Page 1 of 1

የአማራ ፋኖና የአቢይ ኦነግ ወታደራዊ ቁመና ባጭሩ

Posted: 17 Aug 2023, 00:33
by Horus
የፋኖ ኃይል በአስር ሺዎች ፤ ፈጣን ንቅናቄ፤ አጥቅቶ መሰወር፣ በመማረክ መታጠቅ እና ጠላትን እረፍት መንሳት እና አይኮሎጂውን መስበር። ዋና አድቫንቴጅ፣ የአላማና ሞራል የበላይነት ።

የኦሮሙማ ኃይል ምናልባትም በመቶ ሺዎች፤ ከላይ እስከ ታች የተከፋፈለ፣ በመማረክ መሳሪያ አስረካቢ፤ የአላማን ሞራል ስብራት የተላበሰ ።

አቢይ ብዙ ዉጊያዎች ካደረገው በፍጥነት ፋኖ እንዲታጠቅ ያደርጋል ፤ አሁን እንደያዘው ፋኖ መሳሪያ እንዳይማርክ ብርሃኑ ጁላ ዉጊያዎችን ከቀነሰ ለፋኖ መደራጃ ግዜ ይሰጣል ። ያው አሁን ላይ አቢይ የመረጠው ዉጊያ በመቀነስ (ፋኖ እንዳይታጠቅ) ለፋኖ መደራጃ ግዜ መስጠት ነው ።

ለዚህ ወታደራዊ ሂሳብ መልስ እንዲሆን ነው ፋኖ ቋራና ሌሎችም የሱዳን እና ኢትዮጵያ ድምበሮች የተቆጣጠረው ። አሁን ፋኖ በብርሃን ፍትነት በከፈተው በር አማክይነት መሳሪያ ማስገባት አለበት ።

አይ ይህን አስቆማለሁ ብሎ አቢይ ዉጊያ ከገጠመ ደሞ ፋኖ ከአቢይ ወታደሮች በመቀማት መታጠቁን ይቀጥላል ማለት ነው።

አቢይ አህመድ ብረት አሸክሞ ወደ አማራ የሚልካቸው ኦሮማዊ ወታደሮች በበዙ ቁጥር የፋኖ ጦር መሳሪያ ግምባታ እየገዘፈ ይሄዳል ። ይህ ነው የሚሊታሪው ሁኔታ ትራጀክተሪ!