sarcasm wrote: ↑03 Jan 2024, 08:29
"አሁንምኮ ስሰማ
ጥላቻ አለ በኣፋቹ፤ በልባቹ። . . . . አይጠቅምም ጥላቻ ለኢትዮጵያ። ትግሬን መጥላት ምን ይጠቅምላቹሃል?" ፕ/ሮ ኤፍሬም ይስሃቅ
ስሜት ጥላቻ ሊሆን ባይችልም ጥላቻ ግን ስሜት ነው። ሰው ደግሞ ያለ ኣንዳች ምክንያት (stimuli) ጥሩም ሆነ መጥፎ ሊሰማው (ስሜት ሊያዳብር) አይችልም። በምክንያታዊነት ለሚያምን ማህበረሰብ ውጤትን ብቻ ገንጥሎ በማውጣት ሚዛናዊ ፍርድ ስጠኝ ብሎ መክሰስ አይቻልም።
እውነት ለመናገር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግራዋይ የሆነ ግለሰብ ላይ ጭፍን ጣላቻ አለው ብዬ አላምንም፤ የለውምም። ነገር ግን እንደ ፕሮፌሰሩ ያሉ ፖለቲከኞች ህወሃት በመላው ህብረተሰባችን ላይ ያደረሰውን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግፍ ወደኃላ በመግፋት … ኣንድን የፖለቲካ ድርጅት ከአጠቃላይ የትግራይ ማህበረሰብ ጋር በመፐወዝ ‘
ትግሬን መጥላት ምን ይጠቅምላቹሃል?’ የሚል ጥያቄያቸው ውሃ የሚያነሳ አይደለም። ምናልባትም እርሳቸው እራሳቸው ሊገባኝ ባልቻለ ምክንያት በኣማራው ብሔር ላይ (እንደዚህ post thread አቀራረብ ማለቴ ነው) ጥላቻ ስላላቸው የድምዳሜያቸውን መነሻ ምክንያት ወይንም መሠረት ለመመልከት አልፈለጉም እንጂ ‘ለምን?’ ብለው ቢጠይቁ መልሱ ግልፅ ይሆንላቸው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ህወሃት ሲያጠቃ እንደ ጀግና ጎራ ‘
ድርጅት’ አድርጎ ማቅራራት … ሲጠቃ ደግሞ እንደ ‘
ማህበረሰብ’ ቆጥሮ 'ጄኖሳይድ' እያሉ ምድርን በጩኸት ማንደድ አይጠቅምም።
ከሁሉ በፊት ህወሃት በሰፊው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ በተለይም በኣማራው ብሔር ላይ ምን አይነት ግፍና ሰቆቃ ፈፀመ? በእርግጥ ፖለቲከኞችና የዲያስፖራ አባላት '
ህወሃትና የትግራይ ህዝብ ኣንድ ነው' የሚሉትስ ሓሳብ አግባብ ነውን? ብሎ መጠየቅና መመለስ ያስፈልጋል። ያኔ በእርግጥ ጥላቻው አለ ከተባለም የጥላቻው ምክንያት ግልፅ ስለሚሆን ለሚዛናዊ ፍርድ ይቀላል። አለበለዚያ ግን ይህ ምክንያትን ያላገናዘበ የጥላቻ ክስ ... አንድን የማያጨስ ግለሰብ ‘
ለሲጋራ ከፍተኛ ጥላቻ አለብህ’ ብሎ ለመውቀስ ከመነሳትና አውግዙልኝ ብሎ ከመጮህ የማይተናነስ በመሆን የሰውየውን ሚዛናዊነት (ጤንነት) ጥያቄ ውስጥ ያስገባል።