውሳለሁ የሸዋ ምኒልክ ፋኖ "መቀሌ በመሄድ የትግራይ ወገናችንን ከወያኔ ግፍ ነጻ ማውጣት ነው" ሲል። ዳሩ ግን ኦሮሙማ -ኦነግ አብይ አህመድ ያን አልነበረም የሚያስበው - የትግራይን ህዝብ አንገት ማስደፋት እና ሰጥ ለመጥ ብሎ ለእርሱ እርሱ በሚሾማቸው እንደራሴ ወያኔዎች እንድገዛለት ማድረግ ነበር። ትግራይ ቢታድለ ኑሮ ፋኖ ገብቶለት በነበር ነበር። የሽሬ ኗሪዎች ስለፋኖ ስነ-ምግባር መስክረዋል - ወያኔ ሰርቆ የደበቀውን ስንደ ፋኖ አግንቶት ህዝቡን በሰልፍ ስርዐት አስይዞ ሲያከፋፍል ከርሃብ ሲታደጋቸው።
Misraq wrote:
06 Sep 2023, 17:30
የኦሮሞ መከላከያ ትግራይ ውስጥ ወንጀል ፈጽሞዋል የሚል እምነት እያደረብኝ መጥቶአል

Axumezana
Senior Member
Posts: 19128
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የመከላከያ ሰራዊት ሥነ-ምግባር አሁን በአማራ የሚያሳየውን አይነት ከነበረ ወያኔ በሰሜን ዕዝ ኮማንድ ላይ በደረቀ ሌሊት የወሰደችው እርምጃ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? አስተያዬትዎን

Post by Axumezana » 09 Sep 2023, 23:36

ኤርትራዊው፥ አበረ፥ ብዙ፥ታወራለህ ፥ ትሸፋፍናለህ!
የአማራ፥ ታጣቂ፥ የጦር፥ወንጀል፤ የዘር፥ማፅዳትና( እስከ አሁን፥ ድረስ) crime against humanity በትግራይ፥ ላይ፥ እንደፈፀመ፥ በገለልተኛ፥ የሶስተኛ፥ አካል፥የተረጋገጠ፤ጉዳይ፥ ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 15385
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የመከላከያ ሰራዊት ሥነ-ምግባር አሁን በአማራ የሚያሳየውን አይነት ከነበረ ወያኔ በሰሜን ዕዝ ኮማንድ ላይ በደረቀ ሌሊት የወሰደችው እርምጃ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? አስተያዬትዎን

Post by Abere » 10 Sep 2023, 13:16

የትግራይን ህዝብ የጨፈጨፉት ሁለት ወንጀለኛ ቡድኖች

1ኛ) ወያኔ/ትህነግ

2ኛ) የኦነግ መከላከያ ሰራዊት ናቸው።

ከዚህ ውጭ ያለው የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳ ስማቸው ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ወንጀለኛ ቡድን ተከፋዮች የሚነዛ የውሸት ወሬ ነው። You are among those on TPLF's payroll list. ገለልተኛ ቡድን መቸ ተቋቋመና፤ የትርዒቱ ቀንደኛ ተዋናዮች እንጅ።


Axumezana wrote:
09 Sep 2023, 23:36
ኤርትራዊው፥ አበረ፥ ብዙ፥ታወራለህ ፥ ትሸፋፍናለህ!
የአማራ፥ ታጣቂ፥ የጦር፥ወንጀል፤ የዘር፥ማፅዳትና( እስከ አሁን፥ ድረስ) crime against humanity በትግራይ፥ ላይ፥ እንደፈፀመ፥ በገለልተኛ፥ የሶስተኛ፥ አካል፥የተረጋገጠ፤ጉዳይ፥ ነው።

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የመከላከያ ሰራዊት ሥነ-ምግባር አሁን በአማራ የሚያሳየውን አይነት ከነበረ ወያኔ በሰሜን ዕዝ ኮማንድ ላይ በደረቀ ሌሊት የወሰደችው እርምጃ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? አስተያዬትዎን

Post by Assegid S. » 13 Sep 2023, 15:15

በእኔ በግሌ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ውስጥ ወንጀል ፈፅሟል ብዬ ለማመን የተቸገርኩት በሠራዊቱ ዲሲፕሊንና ግብረገብ ላይ እምነት ኖሮኝ ሳይሆን እንኳን ለሰው ለኣምላክም ቢሆን ከመዋሸት የማይመለሱትን የወያኔን ፕሮፓጋንዲስቶች ፈፅሞ ማመን ባለመቻሌና ስለማላምንም ነው።

አለበለዚያ ግን ገና ጥንት መከላከያው የጠቅላይ ሚንስትሩ ዘበኛ እንጂ የሀገርና የህዝብ አርበኛ እንዳልሆነ ገና በ2022 ተረድቻለሁ። ዘበኛ ደግሞ ቆሞ የሚውለውም ሆነ የሚያደርው ለህሊናው ፍርድ ሳይሆን ለሆዱ ፍላጎት ብቻ ነው።

ኣማራ፦ መረረህም ጣፈጠህም ይህን እውነት መዋጥ አለብህ። የሃምሳ ብር ካኔቴራህ ላይ “ከመከላከያ ጎን እቆማለሁ” እያልክ የምታቅራራው አንተ እንጂ፥ መከላከያው ከአንተ ጎን አልቆመም። ያ ባይሆን ኑሮማ ለኣቅመ–ሔዋን ያልደረሰች የወሎና ሸዋ ልጃገረድ ልጅህ በራስህ ቤት – በራስህ ደጃፍ ላይ ወላጅ እናቷ እየተመለከተች ባልተደፈረች፣ ጎበዛዝቶችህም ጥይትና የቡድን መሳሪያ ተከልክለው በህወሃት ከባድ መሳሪያ በጅምላ ባላለቁ ነበር። እውነቱ ይኼ ነው፦ መከላከያው የቆመው ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጎን ነው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩም የቆሙት … ከሚፈሩት “ነገ ከህወሃት ነጥዬ ጎኔ አቆመዋለሁ” ከሚሉት አፍቃሪ–ትህነግ ጎን ነው።

ይህንን የምለው የኣማራው ደህንነት የጠቅላይ ሚንስትሩ “በጎ ችሮታ” ነው ብዬ በማሰብ አይደለም። ኣማራው ለራሱ እራሱ እንደማያንስ ጠንቅቄ አውቃለሁ። ነገር ግን እንደ ክፉ ዕድል ሆነና “ተላላኪ” እንጂ ተሟጋች መሪ ውጥቶለት አያውቅም። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ኣማራው ክብር አይደለም ክልል አልባ ሆኗል። መንግስት በሚሰራበት ሸፍጥ ከኦሮምያና ቤንሻንጉል አይደለም ከራሱም ክልል በሺህዎች ይፈናቀላል፣ በመቶዎች ይገደላል። ይህ ማህበረሰብ ለደረሰበት ዝቅተኛ ውርደት ግንባር ቀደም ተጠያቂው … የታሪክ እድፍ፣ የዘር ጉድፍ የሆነው ብአዴን ቢሆንም፤ በገጠርም ይሁን በከተማ ላለው ኣማራ ደህንነት ቀሪ ተስፋ ግን መሪ ሳይሆን መሣሪያ ብቻ ነው። ፋኖ ተሰማራ … እንደ ጎቤ – እንደ አዝመራ!
ይናገራል ፎቶ ( January 7 2022 )



Post Reply