TGAA wrote: ↑30 Aug 2023, 01:05
TGAA,
ይህ ምኒልክ የሚባል ሰው ምን ዓይነት ፍጡር እንደ ነበር ታውቃለህ ! ይህን ታሪክ ልንገርህ፤ የምታውቀው ከሆነ ላስታውስህ!
በኢትዮጵያ የመንግስት ሰላይ (የዛሬ ሲክሬት ኤጀንት)' ነጭ ለባሽ ' ይባላል ። ለምንድን ነው ሰላይ ነጭ ለባሽ የሚባለው? የተባለው? ነገሩ የሆነው በስንት አመተ ምህረት እንደ ሆነ አላውቅም ፣ የሚያውቁ ጀባ ሊሉን ይችላሉ ! ነገሩ እንዲህ ነው ።
ድሮ ድሮ ምኒልክ የሰዉ አኗኗር ለማየት ፣ የገበያው ጥጋብ መሆን ፣ ይህዝቡ ደስታ ወዘተ ለማየት (የገበያ ጥጋብ ማለት የፍጆታ ቁሳቁሶች፣ ምግቦች በያይነቱ ገበያ ውስጥ መትረፍረፍ ማለት ነው) ካጃቢያቸው ጋር ሆነው ገበያ ይወጡ ነበር ።
አሁን አንድ ቀን መኳንንቶቻቸው አንድ ሃሳብ አቀረቡ። ባገሪቱ ምን እንደ ሙካሄድ፣ ሰው ምን እንደ ሚል፣ በመንግስት ላይ ያለ የሕዝብ ሃሜት (የዛሬ ፓፕሊክ ኦፒኒየን!) ለመሰብሰብ ሰላዮች (ጆሮ ጠቢዎች) ይደራጁ የሚል ፖሊሲ አርቅቀው ጃንሆይ ጋ ቀረቡ ።
ሃሳቡን እስከ አላማው ዘርዝረው አስረዱ ለንጉሱ ። አጼ ምኒልክ በጥሞና ካዳመጡ በኋላ (የሃሳቡ ጥቅምና ግን ያዘለው የሞራል ስህተት አጢነው) ምን ቢሉ ጥሩ ነው! "ሃሳባቹ መልካም ቢሆንም እንዴት ብዬ በራሴ ሰው ላይ ሰላይ አደርግበታለሁ? አይ አስፈላጊ የምትሉ ከሆነ ደሞ ሰዉ ሁሉ በውል እንዲለያቸውና እንዲጠነቀቅም ነጭ ልብስ አልብሷቸው ብለው አዘዙ ።
ስለዚህ የመጀምሪያው የኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት ሴኩሪቲዋች ልዩ ነጭ ልብስ (ነጭ ዩኒፎርም) ለብሰው ሰው ሁሉ ያውቃቸው ነበር ። ታላቁ ሚኒልክ ፣ የተፈጥሮ ጂኒየስ የተቸረው የሴኩሪቲ አላማው ሰዎች ሕግ እንዳጥሱ ለማስጠንቀቅ እንጂ እስከ ሚሳሳቱ ተደብቆ በመጠበቅ ይዞ ለመቅጣት፣ ሕዝብ ለመጉዳት አይደለም የሚል ከዘመኑ በሺ አመት የቀደመ ሎጂክ ያሳየን መሪ ነበር ታላቁ ምኒልክ !!
በዚያ ምክንያት ነው እስከ ዛሬም ሰላዮችን ነጭ ለባሽ የምንላቸው !!! " ሰዉ ሁሉ እንዲያውቃቸው ነጭ አልብሷቸው" አለ ምኒልክ !!! ዛሬ ግ ን ሰዉ ሁሉ እንዳያውቃቸው ፊታቸው በዉሸት ቆዳ ይሸፍናሉ! መንግስት የሕዝብ ጠላት ነው ዛሬ !
ዛሬ የማንም መንግስት ምን ማለት እንደ ሆነ ፣ መሪነት ምን ማለት እንደ ሆነ ቃሉን የማያውቁ እበት ለቃሚ እረኞች ናቸው ከምኒልክ ጋራ ትከሻ ሊጋፉ የሚዳዳቸው ባለ ግዜ ኩበቶች !